እስራኤል በሶስት ግንባሮች ጦርነት በማካሄድ ላይ ነች።
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ድንበሯን በመጣስ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ የአጸፋ ምላሽ እየሰጠችበት ያለው የጋዛ ግንባር ቀዳሚው ነው።
ለሀማስ አጋርነት ለማሳየት ጥቃት ከከፈተው የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ጋር የምትታኮስበት ሰሜን እስራኤል ሁለተኛ ግንባር ሲሆን ዌስትባንክ በኩል ያለው ደግሞ ሶስተኛ ግንባር ሆኗል።
1) የጋዛ ግንባር
የሀማስን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል መጠነ ሰፊ ጥቃት እያካሄደችበት ያለው የጋዛ ግንባር ነው።
ሀማስ መነሻውን ጋዛ በማድረግ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ ጥቃት በማድረሱ ምክንያት ጋዛ የእስራኤል ዋነኛ የጥቃት ኢላማ ልትሆን ችላለች።
እስራኤል 1.1 ሚሊዮን የሚሆኑ የሰሜን ጋዛ ነዋሪዎች እንዲወጡ ማስጠንቀቋን ተከትሎ ነዋሪዎች አካቢያቸውን ለቀው ወጥተዋል።
እስራኤል ጋዛ የምግብ፣ የውሃ፣ መብራት አገልግሎት እንዲቋረጥባት አድጋለች።
ያለማቋረጥ በአየር እየደበደበች ያለችው እስራኤል ጋዛን በመክበብ በእግረኛ ወደታደር ለማጥቃት ተዘጋጅታለች።
2) ሰሜን እስራኤል
የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላ ለሀማስ አጋርነት ለማሳየት በሰሜን እስራኤል በኩል ጥቃት ከፍቷል።
ሂዝቦላ ለሚያስወነጭፋቸው ሮኬቶችም እስራኤል ምላሽ እየሰጠች ትገኛለች።
የእስራኤል እና ሄዝቦላ ግጭት እየተባባሰ የመጣ ሲሆን እስራኤል በትናንትናው እለት በወሰደችው የአየር ጥቃት ስድስት የቡድኑን ታጣቂዎች መግደሏን አስታውቃለች።
ሄዝቦላህ እስራኤል በጋዛ ላይ በእግረኛ ወታደር ጥቃት የምትከፍት ከሆነ አጸፋው ይከፋባታል ሲል አስጠንቅቋል።
3) ዌስትባንክ
እስራኤል በወረራ በያዘቻት ዌስባንክ ተቃውሞ እና ግጭት ተቀስቅሷል። በጋዛ በተለይም በሆስፒታል ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በዌስባንክ ግጭት ተቀስቅሶ በርካቶች ተገድለዋል።
በራማላህ የሀማስ እና የፍልሴጤም እስላማዊ ጅሃድ ታጣቂዎች ጥቃት ለማድረስ ይሰበሰቡበት ነበር ያለችው ከመስጅድ ስር የሚገኝ ቦታን መምታቷን እስራኤል ገልጻለች። የፍልስጤም የጤና ባለሙያዎች እንደገለጹት በዚህ ጥቃት ቢያንስ አንድ ሰው ተገድሏል።
የቅርቡ የሀማስ-እስራኤል ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ እሴራኤል ዌስትባንክን በአየር ስታጠቃ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ግጭቱ እንዲቆም ጥሪዎች ቢደረግም እስራኤል አሁንም ማጥቃቷን ቀጥላለች።
የአረብ ሀገራት እስራኤል ተኩስ እንድታቆም ቢጠይቁም ከእስራኤል ጎን የቆሙት ምዕራባውያን ሀገራት ግን ስለሰብአዊ ቀውሱ ብቻ ማውራትን መርጠዋል።
አጫጭር ዜናዎችን ለማግኘት ፎሎው ያድርጉ
https://ummalife.com/MubarekNesre