kamil seman Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

kamil seman shared a
Translation is not possible.

ዱዓአችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ምን ማድረግ አለብን?

ዱዓአችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶችስ የትኞቹ ናቸው?

ዱዓአችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በትንሹ አምስት መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅብናል::

1⃣ አል-ኢኸላስ:- ዱዓአችን በፍጹም ለአላህ ብቻ ተብሎ የሚደረገ መሆን አለበት። ከይዩልኝ እና ይስሙልኝ እንዲሁም ከማንኛውም ምድራዊ ጥቅምን ለማግኘት ከሚደረግ ጥረት የጠራ መሆን ይጠበቅበታል።

2⃣ ሙታበዓህ፡‐የመልእክተኛውን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፈለግ እና ተስተምህሮ የተከተለ መሆን አለበት።

3⃣ በአላህ ላይ በመተማመን እርሱ ምላሹን ይሰጠኛል ብሎ እርግጠኛ በመሆን ሊሆን ይገባል። ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም "ጌታችሁን እርሱ ምላሽ የሚሰጣችሁ መሆኑን በመተማማን እርግጠኛ ሆናችሁ ለምኑት" ብለዋልና።

4⃣ ዱዓእ ሲያደርጉ ዝንጉ አለመሆን፡‐ አላህን በምንለምንበት ወቅት ከመዘናጋት ርቀን በንቃት ልባችን ለአላህ የተናነሰ እና እሱን የሚከጅል ሆኖ መሆን አለበት። ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም "በዝንጉ ልቦና የሚደረግን ዱዓእን የማይቀበል መሆኑን እወቁ" ብለዋልና።

5⃣ ያለምንም ማወላወል በቁርጠኝነት አላህን መለመን ያስፈልጋል።  የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም « አንዳችሁ "አላህ ሆይ!  ከፈለክ ማረኝ"፣ "አላህ ሆይ!  ከፈለክ እዘንልኝ" ብሎ አይበል። ይልቁን አላህን ሲለምን በቁርጠኝነት ጥያቄውን ያቅርብ፤ አላህ ይፈልገውን ያደርጋል እሱን የሚያሰገድደው የለም።» ብለዋልና።

ዱዓችን ተቀባይነት እንዳይኖረው የሚያደርጉ ነገሮች የትኞቹ ናቸው?

ዱዓችን ተቀባይነት እንዳይኖረው የሚያደርጉ ነገሮች ብዙ ናቸው። ዋና ዋናዎቹን የሚከተሉት ናቸው።

⛔️ የተከለከሉ (ሀራም) ነገሮችን መብላት፣ መጠጣት፣ መልበስ እና ከሀራም በተገኘ ገንዘብ አካልን መገንባት።

⛔️ መቻኮል እና ዱዓእን መተው። ማለትም ለዱዓው በቶሎ ምላሽ ለማግኘት መቻኮል እንዲሁም ምላሽ አላገኘሁም ብሎ ዱዓን ከማድረግ መቆጠብ።

⛔️ ከዱዓው በኃላ አላህ የከለከላቸውን ነገሮች በመፈፀም የአላህ እዝነት እንዳይወርድ ሰበብ መሆን።

⛔️ አላህ ግዴታ ያደረጋቸውን ነገሮች መተው አለመፈፀም። ለምሳሌ በመልካም ከማዘዝ ከመጥፎ ከመከልከል መቆጠብ።

⛔️ በወንጀል ወይም ዝምድናን በመቁረጥ ዱዓእ ማድረግ።

✍ ጣሀ አህመድ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
kamil seman shared a
Translation is not possible.

አንድ ወጣት ስራ ለመቀጠር ፈለገ በድርጅቱ ውስጥም ትልቅ ቦታ

ለማግኘት ወደ አንድ ድርጅት አቀና ።

ወጣቱ ቃለ መጠይቁን በጥሩ ሁኔታ አለፈ ።ለመጨረሻ ቃለ

መጠይቅ ለማድረግም ከዳይሬክተሩ ጋር ተገናኘ። ዳይሬክተሩ

የመጨረሻውን መጠይቅ ካረገለት በኋላ ...

የወጣቱን የትምህርት፣ችሎታ የሚያሳየውም ሰነድ (ሲቪ)አገላብጦ

ካየ በኋላ በጣም ጥሩ መሆኑን ገለፀ።

ዳይሬክተሩ:- ከአሁን በፊት የተሻለ የትምህርት እድል አግኝተሃል

ሲል ጠየቀው ?

ልጁም:- "አይ" ሲሳ መለሰ

ትምህርትህን እንድትከታተል እና የትምህርት ቤት ክፍያዎችን

ከፍሎ ያስተማረህ አባትህ ነው?

'ወጣቱ :- አዎ.' ብሎ መለሰ።

ዳይሬክተሩ :- አባትህ ምንድነው የሚሰራው?

ወጣቱ:- አባቴ አንጥረኛ ነው"

ዳይሬክተሩ:- ወጣቱ እጆቹን እንዲያሳየው ጠየቀው።

ወጣቱ :- ለስላሳ እና ፍጹም የሆነ እጆቹን አሳየው

ዳይሬክተሩ:- ወላጅ አባትህን በሥራ ረድተሃቸው ታውቃለህ?

ወጣቱ:- በጭራሽ፣ ወላጅ አባቴ መጻሕፍቶችን እንዳነብና

እንዳጠና ነበር ፍላጎቱ ። እና ደግሞ ከኔ በተሻለ ሁኔታ ስራውን

መስራት ይችላል።

ዳይሬክተሩ እንዲህ አለ፡-

ለዛሬ ወደ ቤትህ ትመለሳለህ እቤት እንደደረስክም የአባትህን እጅ

በደንብ አርገህ ታጥብና ነገ ጥዋት ተመልሰህ አግኘኝ ብሎ ቀጠሮ

ያዘለት ።

ወጣቱ ስራውን የማግኘት እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ተሰማው።

ወደ ቤቱ እንደተመለሰም የአባቱን እጅ እንዲያጥብለት አባቱን

ፍቃድ ጠየቀው?

አባቱ በልጁ እንግዳ ተግባር ተገረመ ደስም አለው , ነገር ግን

የደስታ ስሜቱ የተደባለቀ ነበር።

ከዚያም እጆቹን ለልጁ አሳየው. ወጣቱ ቀስ እያለየአባቱን እጆች

አጠበ። ይህን ጊዜ የአባቱ እጆች የተሰነጣጠቁ እና በጣም ብዙ

ጠባሳ እንዳለባቸው አየ ። ይህን ያስተዋለው ለመጀመሪያ ጊዜ

ነበር።

በአባቱ እጆች ላይ አንዳንድ ቁስሎቹ ነበሩ ፣እነዚህ ቁስሎች

በጣም ያሙት ስለነበር ቆዳውን ሲነካቸው ያመው ነበር ።

ወጣቱ እነዚህ እጆች የእርሱ ትምህርት ገንዘብ ለመክፈል በየቀኑ

መሥራት ምን ማለት እንደሆነ ሲያውቅም ይህ የመጀመሪያው

ነው።

የአባቱ እጆች ላይ ያሉት እብጠቶች አባቱ ለእርሱ ትምህርት

መሰረታዊ፣ ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ለወደፊት ህይወቱ

የከፈለው ዋጋ ነው!!!

ወጣቱ የአባቱን እጅ ካጸዳ በኋላ ለጠቂት ያክል በዝምታ ቆመ

።ከዚያም የአባቱን የስራ መስሪያ ቁሳቁሶች ማፅዳት ጀመረ። በዚያ

ምሽት ላይ አባትና ልጅ ለረጅም ሰዓታት ተነጋገሩ፣ አብዛኛውን

የምሽቱን ክፍለ ጊዜ በጨዋታ እና በውግ አሳለፉ ።

በማግስቱ ጠዋት ወጣቱ ወደ ዳይሬክተሩ ቢሮ ሄደ።

ዳይሬክተሩ የወጣቱ አይን እንባ ሲያቀር አስተዋለ ።

ዳይሬክተሩ:- ትናንት ቤትህ ውስጥ ያደረግከውን ሁሉ ልትነግረኝ

ትችላለህ?

ልጁም 'የአባቴን እጅ አጥቤ ስጨርስ የአባቴን የስራ መገልገያ

( አውደ ጥበቡን )አጸዳሁ' ሲል መለሰ።

ዳይሬክተሩ :- ከዚህ ምን ተማርክ ?

ወጣቱ :- ወላጆቼ ባይኖሩ ኖሮ ዛሬ ላይ እኔ

[እኔ እንደማልሆን] ተረዳሁ ።በዚህም አባቴን በመርዳት አንድ ነገር

በራሴ ማድረግ ምን ያህል ከባድ እና ከባድ እንደሆነ አሁን

ተገነዘብኩ። ቤተሰቤን የመርዳትን አስፈላጊነት እና ጥቅም

ተገነዘብኩ አለ ።

ዳይሬክተሩም "በድርጅቴ የምቀጥረው እና በድርጅቴ ውስጥ

እንዲኖር የምፈልገው ይህንን ነው,።እርሱ የሌሎችን እርዳታ

የሚያደንቅ፣በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ለእኛ ሲሉ ብቻ የእነሱ ያልሆኑ

ሌሎች ነገሮችን ለማከናወን ሲሉ የሚደርስባቸውን ችግር እና

ስቃይ የሚያውቅ ሰው መቅጠር እፈልጋለሁ አለ ።

ሁላችንም የራሳችንን ሸክም መሸከም ስንጀምር ለወላጆቻችን

ልፋት ዋጋ መስጠት እንጀምራለን

ወላጆች በእንተ ዘንድ ሆነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅና

ላይ በደረሱ ጊዜ (ኡፍ) አትበላቸው፤ አትገላምጣቸውም።

መልካምን ቃል ተናገራቸው። ከትህትና የመነጨ የእዝነት እና

የርህራሄ ክንፍህን ዝቅ አድርግላቸው። እናም «ጌታዬ ሆይ!

በሕፃንነቴ በርህራሄ እንዳሳደጉኝ ሁሉ ምህረትህን ስጣቸው» በል

ቁርኣን ( 17 : 23 - 24 )

ወላጆችን ሁለቱንም ውደዱ። "ለእናንተ ጉልበታቸውን አጥተዋል::

አላህ ሆይ የሁለተንም ወላጆች ሀቅ የምንጠብቅ አድርገን

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
kamil seman shared a
Translation is not possible.

ማዛጋት መንፈሳዊ ትርጉሙን ብታውቁት ኖሮ ማዛጋታቹን ታፍሩበት

ነበር ።

የማዛጋት ትርጉም በፊዚዮሎጂ....

ማዛጋት በሁሉም የጀርባ አጥንቶች ውስጥ የተለመደ እና አየር

ወደ ውስጥ የመማግ እና መተንፈስ እእንዲሁም የጡንቻዎችን

መወጠርን የሚያካትት የፊዚዮሎጂ እንቅስቃሴ ነው።

ማዛጋት የኛ የአጸፋዊ ስርዓታችን አካል ነው፣ እሱም በዋነኝነት

የሚቀሰቀሰው ያለፍላጎቱ በውጫዊ ተነሳሽነት ነው።

ለምን እንደምናዛጋ በፊዚዮሎጂ ብዙ ማብራሪያዎች አሉ፣ በጣም

የታወቀው ደግሞ በሳንባችን ውስጥ ያለው ዝቅተኛ የኦክስጂን

መጠን ነው።

ማዛጋት የሚጀምረው በማህፀን ውስጥ ነው, ነገር ግን በዋነኛነት

በአዋቂዎች ላይ ይታያል ። በልጆች ላይ የእንቅልፍ ጊዜ ወይም

አሰልቺ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ያነሰ ነው።

ይሁን እንጂ ማዛጋት ብዙውን ጊዜ እንደ ጸሎት ወይም ማሰላሰል

ባሉ በጣም አስፈላጊ ተግባራት ውስጥ ሊከሰት ይችላል።

ታዲያ በጸሎት ጊዜ ማዛጋት መንፈሳዊ ትርጉሙ ምንድን ነው?

በጸሎት ጊዜ ማዛጋት ያለውን ድብቅ መንፈሳዊ ትርጉም፣ ምን

እንደሚያመለክተው እና በሱ ልታፍሩበት እንደሚገባ በጥቂቱ ።

ስለ ማዛጋት ተምሳሌታዊ ትርጉሞች የበለጠ ለማወቅ ቀጣዩን

ፅሁፍ ያንብቡ

ማዛጋት መንፈሳዊ ትርጉም በእስልምና

በጸሎት ጊዜ ማዛጋት በእስልምና አብዛኛውን ጊዜ አማኞች

በሚጸልዩበት ወቅት ስለ ማዛጋት ብዙ ባህላዊ እምነቶች አሉ።

በጣም የተለመደው የሰይጣን ፈተና ነው።

በጸሎት ጊዜ ማዛጋት ሰይጣን ወደ ሰውነትህ ለመግባት

የሚሞክርበት መንገድ ነው።

እንደ ነቢዩ (ሰ.ዐ. ወ)ገለጻ፣ ሰይጣን የአማኞችን ትኩረት

አቅጣጫ ለማስቀየር እና እነሱን ለማዋረድ የሚሞክርበት

መንገድ ነው።

አማኞች ሲያዛጉ ሰይጣን በጣም ይደሰታል። ይህንንም የሚያሳካው

ሃሳባቸውን በመውረር እና ትኩረታቸውን እንደ ማዛጋት ባሉ

ፈተናዎች በማወክ ነው።

በተጨማሪም ወንዶች ሲያዛጉ የሚያሳዩዋቸው የፊት ገጽታዎች

በተለይ ለእሱ አስደሳች ሆኖ አግኝተውታል ታማኝ ሙስሊም

ከሰይጣን ፈተናዎች መራቅና ትጋቱን መጠበቅ አለበት።

ስታዛጋ ሰይጣን በአንተ ላይ ይስቃል፡- አንድ ሰው ሲያዛጋና አፉን

ሲከፍት የሚያሳየው የፊት ገፅታ ለሰይጣን የሳቅ ምንጭ ነው።

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል

አማኞች ሲያዛጉ በተቻለ መጠን ለረጅም ጊዜ ማዛጋቱን

በውስጣቸው መያዝ አለባቸው።

ሊቋቋሙት የማይችሉት ከሆነ ወዲያውኑ አፋቸውን በእጃቸው

ወይም በልብስ መሸፈን አለባቸው ይህ ምልክት የሚደረገው

ሰይጣን ወደ ሰውነት እንዳይገባ በመፍራት ነው።

እስልምና የመጨረሻው ሰላም ሀዲስ አንድ ሰው ከሞተ በኋላ

ሶስት ነገሮች አብረውት ይሄዳሉ

የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

የአደም ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል!! ከሶስት ነገሮች በስተቀር፡

1,ኛ ሰደቃ

2,ኛ እውቀቱ

3,ኛ ዱአው (ፀሎቱ )

ሰደቃ ጥቅሟ ቀጣይነት አለው

ዱአ እና እውቀት ከርሱ ጥቅማጥቅም የሚሰበሰብበት ነው

(ለምሳሌ ለሰዎች መልካም ነገር ብታስተምር ) ላንተ የፅድቅ

መንገድ ነው።

እነዚህ ሶስት ነገሮ ቀጣይነት ያላቸው እና ጥቅማቸው በአላህ

ዘንድ የሚታጨድበት ሲሆን ።ከሞት በኋላ የሚጠቅሙህ

ምንዳዎችን ይልኩልሃል

ረሱል (ሶ.ዐ.ወ) እውቀትን ከኔ ለሌላው አስተላልፉ አንድም

አረፍተ ነገር ብትሆን እንኩዋን ብለዋል።

እኔ ነቢያዊ መልእክቱን ለናንተ አድርሻለው

ይህንን ፅሁፍ ለወዳጅ ዘመዶዎ ይደርስ ዘንድ ሼር ያድርጉ

አላህ ሆይ በነዚህ ሶስት ነገሮች የምንጠቀም አድርገን

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group