muhammed HUSSEN Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Тарҷума мумкин нест.

አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “አላህ ለናንተ ሶስት ነገሮችን ይወድላችኃል፣ ሶስት ነገሮችንም ይጠላባችኃል።

*(1)እርሱን በብቸኝነት ማምለካችሁን በርሱም ላይ ማንንም/ምንንም አለማጋራታችሁን፤(2)በአላህ የማመን ገመድ አጥብቃችሁ መያያዛችሁን፤አለመለያየታችሁን፤(3)አላህ በናንተ ላይ ሐላፊነት/ስልጣን ለሰጠው አካል (በንፁህ ልብ) መምከርን፣ይወድላችኃል።

*(1)እገሌ እንዲህ አለ፣እንዲህ ተባለ በማለት ወሬ ማዋሰድን፤ (2)ገንዘብ ማባከንን፤(3)ጥያቄዎችን ማብዛትን ደግሞ ይጠላባችኃል።"

(ሙስሊም ዘግበውታል)

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Тарҷума мумкин нест.

✒️||◇

--> የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ⁉️⁉️🍁🍁

-> : የደረሰብኝን እና ለብዙ አመታት ሙስሊሙ ማህበረሰብ የተገፋበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተለያዩ የስራ እድሎች

ጉዳዩ : ቅሬታዬ እንደ አንድ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ

ነገሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው እድል እኔ እንደ አንድ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ከእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን እና ሀገርን ለማገልገል ፍላጎት ስለነበረኝ በፓይለት/አብራሪ ቦታ ላይ አመልክቼ መስፈርቶች  እና ፈተናውን በማለፍ ለቃለ መጠይቅ በቀን 16/4/2016 በአቪየሽን ዩኒቨርሲቲ ተጠርቼ የነበር እና ኢንተርቪው ሚሰጠው አንድ ቀን መሆኑ እየታወቀ እኔን ከእድሉ ለማሰናበት #ፂም ካልተላጨክ??? ኢንተርቪው መግባት አትችልም ብለው አስተባባሪ ፍላይት ኢንስትራተር ማቲያስ እና ፍላይት ኢንስትራተር እዩኤል አበበ የተባሉ እና ሌሎችም የአየር መንገድ ሠራተኞች ሁሉንም ሚጠበቅብኝን ባሟላም በፂም ምክንያት ብቻ አባረሩኝ !?!::

-> ነገር ግን ለደረሰብኝ አግባብ የለሽ የመብት ጥሰት ዝም ብዬ ከመቀበል ለሠራተኞች የቅጥር ሀላፊ አቶ ፍስሀ ጉዳዩን በመግለፅ ለተከሰተው የመብት ጥሰት መፍትሄ እንዲሰጠኝ ጠየኩኝ:: በጉዳዩ ላይ ከመከሩ በኋላ ለፈጠሩት ችግር ተወቃሽ ላለመሆን ስሜን ለይተው በመያዝ ኢንተርቪው በ2 ኛው ቀን ጠዋት 2:00 አሠራሩን በመጣስ ቀጠሩኝ:: እኔም በጠዋት 1:40 በቦታው ብገኝም እስከ 6:30 ድረስ ማንም እኔን ለማናገር ፍቃደኛ አልነበረም በዚህ ምክንያት ለሁለተኛ ግዜ ኢንተርቪው ካለፈ በኋላ አቶ ፍስሀን አገኘሁትና ከብዙ እንግልት በኋላ በሶስተኛ ጊዜ ኢንተርቪው ወሰድኩ:: ነገር ግን ቀድምውኑ ስሜ ስለተነገራቸው ፍላይት ኢንስትራተር ቢንያም እና ሁለት ባልደረቦቹ በኢንተርቪው ላይ ከሌሎቹ ተወዳዳሪዎች ሰፋ ያለ ጊዜ ቢወስድባቸውም እኔ አላህ ካለ ኢንተርቪውን እንደማልፍ አምናለሁ::

አሁንም ቢሆን ስጋት አለኝ::

-> ችግሩ ያጋጠመኝ #ሙስሊም በመሆኔ ነው:: ምክንያቱም ሀይማኖቱ በዚህ ስለሚያዝ ነው::

-> ይህ ማለት ችግሩ እኔን ብቻ ሳይሆን ብዙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከእድሉ መጠቀም ቢፈልጉም በእንዲህ አይነት ችግሮች እድል እያጡ ስለሆነ መፎትሔ እንዲበጅለት ስል በአፅእኖት መሆኑን ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል አቀርባለሁ ::

-> ለዚህም መፍትሔ ሊሆን የሚችለው በሌሎች አለም አቀፍ አየር መንገዶች (International Airlines) እንደሚደረገው ለህጉ Exceptional በማስቀመጥ ( Inclusive በማድረግ ) አየር መንገድ ውስጥ ያሉ እድሎች ሁሉንም ማህበረሰብ በእኩል ማስተናገድ እንዲችል በማድረግ ያለ ምንም አድሎ ለዚህ ችግር መፍትሔ መስጠት ይቻላል ::

image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group