Translation is not possible.

ያደርገኛል።

ሐጃጅ፦ ይቅር ልበልህ? ልተውህ??

ሰዒድ፦ ይቅር ከተባልኩ ይቅርታው ከአላህ ነው። አንተ ይቅር አልክ አላልክ ዋጋ የለውም።

ሐጃጅ (ለግድያ ፈጻሚዎቹ)፦ "ይህን ሰው ግደሉት!" ብሎ አዘዘ።

ሰዒድም ወደሚገደልበት ቦታ እየተወሰደ ሳለ ልጁ በዚህ ቦታ ስላየው ያለቅስ ጀመር። ሰዒድም ልጁን ሲመለከተው "ምንድን ነው የሚያስለቅስህ?" አለው።

ልጁም "ከ57 አመት በኋላ አባትህ ምን ቀረው?" አል።

ሰዒድ አንድ ወዳጁንም ሲያለቅስ ተመለከተው።

"ምንድን ነው የሚያስለቅስህ?" ሲልም ጠየቀው።

ግለሰቡም "ባገኘህ ነገር!" ሲል መለሰ።

ሰዒድም "አታልቅስ!፤ ይህ እንደሚሆን በአላህ እውቀት ዘንድ ነበር!" አለውና ይህን የቁርኣን አንቀጽ አነበበ፦

{ما أصاب من مصيبة في الأرض ولا في أنفسكم إلا في كتاب من قبل أن نبرأها}

"በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትሆን እንጅ፤ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው። "

[አል-ሐዲድ: 22]

ሰዒድ ሊገደል ሲል ሳቀ። ገዳዎቹም ተገረሙና ለሐጃጅ ነገሩት። ሐጃጅም ወደርሱ እንዲያመጡት ነገራቸው።

ሰዒድ ዳግመኛ ወደ ሐጃጅ ዘንድ ሲመጣ፤ ሐጃጅ "ምንድን ነው ያሳቀህ?" አለው።

ሰዒድ፦ "አንተ ለአላህ እንዲህ አይነት አመለኛ ሁነህ ሳለ፤ እርሱ ባንተ ላይ ያለው ትዕግስትና እዝነት ገርሞኝ ነው!" አለው።

ሐጃጅ (ለገዳዮቹ)፦ "ፊት ለፊቴ ግደሉት!" አላቸው።

ሰዒድ፦ "መጀመሪያ ሁለት ረከዓ ሶላት እንድሰግድ ፍቀዱልኝ?" አላቸው። ፈቀዱለት። ቂብላውን ተቅጣጭቶ እየሰገደ ሳለ ይህን የቁርኣን አንቀጽ አነበበ፦

{وجهت وجهي للذي فطر السموات والأرض حنيفًا وما أنا من المشركين}

"«እኔ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው (አምላክ) ቀጥተኛ ስኾን ፊቴን አዞርኩ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም»፡፡ "

[አል-አንዓም: 79]

የዚህን ጊዜ ሐጃጅ፦ "ፊቱን ከቂብላው አዙሩና ወደ ክርስቲያኖች ቂብላ አዙሩት!" አለ።

እነርሱም አዞሩት።

ሰዒድም የዚህን ጊዜ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ አነበበ፦

{فأينما تولوا فثم وجه الله}

"ምሥራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው (ፊቶቻችሁን) ወደ የትም ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ነው፡፡ "

[አል-በቀራህ: 115]

ሐጃጅ አሁንም "ፊቱን ወደ መሬት ድፉት!" አለ።

ሰዒድም የዚህን ጊዜ ይህን አንቀጽ አነበበ፦

(مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَى!)

"ከርሷ (ከምድር) ፈጠርናቸሁ፤ በርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፤ ከርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን።"

[ጦሃ: 55]

ሐጃጅም "እረዱት!" አላቸው።

ሰዒድ እንዲህ አለ፥ "أما أنا فأشهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له وأن محمدًا عبده ورسوله، خذها مني يا حجاج حتى تلقاني بها يوم القيامة"

"ከአላህ ውጭ በሐቅ የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፣ ለርሱ ቢጤም አጋርም የለውም። ሙሐመድም የርሱ ባሪያውና መልዕክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ!" አለና፥ "ሐጃጅ ሆይ! ይህቺን ቃል ከኔ ያዛት፤ በርሷ ኋላ የውመል ቂያማ አላህ ፊት እንገናኛለን!" አለው።

እንዲህም ብሎ ዱዓ አደረገ፦ (اللهم لا تسلطه على أحد يقتله بعدي)

"አላህ ሆይ! ከኔ በኋላ ማንንም እንዲገድል አቅሙን አትስጠው።"

ሰዒድም በሃምሳ ዘጠኝ አመቱ በወርሃ ረመዳን 11, 95 ዓ.ሂ (714 G.C) ምላሱ በዚክር እንደረጠበች ታረደ።

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን‼

እኛ የአላህ ነን፤ ወደርሱም ተመላሾች ነን‼

የሚገርመው ነገር፤ ሐጃጅ ሰዒድን ከገደለ በኋላ ከሃምሳ ወይም ከአርባ ቀናት በላይ በህይወት አልቆዬም። እነዚህንም የቆዬው በከባድ የህመም ስቃይ ውስጥ ሁኖ ነበር።

ሐጃጅ በከፋ ህመም ውስጥ ገባ። "በኔና በሰዒድ ኢብኑ ጁበይር መካከል ያለው ምን ነበር? በጠና ታምሜ መተኛት ስፈልግ፤ ልተኛ ስል እግሬን እየነካካ አላስተኛኝ ይላል!" ይል ነበር።

(ሱብሐነል'ሏህ!!)

አንዳንድ ዘገባዎች ላይ እንደሰፈረው፤

ሐጃጅ በጠና ታሞ ተኝቶ ሳለ በህልሙ ሁልጊዜ ሰዒድ ኢብኑ ጁበይርን ይመለከታል፣ አይኑ ላይ ግርጥ ይልበታል። ሰዒድ ሐጃጅን በልብሱ ይይዘውና "አንተ የአላህ ጠላት ሆይ ምን አድርጌህ ነበር የገደልከኝ?" ይለዋል። ሲነጋና ሐጃጅ ከእንቅልፉ ሲነቃ፤

(ما لي ولسعيد بن جبير كلما أردت النوم أخذ برجلي!!)

"በኔና በሰዒድ ኢብኑ ጁበይር መካከል ያለው ምንድን ነው?፣ በኔና በሰዒድ ኢብኑ ጁበይር መካከል ያለው ምንድን ነው?" በማለት በተደጋጋሚ በትካዜ ተውጦ ይለፍፋል። (ያ ሰላም!!)

የሚደንቀው ነገር ሐጃጅ አሁንም ከእንቅልፉ ሲነቃ፤

"አላህ በአንተ ላይ ምን ሰራ?" ሲባል፤

"በእያንዳንዱ በገደልኩት ሁሉ አንዳንድ ጊዜ ገደለኝ። በሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ግን ሰባ ጊዜ ገደለኝ!" ይላል። (ኢናሊላሂ!)

እንዲህ የሚል ሰፍሯል። አል-ሐጃጅ ሊሞት አቅራቢያ ጥቂት ቀናቶች ሲቀሩት ሰውነቱ ሙሉ ፓራላይዝድ ሆነ። በሚቃጠል እሳት ላይ እጁ ሲደረግ፤ ቆዳው እየነደደ ግን አይሰማውም። ህመሙም በጣም ጠና። ከሰውነቱ ውስጥ ትል ይወጣና ይገባ ጀመር። (አላህ ይጠብቀን።)

*

ሐጃጅ ህመሙ በጣም ሲጠናበት ወደ ሐሰነል በስሪ ዘንድ "ኑልኝ!" ብሎ ሰው ላከ።

ሐሰነል በስሪም እንዲህ አሉት፥ "አልነገርኩህንም ነበር?! የምሁራንን መንገድ አልተከተልክም!፤ ሰዒድን እኮ ገድለሃል!!"

ሐጃጅም "እዚህ የጠራሁህ እኮ እንድታድነኝ አሊያም መድሀኒት እንድትፈልግልኝ አይደለም።

ይልቁንም ከምታዬው ስቃይ አላህ ቶሎ ገድሎ እንዲያሳርፈኝ ለምንልኝ፣ ዱዓ አድርግልኝ ብዬ ነው!" አላቸው።

ወዳው ብዙም ሳይቆይ ሞተ።

ኢማሙ አሕመድ እንዲህ ይላሉ፦ "ሰዒድ በተገደለ ጊዜ፤

የርሱን እውቀት የማይፈልግ በአለም ላይ አንድም ሰው አልነበረም።"

ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ትልቅ ሰው ነበር።

ገና በልጅነቱ ጀምሮ እውቀትን ቀስሟል።

ከአስር በላይ የነብዩ ሶለል'ሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሐቦች ላይ ተምሯል።

ብዙ ሐዲሥም አስተላልፏል። ከአነስ ኢብኑ ማሊክ፣ ከዾሐክ ኢብኑ ቀይስ፣ ከዐብደልሏህ ኢብኑ ዙበይር፣ ከኢብኑ ዐባስ፣ ከኢብኑ ዑመርና ከሌሎችም ተራራ ተራራ ከሚያክሉ ሶሐቦች አስተላልፏል።

ታላቁን የሐዲሥ ዘጋቢ አቢ ሁረይራን፣ የሙእሚኖችን እናት ዓኢሻን፣ አቡ ሙሳ አል-አሽዓሪይንና ሌሎች የነቢዩ ባልደረቦችንም በአይኑ አይቷል፤ ከነርሱም ብዙ እውቀትንና ሐዲሥን ገብይቷል።

ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ከነዚህ ሁሉ ሶሐቦች ሐብሩል ኡማህ የተሰኘውን ታላቁን የቁርኣን ተንታኝ፤ በአሽረፈል ኸልቅ አንደበት "አላህ ሆይ ተፍሲርን አሳውቀው!" ተብሎ የተነገረለትን ታላቅ ሶሐባ ዐብደል'ሏህ ኢብኑ ዐብ-ባስን ቋሚ አስተማሪው አድርጎ ያዘ። ከርሱም ተፍሲርንና ሌሎች እውቀቶችን ቀስሟል።

ከስነ ስርአቱ የተነሳ፤ ሰዒድ አስተማሪው ኢብኑ ዐብ-ባስ እያለ ፈታዋ አይሰጥም ነበር። ግን ስለሚፈቅድለት እዚያው እያለ ፈታዋ ይሰጣል።

ኢብኑ ዐብ-ባስ የዒራቅ ሰዎችን እውቀት ከሰዒድ ኢብኑ ጁበይር እንዲሸምቱ ይነግራቸው ነበር።

||

✔️ በአንድ ወቅት አንድ የኩፋ ሰው ወደ ኢብኑ ዐብ-ባስ ዘንድ መጣና ፈታዋ ጠየቃቸው።

ኢብኑ ዐባስ ለዚህ ለጠያቂ እንዲህ አሉት፦

Send as a message
Share on my page
Share in the group