ዱዓአችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ምን ማድረግ አለብን?
ዱዓአችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶችስ የትኞቹ ናቸው?
ዱዓአችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በትንሹ አምስት መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅብናል::
1⃣ አል-ኢኸላስ:- ዱዓአችን በፍጹም ለአላህ ብቻ ተብሎ የሚደረገ መሆን አለበት። ከይዩልኝ እና ይስሙልኝ እንዲሁም ከማንኛውም ምድራዊ ጥቅምን ለማግኘት ከሚደረግ ጥረት የጠራ መሆን ይጠበቅበታል።
2⃣ ሙታበዓህ፡‐የመልእክተኛውን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፈለግ እና ተስተምህሮ የተከተለ መሆን አለበት።
3⃣ በአላህ ላይ በመተማመን እርሱ ምላሹን ይሰጠኛል ብሎ እርግጠኛ በመሆን ሊሆን ይገባል። ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም "ጌታችሁን እርሱ ምላሽ የሚሰጣችሁ መሆኑን በመተማማን እርግጠኛ ሆናችሁ ለምኑት" ብለዋልና።
4⃣ ዱዓእ ሲያደርጉ ዝንጉ አለመሆን፡‐ አላህን በምንለምንበት ወቅት ከመዘናጋት ርቀን በንቃት ልባችን ለአላህ የተናነሰ እና እሱን የሚከጅል ሆኖ መሆን አለበት። ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም "በዝንጉ ልቦና የሚደረግን ዱዓእን የማይቀበል መሆኑን እወቁ" ብለዋልና።
5⃣ ያለምንም ማወላወል በቁርጠኝነት አላህን መለመን ያስፈልጋል። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም « አንዳችሁ "አላህ ሆይ! ከፈለክ ማረኝ"፣ "አላህ ሆይ! ከፈለክ እዘንልኝ" ብሎ አይበል። ይልቁን አላህን ሲለምን በቁርጠኝነት ጥያቄውን ያቅርብ፤ አላህ ይፈልገውን ያደርጋል እሱን የሚያሰገድደው የለም።» ብለዋልና።
ዱዓችን ተቀባይነት እንዳይኖረው የሚያደርጉ ነገሮች የትኞቹ ናቸው?
ዱዓችን ተቀባይነት እንዳይኖረው የሚያደርጉ ነገሮች ብዙ ናቸው። ዋና ዋናዎቹን የሚከተሉት ናቸው።
⛔️ የተከለከሉ (ሀራም) ነገሮችን መብላት፣ መጠጣት፣ መልበስ እና ከሀራም በተገኘ ገንዘብ አካልን መገንባት።
⛔️ መቻኮል እና ዱዓእን መተው። ማለትም ለዱዓው በቶሎ ምላሽ ለማግኘት መቻኮል እንዲሁም ምላሽ አላገኘሁም ብሎ ዱዓን ከማድረግ መቆጠብ።
⛔️ ከዱዓው በኃላ አላህ የከለከላቸውን ነገሮች በመፈፀም የአላህ እዝነት እንዳይወርድ ሰበብ መሆን።
⛔️ አላህ ግዴታ ያደረጋቸውን ነገሮች መተው አለመፈፀም። ለምሳሌ በመልካም ከማዘዝ ከመጥፎ ከመከልከል መቆጠብ።
⛔️ በወንጀል ወይም ዝምድናን በመቁረጥ ዱዓእ ማድረግ።
✍ ጣሀ አህመድ