Translation is not possible.

የኪሳኢይ ገጠመኝ እና ወሳኝ ማስታወሻ

ኪሳኢይ ረሒመሁላህ ትልቅ የዐረብኛ እና የቁርኣን ጥናት ሊቅ ናቸው። የሆነ ጊዜ የገጠማቸውን አስገራሚ ክስተት እንዲህ ይገልፁታል።

በአንድ ወቅት ኸሊፋው ሀሩን አረሺድ ዘንድ እያሰገድኩ ሳለሁ አቀራሬ መሰጠኝ። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለሁ ፈፅሞ ህፃን የማይስተውን ስህተት ፈፀምኩ። "لعلهم يرجعون" (ለ0ለሁም የርጂዑን) ለማለት ፈልጌ "لعلهم يرجعين" (ለ0ለሁም የርጂዒን) ብዬ ቀራሁ።

በአላህ ይሁንብኝ ኸሊፋው ሃሩን አረሺድ "ተሳሳተሃል!" ሊለኝ አልደፈረም። ይልቁንም ካሰላመትኩኝ በኋላ:

* "ኪሳኢይ ሆይ! ይሄ የምን አነጋገር ነው?" አለኝ።

= "የአማኞች አዛዥ ሆይ! የሰለጠነ ፈረስም'ኮ አንዳንዴ ይንሸራተታል" አልኩት።

* "ይሄስ ልክ ነው" አለ።

ኢማሙ ዘሀቢይ ረሒመሁላህ ይህን ታሪክ ከጠቀሱ በኋላ እንዲህ ይላሉ፦

"አእምሮው ይህንን ንግግር የተገነዘበ ሰው አንድ ዓሊም የፈለገ ያክል ደረጃው ከፍ ቢልና በዒልም ቢገን እንኳ ከስህተቶች የማይተርፍ መሆኑ ነው። እነዚህ ስህተቶች መገኘታቸው ግን አዋቂነቱን አያጎድፉም፡፡ ደረጃውንም ዝቅ አያደርጉም፣ አያጎድሉትምም። የእውቀትና የመልካም ገድል ባለቤቶችን ስህተቶች በዚህ መልኩ እየተረጎመ ያለፈ መንገዱ ምስጉን፣ አካሄዱም ድንቅ ነው። ለትክክለኝነትም የታደለ ይሆናል።"

ምንጭ:- [ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ፡ 1/376]

ሰዎች ላይ የሚታዩ ስህተቶች የተለያየ መልክ ይኖራቸዋል።

* አንዳንዱ ከሚያራምዱት አካሄድ የመነጨ አቋም ተደርጎ የተያዘ ስህተት ነው።

* አንዳንዱ የተሳሳተ መረጃ በመያዛችን ወይም በተሳሳተ መልኩ በመረዳታችን የሚገጥም ስህተት ነው።

* አንዳንዱ ደግሞ በሚገጥመን ጊዜያዊ ግርታ ሰበብ የሚከሰት ነው።

* ሌላው ደግሞ ትኩረት ባለመስጠታችን የሚከሰት ምናልባትም መሳሳታችንን እንኳ ሳናውቀው የሚከሰት ነው።

ሁሉንም ባንድ ጨፍልቆ መረዳት እንደማይገባ ጤነኛ ጭንቅላት አያጣውም። ይልቁንም እንደየ ሁኔታቸው መያዝ ይገባል። አንዳንዴ ደርስ እየሰጠን፣ ደዕዋ እያደረግን ሳለን ደግሞ ለመናገር እንኳ የሚሰቀጥጥ ቃል ያመልጠናል። ሰዎች ነንና እነዚህን የመሰሉ ስህተቶች ብዙዎቻችንን ይገጥሙናል። ከመሰል ስህተቶች የሚተርፉ ካሉ ምናልባት ይሄ ነው የሚባል ተሳትፎ የሌላቸው ይሆናሉ።

ትኩረቴ በተለይ የዑለማዎችን ወይም የዱዓቶችን ትምህርቶች ስንከታተል የሆነ ስህተት ሲገጥመን ሊደንቀን ወይም ልናራግብ አይገባም ለማለት ነው። በተለይ በመልካም የምናውቃቸው ከሆኑ። በጥፋት የምናውቃቸው እንኳ ቢሆኑ ድንገተኛ ስህተቶችን እንደ ቋሚ መንሃጅ አድርጎ ማራገብ አይገባም። ልብ በሉልኝ! ጥቆማ ወይም እርምት አይሰጥ እያልኩ አይደለም። ይልቁንም እራሳችን እንድንያዝበት በማንፈልገው መልኩ ሌሎችን ልንይዝ፣ ስህተቶችን በመጎርጎር ላይ ልንጠመድና አድብተን ልንጠባበቅ አይገባም ለማለት ነው። የድምፅ ትምህርቶች ወይም ከድምፅ ትምህርቶች ተገልብጠው የተዘጋጁ ኪታቦች ላይ እንዲህ አይነት ስህተቶች በብዛት ያጋጥማሉ። የነሕው ትምህርት ላይ የነሕው ስህተት ያጋጥማል። ሰው በቃል ሲናገርና ሲፅፍ አንድ አይደለም። በየእለቱ የምንናገረው አማርኛ ውስጥ ብዙ የሰዋሰው ግድፈት አለበት። ከድምፅ ትምህርቶች ተገልብጠው የተዘጋጁ ኪታቦች ላይ የሰዋሰው ስህተት አገኘን ብለዉ ዓሊሞችን የሚጎነታትሉ አካላት በተጨባጭ አሉ። በዚህ መልኩ ቢያዝ በርግጠኝነት ማንም አይተርፍም።

አንዳንዴ ደግሞ ስህተቱ ከኛ አረዳድ ይሆናል። የሆነ ጊዜ የሆኑ ሸይኽ በሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን የአጅሩሚያህ ሸርሕ ላይ ስህተት አገኘሁ በሚል መነሻ አጠቃላይ የሳዑዲ ዓሊሞችን ጎንተል ያደርጋሉ። ቦታው ላይ የነበሩ ወንድሞች ጉዳዩን አጥብቀው ይይዙትና ጭቅጭቅ ይከሰታል። ደግነቱ ሸይኹ ነፍሲያ አልያዛቸውም። በማግስቱ ስህተቱ የራሳቸው እንደሆነ አመኑ።

አንዳንዴ ደግሞ ዓሊሞቹ ፊትና ጋር የተያያዘ ጥያቄ ሲጠየቁ መልሱን ጥለው ምክር ወይም ቁጣ ያዘለ ተግሳፅ ይሰጣሉ። በዚህን ጊዜ አንዳንዶች የተጠየቀው ጥያቄ ላይ ብቻ በማነጣጠር "ሸይኽ እከሌ በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲህ አሉ"፣ "በእከሌ ላይ ተናገሩ"፣ "ለእከሌ ተከላከሉ" የሚል ደማቅ ርእስ ሰጥተው ያራግቡታል። በእንዲህ አይነት ጉዳይ ላይ ከስሜት ነፃ ሆኖ አላህን በመፍራት የዑለማኦችን ንግግር ያላግባብ ከመመንዘር መጠንቀቅ ይገባል።

ሳጠቃልል እራሴን ጨምሮ ለሁሉም የማሳስበው ከሆነ አካል ስህተት የመሰለን ወይም በርግጥም ስህተት የሆነን ንግግር ስናገኝ ከማራገባችን ወይም "ረድ" ብለን ለምላሽ ከመቸኮላችን በፊት አላህን በመፍራት ግራ ቀኝ ማየት እንደሚገባ ለማስታወስ ነው።

👇👇👇👇👇👇

ጥያቄአችሁን በዚህ ፃፉልን

👆👆👆👆❗️👆

https://t.me/OfficialDemas

Telegram: Contact @OfficialDemas

Telegram: Contact @OfficialDemas

ይህ ቻናል በአህለል ሱና ወልጀማዓ የተደረጉ ዳእዋዎችና በዲናዊ አዝናኝ ግጥሞች ፤ሀዲሶች ታሪኮች እናንተን ማዝናናት ነው። በተጨማሪም የተደበቁ የጴንጤዎች ተንኮልና አደጋዎች ወደ ህዝበ ሙስሊሙ ያደርሳል። በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተጋረጠ ወቅታዊ አደጋም ካለ እየመረመረ ያደርሳል። ይህ ሁሉ የሚሆነው በአሏህ ፈቃድ ነው። ይግቡ ይቀመጡ ይዝናኑ ይማሩ የናንተ ሚድያ ነው።
Send as a message
Share on my page
Share in the group