UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ያደርገኛል።

ሐጃጅ፦ ይቅር ልበልህ? ልተውህ??

ሰዒድ፦ ይቅር ከተባልኩ ይቅርታው ከአላህ ነው። አንተ ይቅር አልክ አላልክ ዋጋ የለውም።

ሐጃጅ (ለግድያ ፈጻሚዎቹ)፦ "ይህን ሰው ግደሉት!" ብሎ አዘዘ።

ሰዒድም ወደሚገደልበት ቦታ እየተወሰደ ሳለ ልጁ በዚህ ቦታ ስላየው ያለቅስ ጀመር። ሰዒድም ልጁን ሲመለከተው "ምንድን ነው የሚያስለቅስህ?" አለው።

ልጁም "ከ57 አመት በኋላ አባትህ ምን ቀረው?" አል።

ሰዒድ አንድ ወዳጁንም ሲያለቅስ ተመለከተው።

"ምንድን ነው የሚያስለቅስህ?" ሲልም ጠየቀው።

ግለሰቡም "ባገኘህ ነገር!" ሲል መለሰ።

ሰዒድም "አታልቅስ!፤ ይህ እንደሚሆን በአላህ እውቀት ዘንድ ነበር!" አለውና ይህን የቁርኣን አንቀጽ አነበበ፦

{ما أصاب من مصيبة في الأرض ولا في أنفسكم إلا في كتاب من قبل أن نبرأها}

"በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትሆን እንጅ፤ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው። "

[አል-ሐዲድ: 22]

ሰዒድ ሊገደል ሲል ሳቀ። ገዳዎቹም ተገረሙና ለሐጃጅ ነገሩት። ሐጃጅም ወደርሱ እንዲያመጡት ነገራቸው።

ሰዒድ ዳግመኛ ወደ ሐጃጅ ዘንድ ሲመጣ፤ ሐጃጅ "ምንድን ነው ያሳቀህ?" አለው።

ሰዒድ፦ "አንተ ለአላህ እንዲህ አይነት አመለኛ ሁነህ ሳለ፤ እርሱ ባንተ ላይ ያለው ትዕግስትና እዝነት ገርሞኝ ነው!" አለው።

ሐጃጅ (ለገዳዮቹ)፦ "ፊት ለፊቴ ግደሉት!" አላቸው።

ሰዒድ፦ "መጀመሪያ ሁለት ረከዓ ሶላት እንድሰግድ ፍቀዱልኝ?" አላቸው። ፈቀዱለት። ቂብላውን ተቅጣጭቶ እየሰገደ ሳለ ይህን የቁርኣን አንቀጽ አነበበ፦

{وجهت وجهي للذي فطر السموات والأرض حنيفًا وما أنا من المشركين}

"«እኔ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው (አምላክ) ቀጥተኛ ስኾን ፊቴን አዞርኩ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም»፡፡ "

[አል-አንዓም: 79]

የዚህን ጊዜ ሐጃጅ፦ "ፊቱን ከቂብላው አዙሩና ወደ ክርስቲያኖች ቂብላ አዙሩት!" አለ።

እነርሱም አዞሩት።

ሰዒድም የዚህን ጊዜ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ አነበበ፦

{فأينما تولوا فثم وجه الله}

"ምሥራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው (ፊቶቻችሁን) ወደ የትም ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ነው፡፡ "

[አል-በቀራህ: 115]

ሐጃጅ አሁንም "ፊቱን ወደ መሬት ድፉት!" አለ።

ሰዒድም የዚህን ጊዜ ይህን አንቀጽ አነበበ፦

(مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَى!)

"ከርሷ (ከምድር) ፈጠርናቸሁ፤ በርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፤ ከርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን።"

[ጦሃ: 55]

ሐጃጅም "እረዱት!" አላቸው።

ሰዒድ እንዲህ አለ፥ "أما أنا فأشهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له وأن محمدًا عبده ورسوله، خذها مني يا حجاج حتى تلقاني بها يوم القيامة"

"ከአላህ ውጭ በሐቅ የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፣ ለርሱ ቢጤም አጋርም የለውም። ሙሐመድም የርሱ ባሪያውና መልዕክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ!" አለና፥ "ሐጃጅ ሆይ! ይህቺን ቃል ከኔ ያዛት፤ በርሷ ኋላ የውመል ቂያማ አላህ ፊት እንገናኛለን!" አለው።

እንዲህም ብሎ ዱዓ አደረገ፦ (اللهم لا تسلطه على أحد يقتله بعدي)

"አላህ ሆይ! ከኔ በኋላ ማንንም እንዲገድል አቅሙን አትስጠው።"

ሰዒድም በሃምሳ ዘጠኝ አመቱ በወርሃ ረመዳን 11, 95 ዓ.ሂ (714 G.C) ምላሱ በዚክር እንደረጠበች ታረደ።

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን‼

እኛ የአላህ ነን፤ ወደርሱም ተመላሾች ነን‼

የሚገርመው ነገር፤ ሐጃጅ ሰዒድን ከገደለ በኋላ ከሃምሳ ወይም ከአርባ ቀናት በላይ በህይወት አልቆዬም። እነዚህንም የቆዬው በከባድ የህመም ስቃይ ውስጥ ሁኖ ነበር።

ሐጃጅ በከፋ ህመም ውስጥ ገባ። "በኔና በሰዒድ ኢብኑ ጁበይር መካከል ያለው ምን ነበር? በጠና ታምሜ መተኛት ስፈልግ፤ ልተኛ ስል እግሬን እየነካካ አላስተኛኝ ይላል!" ይል ነበር።

(ሱብሐነል'ሏህ!!)

አንዳንድ ዘገባዎች ላይ እንደሰፈረው፤

ሐጃጅ በጠና ታሞ ተኝቶ ሳለ በህልሙ ሁልጊዜ ሰዒድ ኢብኑ ጁበይርን ይመለከታል፣ አይኑ ላይ ግርጥ ይልበታል። ሰዒድ ሐጃጅን በልብሱ ይይዘውና "አንተ የአላህ ጠላት ሆይ ምን አድርጌህ ነበር የገደልከኝ?" ይለዋል። ሲነጋና ሐጃጅ ከእንቅልፉ ሲነቃ፤

(ما لي ولسعيد بن جبير كلما أردت النوم أخذ برجلي!!)

"በኔና በሰዒድ ኢብኑ ጁበይር መካከል ያለው ምንድን ነው?፣ በኔና በሰዒድ ኢብኑ ጁበይር መካከል ያለው ምንድን ነው?" በማለት በተደጋጋሚ በትካዜ ተውጦ ይለፍፋል። (ያ ሰላም!!)

የሚደንቀው ነገር ሐጃጅ አሁንም ከእንቅልፉ ሲነቃ፤

"አላህ በአንተ ላይ ምን ሰራ?" ሲባል፤

"በእያንዳንዱ በገደልኩት ሁሉ አንዳንድ ጊዜ ገደለኝ። በሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ግን ሰባ ጊዜ ገደለኝ!" ይላል። (ኢናሊላሂ!)

እንዲህ የሚል ሰፍሯል። አል-ሐጃጅ ሊሞት አቅራቢያ ጥቂት ቀናቶች ሲቀሩት ሰውነቱ ሙሉ ፓራላይዝድ ሆነ። በሚቃጠል እሳት ላይ እጁ ሲደረግ፤ ቆዳው እየነደደ ግን አይሰማውም። ህመሙም በጣም ጠና። ከሰውነቱ ውስጥ ትል ይወጣና ይገባ ጀመር። (አላህ ይጠብቀን።)

*

ሐጃጅ ህመሙ በጣም ሲጠናበት ወደ ሐሰነል በስሪ ዘንድ "ኑልኝ!" ብሎ ሰው ላከ።

ሐሰነል በስሪም እንዲህ አሉት፥ "አልነገርኩህንም ነበር?! የምሁራንን መንገድ አልተከተልክም!፤ ሰዒድን እኮ ገድለሃል!!"

ሐጃጅም "እዚህ የጠራሁህ እኮ እንድታድነኝ አሊያም መድሀኒት እንድትፈልግልኝ አይደለም።

ይልቁንም ከምታዬው ስቃይ አላህ ቶሎ ገድሎ እንዲያሳርፈኝ ለምንልኝ፣ ዱዓ አድርግልኝ ብዬ ነው!" አላቸው።

ወዳው ብዙም ሳይቆይ ሞተ።

ኢማሙ አሕመድ እንዲህ ይላሉ፦ "ሰዒድ በተገደለ ጊዜ፤

የርሱን እውቀት የማይፈልግ በአለም ላይ አንድም ሰው አልነበረም።"

ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ትልቅ ሰው ነበር።

ገና በልጅነቱ ጀምሮ እውቀትን ቀስሟል።

ከአስር በላይ የነብዩ ሶለል'ሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሐቦች ላይ ተምሯል።

ብዙ ሐዲሥም አስተላልፏል። ከአነስ ኢብኑ ማሊክ፣ ከዾሐክ ኢብኑ ቀይስ፣ ከዐብደልሏህ ኢብኑ ዙበይር፣ ከኢብኑ ዐባስ፣ ከኢብኑ ዑመርና ከሌሎችም ተራራ ተራራ ከሚያክሉ ሶሐቦች አስተላልፏል።

ታላቁን የሐዲሥ ዘጋቢ አቢ ሁረይራን፣ የሙእሚኖችን እናት ዓኢሻን፣ አቡ ሙሳ አል-አሽዓሪይንና ሌሎች የነቢዩ ባልደረቦችንም በአይኑ አይቷል፤ ከነርሱም ብዙ እውቀትንና ሐዲሥን ገብይቷል።

ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ከነዚህ ሁሉ ሶሐቦች ሐብሩል ኡማህ የተሰኘውን ታላቁን የቁርኣን ተንታኝ፤ በአሽረፈል ኸልቅ አንደበት "አላህ ሆይ ተፍሲርን አሳውቀው!" ተብሎ የተነገረለትን ታላቅ ሶሐባ ዐብደል'ሏህ ኢብኑ ዐብ-ባስን ቋሚ አስተማሪው አድርጎ ያዘ። ከርሱም ተፍሲርንና ሌሎች እውቀቶችን ቀስሟል።

ከስነ ስርአቱ የተነሳ፤ ሰዒድ አስተማሪው ኢብኑ ዐብ-ባስ እያለ ፈታዋ አይሰጥም ነበር። ግን ስለሚፈቅድለት እዚያው እያለ ፈታዋ ይሰጣል።

ኢብኑ ዐብ-ባስ የዒራቅ ሰዎችን እውቀት ከሰዒድ ኢብኑ ጁበይር እንዲሸምቱ ይነግራቸው ነበር።

||

✔️ በአንድ ወቅት አንድ የኩፋ ሰው ወደ ኢብኑ ዐብ-ባስ ዘንድ መጣና ፈታዋ ጠየቃቸው።

ኢብኑ ዐባስ ለዚህ ለጠያቂ እንዲህ አሉት፦

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

(أليس فيكم ابن أم الدهماء؟! يقصد سعيد بن جبير.)

"በመካከላችሁ ኢብኑ ኡሚ ደህማእ የለም እንደ?!"

(ኢብኑ ኡሚ ደህማእ ማለት ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ነው።) እንግዲህ አስቡት ምን ያክል ታላቅ ሰው እንደነበር!!

✔️ ወደ ታላቁ ሶሐባ ዐብደል'ሏህ ኢብኑ ዑመር ዘንድ አንድ ሰው መጣና ስለ ውርስ ጠየቃቸው። እርሳቸውም "ወደ ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ዘንድ ሂድ!፤ እርሱ ከኔ ይበልጥ በሒሳብ ረገድ አዋቂ ነው!" አሉት።

✔️ ኢብራሂም አን-ነኸዒይ እንዲህ ይላሉ፦ "ከሰዒድ ኢብኑ ጁበይር በኋላ የርሱ አምሳያ አልተተካም።"

✔️ አሽዓት ኢብኑ ኢስሐቅ እንዲህ ይላሉ፦ "ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር የዑለማዎች ፈርጥ ነው።"

✔️ አቡ ቃሲም አል-ላለካኢይ እንዲህ ይላሉ፦ "እርሱ (ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር) ታማኝ ነው። በሙስሊሞች ላይ ማስረጃ የሚሆን ሰው ነው።"

✔️ ዐልይ አል-መዲኒይ እንዲህ ይላሉ፦

(ليس في أصحاب ابن عباس مثل سعيد بن جبير، قيل: ولا طاوس؟ قال: ولا طاوس، ولا أحد)

"ከኢብኑ ዐብ-ባስ ባልደረቦች (ተማሪዎች) ውስጥ እንደ ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ያለ አምሳያ የለም።

'ጧውስም ቢሆን?" ተባሉ። "አዎ! ጧውስም ቢሆን!!" አሉ። ሌሎችም ቢሆኑ።"

✔️ መይሙን ኢብኑ ሚህራን እንዲህ ይላሉ፦ "ወደ እውቀቱ የፈለገ ቢሆን እንጂ፤ በምድር ላይ የማይወጣ ሁኖ ሳለ ሰዒድ በርግጥ ሞተ።"

✔️ ከኢብኑ ዐብ-ባስ ባልደረቦች ውስጥ አንዱ የሆኑት ኸዺፍ ኢብኑ ዐብዱር-ረ-ሕማን እንዲህ ይላሉ፦

(كان أعلمهم بالقرآن مجاهد، وأعلمهم بالحج عطاء، وأعلمهم بالحلال والحرام طاوس، وأعلمهم بالطلاق سعيد بن المسيب، وأجمعهم لهذه العلوم سعيد بن جبير.)

"(ከታቢዒዮች) ከመካከላቸው በቁርኣን ይበልጥ አዋቂያቸው ሙጃሂድ ነበር። ስለ ሐጅ ደግሞ ይበልጥ አዋቂያቸው ዐጧእ ነው። ስለ ሐራምና ሐላል (ክልክልና ፍቁድ ነገራቶች) ይበልጥ አዋቂያቸው ጧውስ ነው። ስለ ፍች ይበልጥ አዋቂያቸው ሰዒድ ኢብኑ ሙሰየብ ነው። እነዚህን የእውቀት ዘርፎች በሙሉ አካቶ ይበልጥ አዋቂያቸው ደግሞ ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ነው።"

አስባችሁታል?! ሰኢድ ምን ያክል ዐሊም እንደሆነ!!

||

♠ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ከዒልሙ ባሻገር ይበልጥ አላህን ፈሪ፣ በርሱም ላይ ተመኪ፣ እጅጉን ተናናሽ ነበር።

ከእለታት አንድ ቀን ሌሊት ላይ እየሰገደ ሳለ ሲያለቅስ፤ ያለቀሰበት አይኑ ሲነጋ እይታዋ ደከመ። ሐጂና ዑምራ በየ አመቱ ያደርግ ነበር። ቁርኣን በሶስት ቀን ውስጥ ያኸትም ነበር። በአንዳንድ ዘገባዎች ላይ እንደሰፈረው እንዳውም በአንድ ቀን ያኸትም ነበር ይላል። ብቻውን ሲሰግድ ለማኽተም ብሎ መቆሙን ይበልጥ ያስረዝም ነበር።

♠የሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ታሪክ ይህን ይመስላል።

ከዚህ ታሪክ ብዙ የምንማራቸው ቁም ነገሮች አሉ።

①, የሰዒድ ኢብኑ ጁበይርን ታላቅነትና የታላላቅ ታቢዒዮችን ውዳሴ።

②, የሰዒድ ዱዓ ተቀባይነት። ሐጃጅ እርሱን ከገደለ በኋላ በህይወት ብዙም ቀን አልቆዬም። በአንዳንድ ዘገባዎች ላይ እንደሰፈረው አርባ ቀን ሲሆን በአንዳንዶች ላይ ደግሞ ሃምሳ ቀን ነው፤ እነዚሁንም በከባድ ስቃይ ውስጥ ተውጦ።

መሞቱ በተሻለው ነበር።

③, ግፈኛ መሆን ያለውን መዘዝ።

ግፈኛ ሰው የቱንም ያክል ተመቸኝና አቅም አለኝ ብሎ ሌሎችን ቢበድል፤

በዚህች አለም ራሱ ቅጣቱን ይቀምሳል። በዚያኛው አለም ያለውንማ አላህ ይዞታል።

④, የሐጃጅ አሟሟት ትልቅ ውርደት ነው።

ተኝቶ እንኳ እንቅልፍ የለውም ነበር።

ሰውነቱ ሁሉ ተበክሎ ፓራላይዝድ ሁኖ ነበር የሞተው።

||

👉 ጽሑፌን እዚህ ላይ ልቋጨው።

እኛንም የቀደምት አበው ትውልዶችን ፈለግ ቀጥ አድርገን የምንከተል ሰዎች ያድርገን።

መቼም እናንተ እንኳ የረጅም ጽሑፍ ጥላቻ (Phobia) አለባችሁ፤ እኔ ስጽፍ የማይደክመኝን እናንተ ለማንበብ ይደክማችኋል።

የአላህ ፈቃዱ ከሆነ እንዲህ አይነት የቀደምት ደጋግ ሰለፎችን ታሪክ በማውሳት በቀጣይ ክፍሎች አስተያየታችሁንና የማንበብ ሁኔታችሁን አይቼ እመለሳለሁ።

እንዲህ አይነት እውነተኛ ታሪኮች ምናልባትም ዛሬ ላይ ከተቅዋ ተራቁታ የደረቀችውን ልባችንን፣ የማታነባውን አይናችንን፣ የተኛውን ህሊናችንን ለማርጠብና ለማንቃት ይረዱናል።

ሰለፎች ህይወታቸውን እንደት አሳለፏት ብለን እንመርምር።

ለማንኛውም እንደ ሁኔታችሁ አይቼ በቀጣይ ክፍል እስከምንገናኝ ሰላም ሰንብቱ።

ወስ-ሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱልሏሂ ወበረካቱህ።

ጽሑፉን ለሌሎችም ብታስተላልፉትና ሌሎችም አንብበው ቢጠቀሙ፤

ወደ ኸይር በማመላከታችሁ ምንዳን ትሸምታላችሁ።

||

ጽሁፉን ከሚከተሉት ድርሳናት ላይ ከከፊሎቹ ላይ ከፊል ታሪኩን፣ ከከፊሎቹ ላይ ደግሞ በብዛት ታገኙታላችሁ።

ሙሉ በሙሉ ግን አንዱ ላይ ብቻ አታገኙትም።

ሆኖም ግን እንዳይረዝም ብዬ (ረዝሞ የለም ወይ ባትሉኝ) የቀነስኳቸው ብዙ ሃሳቦች አሉ።

👉 ዋቢዎች፦

===========

✔️ ሒልየቱ-ል-አውሊያእ፡ 4/290-295

✔️ አል-ቢዳያህ ወን-ኒሃያህ፡ 9/107-108

✔️ ሲፈቱ-ስ-ሶፍዋህ፡ 2/51-54, 44

✔️ ሲየር አዕላም አን-ኑበላእ፡4/321

✔️ ታሪኹ-ጥ-ጦበሪይ፡ 4/23

✔️ ወፊያቱ-ል-አዕያን፡ 2/371

✔️ አን-ኑጁሙ-ዝ-ዛሂራህ፡ 1/228

✔️ አል-ሙንተዞም፡ 6/318

✔️ ሸዘራቱ-ዝ-ዝሃብ፡ 1/108

✔️ ታሪኹ ኸሊፋህ፡1/307

✔️ ጦበቃቱ ኸሊፋህ፡1/280

✔️ ጦበቃቱ ኢብኑ ሰዒድ፡ 6/256

✔️ ተራጂዑ አዕላሙ-ስ-ሰለፍ፡ ገጽ 47

↑↓

ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ

==========

ሙሐረም 27, 1441 ዓ.ሂ

መስከረም 15, 2012 E.C

September 26, 2019 G.C

||

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል የምለቃቸውን መከታተል ትችላላችሁ።

Join: t.me/MuradTadesse

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የየመን ጦር ኃይሎች መግለጫ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

የኮማንደር አብዱልመሊክ በድር አል-ዲን አል ሁቲ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ እና የታላቁን የየመን ህዝባችንን ጥያቄ እና የአረብ እና የእስላማዊ ሀገራት እና ነፃ ህዝቦች ሙሉ በሙሉ በጋራ እንዲቆሙ ላቀረቡት ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ከፍልስጤም ህዝብ ምርጫ እና ከነሱ አኩሪ ተቃውሞ ጋር አብሮ ለመቆም

ዛሬ ማለዳ የየመን ጦር ሃይሎች የባህር ሃይል በሁሉን ቻይ አላህ እርዳታ በባብ አል-ማንዳብ በሚገኙ ሁለት የእስራኤል መርከቦች ማለትም “ዩኒቲ ኤክስፕሎረር” መርከብ እና “ቁጥር ዘጠኝ” መርከብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽሟል።

የመጀመሪያው መርከብ በባህር ሃይል ሚሳኤል እና ሁለተኛው መርከብ በባህር ሃይል ድሮን ኢላማ የተደረገ ነው።

ኢላማ የተደረጉት ሁለቱ መርከቦች የየመን የባህር ኃይል ሃይሎችን የማስጠንቀቂያ መልእክት ውድቅ ካደረጉ በኋላ ነው።

የየመን ታጣቂ ሃይሎች የእስራኤል መርከቦች በጋዛ ሰርጥ በሚገኙ ፅኑ ወንድሞቻችን ላይ እያደረሱት ያለው ጥቃት እስኪቆም ድረስ የእስራኤል መርከቦች በቀይ እና በአረብ ባህር እንዳይጓዙ መከልከላቸውን እናሳውቃለን።

የየመን ጦር ሃይሎች ይህን መግለጫ እና ከዚህ ቀደም የየመን ጦር ሃይሎች ያወጣቸውን መግለጫዎች የሚጥሱ ከሆነ ህጋዊ ኢላማ እንደሚሆኑ ለመላው የእስራኤል መርከቦች ወይም ከእስራኤላውያን ጋር ግንኙነት ላላቸው መርከቦች ማስጠንቀቂያችንን ድጋሚ እናቀረባለን።

ሰነዓ፣ 20 ጁማዳ አል-አወል 1445 ሂጅራ

ዲሴምበር 3 ቀን 2023 ዓ.ም

በየመን ጦር ሃይሎች የተሰጠ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከዛሬው ጉባኤ የወጣ የጋራ ስምምነት መግለጫ!

🔴 በጋዛ ሰርጥ ላይ ያለውን የእብደት ጦርነት ለማስቆም ታሪካዊ፣ ልዩ እና ቆራጥ ውሳኔ ወስዷል።

🔴 በጋዛ ሰርጥ ላይ ለ17 አመታት የቆየውን ከበባ ለማንሳት ውሳኔ ሰጥቷል።

🔴 የራፋህ ድንበርን በቋሚነት በመክፈት፣ ለነዳጅ፣ ለእርዳታ እና ለህክምና ቁሳቁሶች ምቹ መተላለፊያ እንዲሆን ተወስኗል።

🔴 የጋዛ ሰርጥ መልሶ ግንባታን የሚያግዝ ፈንድ የጋራ ጥምረት በአስቸኳይ በማቋቋም ከ41 ሺህ በላይ ሙሉ በሙሉ የወደመ መኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም ከ222 ሺህ በላይ በከፊል የወደሙ መኖሪያ ቤቶችን የመንግስት መስሪያ ቤቶችን፣ መስጊዶችን፣ ቤተክርስትያኖችን፣ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመገንባት የወሰነ ሲሆን ይህን የፈፀሙ የጦር ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ እና ለአለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች እና ለሚመለከታቸው ፍርድ ቤቶች ለማቅረብ የአረብ እስላማዊ የህግ አካል ለማቋቋም ተወስኗል።

🔴 የወራሪዋ አምባሳደሮች ከአረብ እና ሁሉም እስላማዊ ሀገራት ማባረር ፣የሀገራቸውን አምባሳደሮች በመጥራት እየተፈጸመ ላለው ወንጀል እና እልቂት ምላሽ እና ይህንን ወራሪ ሙሉ በሙሉ ቦይኮት ለማድረግ ተወስኗል።

🔴 ወራሪውን ከፍልስጤም ግዛት ማባረር፣ ወረራውን ማስቆም እና እየሩሳሌም ዋና ከተማዋ በማድረግ የፍልስጤም ሀገርን ለመመስረት ስምምነት ላር ተደርሷል።

የሙሐመድ ትውልድ From Ultra palestine

#palestine

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#ተጨማሪ

የኢራን ፕሬዚደንት፡- የመሪዎች ጉባኤው ዘግይቷል፣ እናም የዛሬው ስብሰባችን ለፍልስጤም ህዝብ የሚጠቅም ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ተስፋ አደርጋለሁ እና ቅድሚያ የሚሰጠው የተኩስ አቁም ነው።

የኢራኑ ፕሬዝዳንት፡ የጽዮናዊው አካል ከጋዛ እንዲወጣ እና እራደረሰ ያለው ከበባ እንድቆም ማድረግ አለብን።

የኢራኑ ፕሬዝዳንት፡ የጽዮናዊውን አካል ጥቃት በተለይም በሃይል ደረጃ ማቋረጥ አለብን

የኢራን ፕሬዝዳንት፡ የጽዮናውያን እና የአሜሪካ መሪዎችን ለመቅጣት አለም አቀፍ ፍርድ ቤት መመስረት አለበት።

የኢራን ፕሬዝዳንት፡ የጋዛ መልሶ ግንባታ ፈንድ መመስረት እና የእርዳታ ኮንቮይዎች መላክ አለባቸው

የኢራን ፕሬዚደንት፡- ለታጋሩ የፍልስጤም ህዝብ ሰላምታ እንሰጣለን እና የተቃውሞ ብድኑን እጅ እንሳሳለን።

የኢራን ፕረዚደንት፡ እስላማዊ ሀገራት በእስራኤል ላይ ነዳጅና የንግድ ማዕቀብ እንዲጭኑ

Send as a message
Share on my page
Share in the group