Translation is not possible.

‍ 👨የሕፃኑ አስደናቂ ታሪክ

•┈┈•❈••✦✾✦••❈•┈┈•

☞በአረብ አለም የሚኖር አንድ የአሥር አመት ታዳጊ ነው

ይህ ታዳጊ የሰራው ነገር ግን ሠውን አጃኢብ አስኝቷል።

ነገሩ እንዲህ ነው:

ይህ የአስር አመት ህፃን ዘውትር በሠላት ወቅቶች ከመሥጂድ ይታደማል

ሠላቱም በጀመዓ ይሠግዳል ድምፅ ከፍ ተደርጎ በሚሰገድባቸው ሦስት ሠላቶች ላይ ታዲያ ኢማሙ ፋቲሀን ቀርቶ ሲጨርስ ማለትም ወለዷ ሊን ሲል ሠጋጁ በአንድነት አሚን ሢል ይህ ልጅ ድምፁን ከፍ አድርጎ ከጀመዓው ተነጥሎ ብቻውን አሚን ይላል....

🔴ይህ ነገር በመደጋገሙ ኢማሙን እጅግ ያበሳጨው ነበር ቢያየው ቢያየው ልጁ ሊያቆም ስላልቻለ አንድ ቀን ከመግሪብ ሠላት በኃላ ንዴቱን መቆጣጠር ያቃተው ኢማም ይህን ልጅ እንቅ አድርጎ አንጠልጥሎ ያምባርቅበታል!

🤔ለምንድነው ምትረብሸው ከጀመዓው ጋር አብረህ ለምን አሚን አትልም እና መሰል ነገሮችን ይህን ህፃን ልጅ ተናገረው ይህ ታዳጊ በፍርሃት በተሸበሸቡት ልብሶቹና ቲማቲም በሚመሥሉ ጉንጮቹ እምባ ያቀረሩ አይኖቹ ያንን ኢማም በሥሥት እየተመለከቱ...

🗣«እኔ ምጮህው አለ......

እኔ ምጮህው እቤታችን መስጂዱ አጠገብ ነው አባቴ ደሞ ሠላት አይሰግድም ምናልባት የኔን ድምፅ ሢሠማ ደስ ብሎት አልያም ተደንቆ ከመጣና ከሠገደ ብዬ ነው ያ ኢማም» ብሎ መለሰለት ይህን ጊዜ ኢማሙ ሚናገረው ጠፋው ሠውነቱ ተርገፈገፈ የአከባቢውን ሠው አፈላልጎ ይህን ለአባቱ አደረሠው አባቱም በልጁ ተግባር እጅግ ተደንቆ ወደ ጌታው አልቅሦ ተውበት በማድረግ ሠላቱን ጀመረ።

🚫ሰዎችን አይተን ብቻ በችኮላ አንፍረድ። ይህን ለመስራት ያበቃቸው ምን ምክንያት ሊኖር ይችላል ብለን ኡዝር እንፈልግላቸው ምናልባት መጥፎ ሥራ የሚሰሩ መስሎን ሲፈተሽ ግን በጣም የሚደንቅ ሊሆን ይችላል!!

♥️ሱብሃን አላህ

በጣም ልብ የሚነካ ታሪክ ነው

"ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

ኮፒ,

Send as a message
Share on my page
Share in the group