Translation is not possible.

➡️ በሁሉም የሰው ልጆች ላይ የሚፈራረቁ ስምንት ነገራቶች፦

①) ደስታ ②) ሀዘን

③) መሰባሰብ ④) መለያየት

⑤) ምቾት ⑥) ችግር

⑦) ህመም ⑧) ጤንነት

♦️መልካም ነገር ሲገጥማቸው ከሚያመሰግኑት

♦️በመጥፎ ነገር ላይ ደሞ ከሚታገሱ

https://t.me/+DHzDI6T7QyxkNGRk

Telegram: Join Group Chat

Telegram: Join Group Chat

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ዱንያ ከአላህ...ለራቀ ሰው

ልክ እንደ ቃርያ ማሳ ናት

እየተቃጠለ እንጂ እየተደሰተ

መቼም አይኖርም...ደስተኛ

ለመሆን ከፈለክ መጀመርያ

አላህን በትክክል በመገዛት

አስደስተው አላህን ባግባቡ

መገዛት በራሱ ትልቅ ደስታ አለው

👇👇👇👇👇 https://t.me/+DHzDI6T7QyxkNGRk

Telegram: Join Group Chat

Telegram: Join Group Chat

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

በእስልምና ውስጥ መኖር እራሱ ትልቁ ጸጋ ነው ። አልሃምዱሊላህ🤲🤲🤲

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ቀናተኛው ነብይ! 

ካሀዲያን ሀይማኖታቸው የጦርነት ህግ የለውም።ስለሆነም ጦርነት ማለት ለነርሱ ያገኙትን መግደል ነው።ሴቶችና ህፃናት ታርጌት ናቸው።ቤቶችና እንስሳት ጭምር ቀጥተኛ ሰለባ ናቸው።በኡሑድ ዘመቻ እለት የተከሰተውም ይህ ነበር።

ከሴት ሰሓቦች የሆነችው ኡሙ አይመን (ረዐ) ቁስለኞችን ውሃ ለማጠጣት ነበር የመጣችው።የውሃ እቃ ብቻ የያዘች ሴት! .... የሙሽሪኩ ወታደር ኢላማ ከመሆን ግን  አልተረፈችም ነበር። ቀስቱን አወጣና ወደርሷ አነጣጥሮ አስወነጨፈው....

ቀስቱ እሷን መግደል ባይሳካለትም የልብሷን ጫፍ ሸመቀቀውና ሰውነቷ ተጋለጠ።ረሱል በኡማቸው ክብር ላይ ቀናተኛ ነበሩ ።ይህን ሲመለከቱም የሙስሊም ሴት ክብር ነውና በጣም ከፋቸው።

የኡሑድ ዘመቻ የመጨረሻዎቹ ሰአታት ላይ ነበሩ። ትጥቅና ጉርስ የተመናመነበት ሰአት ላይ!  ....

ያለችውን ስለት-አልባ ቀስት ከኮረጆው ውስጥ መዘዙና ለጀግናው ሰዕድ አቀበሉት!

«አስወንጭፍ! እናትና አባቴ ፊዳ ይሁኑልህና!» አሉት። .... ረሱል ወላጆቼ ፊዳ ይሁኑልህ ያሉት ሌላ ሰሃባ የለም!

ከዚያስ ምን ሆነ?  ....

የቀስት ባለሙያው ሰዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስ (ረዐ) ራሱ ይተርክልናል ...

«(በኡሑድ ቀን)  ከሙሽሪኮች አንድ ሰው በሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ነበር። የአላህ መልእክተኛም ﷺ እናቴም አባቴም ፊዳ ይሁኑልህ አስወንጭፍ አሉኝ። ስለት አልባ ቀስት መዘዝኩኝና አስወነጨፍኩ።ጎኑን አገኘሁትና ወድቆ ሀፍረተ ገላው ተጋለጠ!የአላህ መልእክተኛምﷺ የፊት ጥርሳቸውን እስካየው ድረስ ሳቁ። ( ሙስሊም 6237)

በቡኻሪ (4055)  ላይ ደግሞ ረሱልﷺ ራሳቸው ቀስት መዘው እንደሰጡት ተዘግቧል።

ድሮ ታላቅ እንደነበርን ሂሳብ የሚወራረደው እንዲህ ነበር!ረሱለላህ የሙእሚን ክብር ሲዋረድ የሚያብከነክናቸውና ህዝባቸው ሲጠቃ  የሚከብድባቸው የሆኑ ቀናተኛ ነብይ ነበሩ።

ይህን ሲል የገለፃቸው ጌታ የላቀ ነው! 

«ከነፍሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን (ላይ) ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡» (አት ተውባህ 128)  

ኢማሙ ነወዊይ «ረሱል የሳቁት በመገደሉ እንጅ ሀፍረተ ገላው በመገለጡ አይደለም» ይላሉ።

 

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ዐብዱላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱም «ዐይነበሲር» የሆነ ሰሃባ ነበር ። የእናታችን ኸዲጃ  (ረዐ) የየሹማዋ ልጅ ነው።በኢስላም ትልቅ ደረጃ ካላቸው ሰሃቦች ውስጥ ሲሆን ማየት የማይችል በመሆኑ የጂሃድ ግዳጅ የተነሳለት ነበር።

የአላህ መልእክተኛ( ሰዐወ) ለዘመቻ ሲወጡ እርሱን መዲናን እንዲያስተዳድር ወክለውት ይሄዱ ነበር።

በዑመር ኢብኑልኸጣብ ዘመን ፋርሳውያንን ለመዝመት ዑመር አወጁ።ሰዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስንም አሚር አደረጉት። ኢብኑ ኡሚ መክቱም ዑዝር ያለው ሰው ሆኖ ሳለ ነገር ግን ከመዲና ወደ ዒራቅ ቃዲሲያ ላይ ለመሳተፍ ተጓዘ።

አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዐ)እንዲህ ይላል፦ የቃዲሲያ ጦርነት ላይ ማየት የተሳነውን ዐብዱላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱምን ተመለከትኩት።የጦር ልብስ ለብሶ ጫፎቹ ይጎተታሉ።በእጁም ጥቁር ባንድራ ይዟል ።

«አላህ ያንተን ዑዝር አንቀፅ አውርዶበት የለ?» ተብሎ ተጠየቀ።እሱም «አዎ!  ነገር ግን እኔ ራሴን በማስገኘት የሙስሊሞችን ቁጥር ለማብዛት አስቤ ነው !አላቸው።»

(ተፍሲሩል ቁርጡቢይ)

ኢማሙ ዘሀቢይ ይህ ታላቅ ሰሃባ በዚሁ ቃዲሲያ ላይ ሸሂድ እንደሆነ ያትታሉ። የሙስሊሞች ቁጥር በዛ ከተባለ ከ7000 በላይ ሲሆን የካሀዲያን ቁጥር ደግሞ 40,000 ወይም 60,000 ነበር ተብሏል።

የረሱል ሙአዚን ረዲየላሁ ዐንሁ ወአርዳሁ!

የቴሌግራም ቻናል ፦ ismaiilnuru!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group