የኢማም አቡ በከር ባቅላኒይ እና የነሷራዉ ቄስ ታሪክ:-
⭕️አቡ በክር አልባቅላኒይ ይህ ሰው ትልቅ ዓሊም ከመሆኑም ባሻገር ክርክር ላይ ሚስተካከለው የለም የሚባልለት ሰው ነው እናላችሁ የሆነ ቀን ይህ ሰው ከአንድ ቄስ ጋር ይገናኙ'ና
☞ቄሱ፦"እናንተ ሙስሊሞች ከባድ የሆነ ወገንተኝነት ይታይባችኋል"
☞አቡ በክር፦"እንዴት?"
☞ቄሱ፦ "ምክንያቱም እናንተ ለራሳችሁ ክርስትያን ሴቶችን እና የአይሁድ ሴቶችን ታገባላችሁ፤ ነገር ግን የናንተን ሴቶች ለማንም አሳልፋችሁ አትሰጡም፤ ሀራም ትላላችሁ።"
☞አቡ በክር፦ "አሃ! እኛ እኮ ክርስቲያን ሴቶችን ምናገባው በዒሳ ስለምናምን ነው።
☞የአይሁድ ሴቶችን ምናገባው ደግሞ በሙሳ ስለምናምን ነው፤ እናንተም በሙሀመድ ካመናችሁ ሴቶቻችንን እንድርላችኋለን።"
✹•━━━━━━•✹…………
☞አቡ በክር በሂጅራ አቆጣጠር በ371 ላይ ከነበሩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዑለማኦች ይመደብ ስለነበር በግዜው የነበረው የዒራቅ ገዢ አቡ በክርን ወደ ቆስጠንጢንያ በግዜው የሮም ዋና ከተማ ለክርክር ላከው።
☞የሮሙ ንጉስ የአቡ በክርን መድረስ በሰማ ግዜ ለወታደሮቹ የቤተመንግስቱን በር እንዲያሳጥሩት'ና፤ አቡ በክር ሲገባ አጎብድዶ እንዲጋባ ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ ባዘዛቸው መሰረት ወደ ቤተ መንግስት እሚገባ ሰው ሁሉ ዝቅ ብሎ እንዲገባ በሩን አሳጠሩት።
☞አቡ በክርም ቤተ መንግስት ደርሶ ሊገባ ሲል በሩ አጥሮ ተመለከተ'ና የተሸረበውን ሴራ በመረዳት ፊቱን አዞሮ፤ ወደ ኋላ በማጎብደድ ለንጉሱ ፊት ቂጡን ሰጥቶ ገባ።
☞ይህን ግዜ ንጉሱ የአቡ በክርን ከባድነት ተገነዘበ።
☞አቡ በክር ከገባ በኋላ ከንጉሱ ዙርያ የተሰለፉትን ቄሶችን ሲያይ እንኳን ደህና ቆያችሁኝ አይነት ነገር አላቸው [ሸሪዓው ሰላምታን ግን አላቀረበም ለምን አህለል ኪታብ ስለነበሩ]።
☞ከዝያም ወደ ዋናው ቄሳቸው ዞር ብሎ፦ "እንዴት ነህ? ቤተሰብ ልጆች እንዴን ናቸው?" አለው።
☞ይህን ሲሰማ ንጉሱ እጅግ በመቆጣት "ቄሳችንን እንደማይጋቡ እና እንደማይዋለዱ እያወቅክ እንዴት እንዲህ አይነት ጥያቄ ትጠይቃለህ?" አለው።
☞አቡ በክርም፦ "አላሁ አክበር !
☞ቄሶቻችሁን ልጅ ከመውለድ እና ሚስት ከማግባት እያጥራራችሁ ለአላህ ግን የመርየም ልጅ የሆነውን ዒሳን ልጁ ነው በማለት ትቀጥፋላችሁ" አለው።
☞የንጉሱ ንዴት እየጨመረ በንቀት ተውጦ፦ "ዓኢሻ ስለፈፀመችው ቅጥፈት ምን ትላለህ" አለው።
☞አቡ በክርም፦ "ዓኢሻ ባልሰራችው ያወሩባት ሙናፊቆች ናቸው።
መርየምም ባልሰራችው ያወሩባት የሁዶች ናቸው፤ ሁለቱም ግን ንፁሃን ናቸው።
☞#መርየም ደግሞ ትዳር አልያዘችም ፤ ግን ወልዳለች። ታዲያ ማን ናት እስቲ ከሁለቱ ለጭፍን ወቀሳ ቅርብ የሆነችው።
☞#እውነት እናውራ ካልን ዓኢሻ ትዳር ይዛለች ግን በውሸት ቢቀጠፍባትም አልወለደችም።
☞ሁለቱም ንፁሃን እንስቶች
ናቸው" አለ።
☞ንጉሱ ብስጭቱ ጨመረ እና፦ "ነብያችሁ ለጦርነት ይዘምት ነበር?" አለው።
☞አቡ በክርም፦ "አዎን" አለ።
☞ንጉሱም፦"በጦርነት ሰዐት ፊት ለፊት ገብቶ ይጋፈጥ ነበር?" አለው።
☞አቡ በክርም፦ "አዎን" አለው።
☞ንጉሱም፦ "ድልን ይቀዳጅ ነበር?" አለው።
☞አቡ በክርም፦ "አዎን" አለው።
☞ንጉሱም፦ "ይሸነፍስ ነበር?" አለው።
☞አቡ በክርም፦"አዎን" አለው።
☞ንጉሱም፦"ይገርማል?ነቢይ ይሸነፋል እንዴ?" አለ።
☞አቡ በክርም፦"ይገርማል!
ጌታ ይሰቀላል እንዴ?" ብሎ ክርክሩን አሳመረለት።
💥 فَبُهِتَ الذي كفر