UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ነቢዩን ﷺ በህልማችን ካየናቸው እነሱ መሆናቸውን በምን ማረጋገጥ እንችላለን?

ነቢዩ ﷺ «በህልሙ ያየኝ የእውነት አይቶኛል። ሸይጧን በእኔ መመሰል አይችልምና።» ብለዋል።

(ቡኻሪይ 6994 / ሙስሊም 2268)

በዚህም ዑለማዎች ሸይጧን በሶሂህ ሐዲሶች በተገለፀው የነቢዩ ﷺ ትክክለኛ መልክ ተመስሎ በህልም መምጣት እንደማይችል ተስማምተውበታል። ይህም ሸይጧን በነቢዩ ﷺ ተመስሎ እየመጣ ሰዎችን እንዳያሳስት አላህ የዋለልን ፀጋ ነው።

ነገርግን አንዳንዴ ሸይጧን ሽማግሌ፣ ሽበታቸው የበዛና መልከመልካም አይነት ሰው ተመስሎ በመምጣት ነቢዩ ﷺ ነኝ በማለት ለማታለል ሊሞክር ይችላል።

♦️ ይህ ሲሆን ሰውየው ህልሙ ከአላህ ይሁን ከሸይጧን ማረጋገጫ የሚችለው በህልሙ ያያቸውን ሰው በሶሂህ ሐዲሶች ከተገለፀው ከነቢዩ ﷺ ትክክለኛ መልክ ጋር በማመሳከር ነው።

ኢብን ሲሪን ስለዚሁ ሲናገሩ «በህልሙ ያየኝ የእውነት አይቶኛል ማለት በእውነተኛ መልካቸው አይቷቸው ከሆነ ማለት ነው።» ብለዋል።

(ቡኻሪይ 6993)

ኢብን ሐጀር እንደዘገቡት ሰዎች ወደ ኢብን ዐባስ በመሄድ ነቢዩን ﷺ በህልማቸው እንዳዩ ሲነግሯቸው «መልካቸው ምን ይመስላል?» በማለት ይጠይቃቸው ነበር። ለአብነት ዐሲም ኢብን ኩላቢ ሲናገሩ «አባቴ ወደ ዐብዱላህ ኢብን ዐባስ ሄደና በህልሙ ነቢዩን እንዳያቸው ነገረው። ኢብን ዐባስም «መልካቸው ምን ይመስላል?» በማለት ጠየቀው። አባቴም «ሐሰን ኢብን ዐሊይን ይመስላሉ» አለው። ኢብን ዐባስም «በትክክል አይተሃቸዋል።» አለው።» ብለዋል።

(ፈትህ አል-ባሪ 12/383)

በተመሳሳይ የዚድ ኢብን አል-ፋሪሲ ሲናገር እንዲህ አለ «ነቢዩን በህልሜ አየኋቸውና ለኢብን ዐባስ ነገርኩት። እሱም «ያየኸው ሰው ምን እንደሚመስል ልትነግረኝ ትችላለህ?» አለኝ። እኔም ያየሁትን ገለፅኩለት። እሱም «ነቢዩን መንገድ ላይ ብታያቸው እንኳን ከዚህ በላይ ልትገልፃቸው አትችልም።» በማለት እነሱ መሆናቸውን አረጋገጠልኝ።»

(አሽ-ሸማኢል 412)

እንዲሁ ኢብን ሲሪንም አንድ ሰው ነቢዩን ﷺ በህልሙ እንዳያቸው ከነገራቸው «መልካቸው ምን ይመስላል?» በማለት ይጠይቁታል። ሰውየውም የነቢዩ ﷺ ያልሆነ ሌላ መልክ ከነገራቸው «አላየሃቸውም» ይሉት ነበር።

(ፈትህ አል-ባሪ 12/384)

♦️ ነቢዩን ﷺ በትክክለኛ መልካቸው ማየት አለበት ሲባል ታዲያ በተለያየ የዕድሜ ደረጃ ሆነው ሊሆን ይችላል። ኢብን ሐጀር ስለዚሁ ሲናገሩ፡-

«በወጣትነት ወይም በትልቅነት ዘመናቸው በነበራቸው መልክ ሊያያቸው ይችላል። ነገርግን በትክክል እነሱ በወቅቱ ከነበራቸው መልክ ጋር አንድ መሆን አለበት። ምሳሌ ሊሞቱ አቅራቢያ በነበራቸው መልክ ካያቸው የሽበት ፀጉራቸው ብዛት ከ20 እንደማይበልጥ ማረጋገጥ አለበት።» ብለዋል።

(ፈትህ አል-ባሪ 12/386)

(ነቢዩ ﷺ መልካቸው ምን ይመስላል? የሚል ጥያቄ ያለው ካለ ይሄንን አለማወቅ ተገቢ ስላልሆነ ዛሬውኑ ዑለማዎችን መጠየቅ አለበት)

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ዕድሜ በዱዓዕ ሊጨምር ይችላል?

ዕድሜ አላህ ቀድሞ ከቀደራቸው ነገሮች አንዱ ሲሆን፦

«ዕድሜው ከሚረዘምም አንድም አይረዘምም ከዕድሜውም አይጎደልም በመጽሐፉ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጂ።» ብሏል።

(ፋጢር 11)

ሆኖም አንድ ሰው ዕድሜው እንዲረዝምለት ዱዓዕ ማድረግ ይችላል። ነቢዩ (ﷺ) ስለዚሁ ሲናገሩ፦

«ሪዝቁ እንዲጨምርና ዕድሜው እንዲረዝም የፈለገ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።» ብለዋል።

(ቡኻሪይ 2067/ ሙስሊም 2527)

♦️ አላህ ዕድሜውን ቀድሞ ከወሰነው በኋላ እንዴት ሊረዝምለት ይችላል? ለሚለው ጥያቄ፦

ኢብን ተይሚያህ ሲያብራሩ «አላህ መለዒካዎችን ዕድሜውን እንዲፅፉ ያዛቸዋል። ከዚያም “ዝምድናውን ከቀጠለ በዚህ ያህል ዕድሜ አረዝምለታለሁ” ይላቸዋል። መለዒካዎቹ ወደፊት ዕድሜው ይጨምር አይጨምር አያውቁም። አላህ ግን ያውቃል። ከዚያም አላህ በወሰነው ጊዜ ሞቱ ይመጣበታል። ብለዋል።

(መጅሙዕ አል-ፈታዋ 8/517)

♦️ ኢማም ነወዊይ ደግሞ ዕድሜ ስለሚጨምርበት መንገዶች ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል፦

«ዕድሜ በሶስት መንገዶች ሊጨምር ይችላል።

❶ አላህ ዕድሜውን በረካ ወይም መልካም የሚሰራበት ሊያደርግለት ይችላል።

❷ አላህ በዕድሜው ላይ ተጨማሪ ዕድሜ ሊሰጠው ይችላል። ምሳሌ 60 የነበረውን 100 ሊያደርገው ይችላል።

➌ ሰውዬው ከሞተ በኋላ የሚቀጥል መልካም ስራ ሊሰጠው ይችላል።

አላህ የበለጠ ያውቃል!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ረዲቱ ቢላሂ ረበን፣

ወቢል_ኢስላሚ ዲነን፣

ወቢሙሐመዲን ሠለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ነቢየን ረሱለን!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ያሰብከው እንዲሳካ…

የሆነ ነገር አሳስቦህ ጭንቅ ጥብብ ብሎህ አላህን የትና እንዴት ልማፀነው ብለህ ታውቃለህ ?

ይሀው መልሱ :–

የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ: ( የአላህ ባርያ ለጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ነው እዚህ ላይ ዱዓ አብዙ ።)ሙስሊም ዘግበውታል

በሌላ ዘገባ (ሊቀበላችሁ እርግጥ ነው ) ይላሉ ።

በል ተነስ/ሺ ወዱእ አድርገህ ሰላት ስገድ ሱጁድ ላይ ሃጃህን በሙሉ ስቅስቅ ብለህ ለአላህ አቅርብ ኢንሻአላህ ይሳካል ።

በዱዓህ እንዚህን ባትረሳ ጥሩ ነው ።

– ያ አላህ ወንጀላችንን ማረን

– ያ አላህ ያአንተ ብቻ ባርያ አድርገን

– ያ አላህ ከሽርክ ፣ከኩፍር፣ ከኒፋቅና ከቢድዓ ጠብቀን

– ያ አላህ ከሀሜት ከምቀኝነት ከተሳዳቢነት ከብልሹ ስነምግባር ጠብቀን

– ያ አላህ በተውሂድና በሱና(لا إله إلا الله محمد رسول الله) መሰረት አንድነታችንን ጠብቅልን

– ያ አላህ በአዱንያም መልካምን በአኼራም መልካምን ስጠን።

– ያ አላህ… …

عن أبي هريرة - رضي الله عنه - قال: قال رسول الله - صلى الله عليه وسلم -: ((أقرب ما يكون العبد من ربه وهو ساجد؛ فأكثروا الدعاء))؛ رواه مسلم.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ፀጋችንና መከራችን ቢወዳደሩ

አላህ በቁርኣኑ «ፀጋዬን ብትቆጥሩ አትዘልቋትም።» ብሎናል።

እኛ ሰዎች ደግሞ ደካሞች ነንና አላህ ከዋለልን ፀጋ ይልቅ መከራችን የበዛ ይመስለናል። ነገርግን በተጨባጭ የአላህ ፀጋ ከሚገጥመን መከራ በላጭ ብቻ ሳይሆን ሊወዳደርም አይችልም። ለምሳሌ፦

♦️ የታመማችሁበትንና በጤና የኖራችሁበትንም ቀናት ቁጠሩ። የታመምንባቸው ቀናት ቢቆጠሩ አንድ ዓመት ቢሞሉ ነው። ብዙ ዓመታትን ግን አላህ በጤና አኑሮናል።

♦️ የተራባችሁበትንና የበላችሁበትንም ቀናት ቁጠሩ። የተራብንባቸው ቀናት ቢደመሩ አንድ ዓመት ቢሞሉ ነው። ብዙ ዓመታትን ግን አላህ መግቦናል።

♦️ የታረዛችሁበትንና የለበሳችሁበትን ቀናት ቁጠሩ። ልብስ ያጣንባቸው ቀናት ቢደመሩ አንድ ዓመትም አይሞሉም። ብዙ ዓመታትን ግን አላህ አልብሶናል።

♦️ የተጨነቃችሁበትንና ሰላም የሆናችሁበትን ቀናት ቁጠሩ። የተጨነቅንባቸው ቀናት ቢደመሩ አንድ ዓመት ቢሆኑ ነው። ብዙ ዓመታትን ግን አላህ በሰላም አኑሮናል።

🔷 የትኛውም መከራ ቁጠሩ። አላህ ከሰጣችሁ ፀጋ ጋር በፍፁም ሊወዳደር አይችልም። የአላህን ፀጋ እኛ ጨርሰን ባናውቀውም ነገርግን ቆጥረን የምንጨርሰው አይደለም። የገጠመው መከራ ግን ተቆጥሮ ያልቃል። እናም መከራችን እንደበዛ አድርገን አናስብ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group