Translation is not possible.

አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “አላህ ለናንተ ሶስት ነገሮችን ይወድላችኃል፣ ሶስት ነገሮችንም ይጠላባችኃል።

*(1)እርሱን በብቸኝነት ማምለካችሁን በርሱም ላይ ማንንም/ምንንም አለማጋራታችሁን፤(2)በአላህ የማመን ገመድ አጥብቃችሁ መያያዛችሁን፤አለመለያየታችሁን፤(3)አላህ በናንተ ላይ ሐላፊነት/ስልጣን ለሰጠው አካል (በንፁህ ልብ) መምከርን፣ይወድላችኃል።

*(1)እገሌ እንዲህ አለ፣እንዲህ ተባለ በማለት ወሬ ማዋሰድን፤ (2)ገንዘብ ማባከንን፤(3)ጥያቄዎችን ማብዛትን ደግሞ ይጠላባችኃል።"

(ሙስሊም ዘግበውታል)

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group