AbuSelsebil Beshir Hassen Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “አላህ ለናንተ ሶስት ነገሮችን ይወድላችኃል፣ ሶስት ነገሮችንም ይጠላባችኃል።

*(1)እርሱን በብቸኝነት ማምለካችሁን በርሱም ላይ ማንንም/ምንንም አለማጋራታችሁን፤(2)በአላህ የማመን ገመድ አጥብቃችሁ መያያዛችሁን፤አለመለያየታችሁን፤(3)አላህ በናንተ ላይ ሐላፊነት/ስልጣን ለሰጠው አካል (በንፁህ ልብ) መምከርን፣ይወድላችኃል።

*(1)እገሌ እንዲህ አለ፣እንዲህ ተባለ በማለት ወሬ ማዋሰድን፤ (2)ገንዘብ ማባከንን፤(3)ጥያቄዎችን ማብዛትን ደግሞ ይጠላባችኃል።"

(ሙስሊም ዘግበውታል)

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group

🚫  ከሰጋጆች ስህተቶች

      ❨¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯❩

 

➽ ብዙ አባቶችና ወንድሞች ላይ ከሶላት ጋር የተገናኙ መስጂድ ሲገባ ጀምሮ በጀማዓም ይሁን በግል በሚሰገድበት ጊዜ የሚስተዋሉ ስህተቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ዱዓቶችና ኡስታዞችም ጭምሮ የሚሰሩዋቸው ይገኙበታል። ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ግን ትኩረት ያጡ ሆነው ይስተዋላሉ። ከእነዚህ ሶላት ውስጥ ከሚታዩና ልናስተካክላቸው ከሚገቡ ስህተቶች ውስጥ፦

❶ኛ በሶላት ውስጥ አለመረጋጋት

♻️ ይህ የሶላት ሩክን ሆኖ ሳለ ብዙዎች ጋር የሚታይ ስህተት ነው። ሩኩዕ ላይ፣ ከሩኩዕ ቀና በሚባልበት ጊዜ (ኢዕቲዳል) ላይ፣ ስጁድ ላይ፣ በስጁድ መካከል መቀመጥ ላይና የመሳሰሉ ቦታወች ላይ መረጋጋት ግዴታ ነው። ካልሆነ ሶላት ያበላሻል።

❷ኛ እንቅስቃሴ ማብዛት

↪️ ይህ ኹሹዕ ከማጣት የሚመጣ ከሶላቱ ጋር በሚገናኝ ጉዳይና ሸሪዓዊ ለሆነ ጉዳይ ካልሆነ በጣም የተጠላ ነው።

❸ኛ ኢማምን መሽቀዳደም

♻️ ኢማምን መከተል ግዴታ ሲሆን እሱን መሽቀዳደምና ቀድሞ መነሳት፣ ሩኩዕ ማድረግ፣ ከሩኩዕ ቀና ማለትና ከስጁድ መነሳት የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ሶላት ያበላሻሉ።

❹ኛ ኢማሙ የሁለተኛውን ተስሊም ሳይጨርስ ያመለጠን ለሞሙላት መነሳት

❺ኛ በንያ ድምፅ አውጥቶ መናገር

➧ ንያ ቦታው ቀልብ ስለሆነ ድምፅ አውጥቶ መናገር አያስፈልግም።

❻ኛ መስጂድ ገብቶ ኢቃም እስከሚባል ቆሞ መጠበቅ

♻️ አዛን ከተባለ በኋላ መስጂድ የገባ ሰው ወዲያውኑ ሁለት ረካዓ መስገድ ይኖርበታል። ነብዩ ﷺ በሁለት አዛኖች (በአዛንና ኢቃም መካከል ሶላት አለ) ስላሉ ቆሞ መጠበቅ አያስፈልግም። ቀብልያ ያለው ሶላት ሆነም አልሆነም ለተሒየቲል መስጂድ ለሱነተል ውዱእና ለሱናውም ይሆንለታል።

❼ኛ መስጂድ ገብቶ ኢማሙ ስጁድ ላይ ወይም ተሸሁድ ላይ ከሆነ ቆሞ መጠበቅ

➲ ይህም በጣም ስህተት ነው። ኢማሙ ባለበት ሁኔታ ተከትሎ ያመለጠውን ኢማሙ ሲጨርስ ሞሙላት ነው ያለበት።

❽ኛ በስጁድና ሩኩዕ ላይ ቁርኣን መቅራት

❾ኛ አይንን ግራና ቀኝ ወይም ወደ ሰማይ ማድረግ

↪️ ሶላት በምንስግድበት ጊዜ ወደ ስጁድ ማድረጊያ ቦታ ማየት ነው የሚያስፈልገው። ሸይጣን ሶላታችንን እንዳይሰርቀን!

❿ኛ በሁለት እግሮች ተረከዝ ላይ ቁጭ ብሎ ስጁድ ላይ ሁለት እጆችን እስከ ክርን መሬት ላይ መዘርጋት

⓫ኛ በሚሰግድ ሰው ፊት ለፊት ማለፍ (ሶላት ማቋረጥ)

⓬ኛ ኢማሙ ሩኩዕ ላይ ሆኖ ደርሶ ተክቢረተል ኢሕራም ሳያደርጉ ጎንበስ ማለት

⓭ኛ ሶላት ላይ ዐይኖችን መጨፈን

⓮ኛ በስጁድ ላይ የእግር ጣቶችን ማንሳት

⓯ኛ ስጁድ ሲያደርግ መሬቱን መሳም

⓰ኛ ሶላት ላይ ሲቆም ቀኝ እጅ በግራ ላይ አድርጎ አንገት ስር ማውጣት

⓱ ስጁድ ሲወረድና ከስጁድ ቀና ሲል ሁለት እጆችን ማንሳት

⓲ኛ በግንባር፣ በሁለት መዳፎችና፣ በሁለት ጉልበቶችና በሁለት አውራ ጣቶች (በሰባት አካላት)  ስጁድ አለመውረድ

⓳ ሴቶች ሽቶ ተቀብተው መስጂድ መምጣት

⓴ ሴቶች በሚሰግዱበት ጊዜ እግራቸውን አለመሸፈን

♻️ እነዚህ ከብዙ ስህተቶች ጥቂቶቹ ናኛቸው ራሴንና አማኞችን ለማስታወስ እነዚህን ጠቀስኩ። አላህ ተጠቃሚ ያድርገን።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Tigst hidetu bimerm wutetu tafachi nw

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Tigst bimerm wutetu tafachi nw.

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አንድም ታካሚ በሌለበት ፣ የማንም ሰው ደም በማይጎርፍበት ቦታየሚኖሩ ሐኪሞች ያሉበት ፣ አስተማሪዎች ያለጭንቀት ተማሪዎች ያለ ጩኸት የሚቆዩበት።

ሀዘን እና ስቃይ የሌለባቸው ቤተሰቦች ፣ የጀነትን ምስል የሚቀርፁ ጋዜጠኛች ፣ ዘልዓለም ስለሚቆይ ፍቅር የሚፅፉ ገጣሚዎች የሚኖሩበት ከተማ ጀነት ላይ እንገነባለን።

ጀነት ውስጥ የፅዮናውያን ወታደራዊ እገዳ የሌለባት አዲሲቷ ገዛ ትኖራለች። ብላ ቀኑን ፃፈች ለሊት ላይ በፅዮናውያን ተገድላ ሸሒድ ሆነች።

ረሒመኪላህ ያ ሒባ!!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group