UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

َ ➖➖➖➖

الاستقلال الحقيقي هو استقلالك يوم القيامة بنفسك، لا يطالبك أحد بثمن غيبة اغتبته إياها، ولا حق من حقوقه. أن تأتي آمنًا يوم القيامة لا تخشى على حسناتك ولا تطمع في أحد من أهلك بحسنة واحدة يوم يفر المرء من أخيه وأمه وأبيه وصاحبته وبنيه

﴿لِكلِّ امرِئ مِنهُم يَومَئِذ شَأنٌ يُغنيهِ﴾.

«جاهد نفسك على ترك الغيبة»

الغيبة: هي ذكرك لشخص بما يكره من العيوب التي فيه في غَيْبَته بلفظٍ، أو إشارةٍ، أو محاكاةٍ.

ولا تُبقي لأحدٍ عندكَ مَظلَمة.

"كُلُّ امْرِئٍ مُصَبَّحٌ في أهْلِهِ

والمَوْتُ أدْنَى مِن شِراكِ نَعْلِهِ"

منقول:بتصرّف

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

أوصى الإسلام بالنساء وصية مشروطه بما في الشريعة لها من حقوق وبما فيها من ضعف فطري فأصبحت بعض النساء تستخدم تلك الوصية للجور على حقوق أزواجهن أو تبرير مصائب تفعلها أو لصد النصح عنها فنوصيكم بتقوى الله فأخذ مال زوجك بغير حق لك فيه هو سرقة وإن ساعدك القضاء في ذلك ومال تحتاسبين عليه أخذك ما في عش الزوجية كاملاً بعد الطلاق من أساس هذا ظلم وبهتان عظيم وسرقة ووالله ستحاسبين عليه وتبرير ذنوبك بأن الكل يفعل أو أن المجتمع موافق ستحاسبين عليه أيضا فلا يخفى على الله شئ ونحن مُلاقيه فُرادا فاتقوا الله في أنفسكم.

#أَمةوعَبد

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሙስሊም አማራ አለ ግን?

~

በተያያዘው ቪዲዮ ላይ የሚታዩት ማኅበረ ደና ቁራ ን እንደሚያስተጋቡት የአማራ ህዝብ የአይሁድ ነገድ አይደለም። ይሄ ፍጥጥ ያለ ውሸት ነው። እንዲያውም "የአይሁድ ነገድ ነን" የሚል አካል በራሱ ላይ "መጤ ነኝ" ብሎ እየመሰከረ ነው። በርግጥ መጤነት የሰለጠኑ ሰዎች ዘንድ ነውር አይደለም። ነውር የሚሆነው በመጤነታቸው የሚኮፈሱ አካላት ሌሎችን "መጤዎች" እያሉ ሊያነውሩ ሲሞክሩ ነው። እንዲህ አይነቶቹን ነውር ጌጡዎች በ"ነውራችሁ" አታጊጡ ብለን እናስታውሳለን።

መታወቅ ያለበት ሐቅ ብሄርና ቋንቋ በዘመናት ውስጥ ውልደት፣ እድገትና ሞት ያስተናግዳሉ። አንድ የነበረ ቋንቋ በአካባቢ መለያየትና መራራቅ የተነሳ በሂደት የተለያየ ቋንቋ ወደመሆን ሊቀየር ይችላል። ይሄ ውልደት ነው። ከሌሎች ቋንቋዎች እየወሰደ የሚዳብርና የሚሰፋም አለ። የቋንቋ እድገት አንዱ መገለጫ ይሄ ነው። የተለያዩ ቋንቋዎች በሌሎች ተውጠው ሊጠፉም ይችላሉ። ይሄ የቋንቋ ሞት ነው። በውጭው በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በዐረብኛ፣... ተውጠው ብዙ ቋንቋዎች ሞተዋል። በሃገራችንም የከሰሙና በመክሰም ላይ ያሉ ቋንቋዎች አሉ።

የአማራ ብሄርና ቋንቋም በዘመናት ውስጥ ሌሎች ህዝቦች የቋንቋው ተናጋሪ በሆኑ ቁጥር እየሰፋ የመጣ ቅይጥ ማንነት ነው። የጋፋት ቋንቋ በዚህ ዓይነት ሂደት ጠፍቷል። የአርጎባ ህዝብ የራሱን ቋንቋ ጥሎ የአማርኛና የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሆኗል። ይሄ የአማርኛ ብቻ ሳይሆን የብዙ ቋንቋዎች የጋራ ባህሪ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በታሪክ አማራ የሚለው ቃል ክርስቲያን ማለት እንደነበር እስከ ቅርብ ጊዜ የሚታወቅ ነው። ይህ የሆነው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪው በአመዛኙ ክርስቲያን በመሆኑ እንጂ አማራነት በራሱ ክርስትና ስለሆነ አይደለም። ብሄር ማለት የጋራ ቋንቋና ማንነት ያላቸውን ህዝቦች ለመግለፅ እስከዋለ ድረስ በእምነት ቢለያዩም አማርኛ ቋንቋ የሚያገናኛቸው ህዝቦች አሉ፣ ዛሬ። ትኩረቴ አማራ ከሚለው ጥሬ ቃል ላይ አይደለም። ወደ ኋላ ረዘም ያለ ዘመን ብንመለስ ብዙ ብሄሮችን የዛሬ ስማቸውን ከነ ጭራሹ አናገኝም። ይሄ ማለት የጋራ ማንነት አልነበረም ማለት አይደለም።

ስለዚህ ዛሬ የትናንቱ የአማራነት ፅንሰ ሃሳብ የለም። አማራ ማለት ዛሬ ብሄር እንጂ ሃይማኖት ገላጭ አይደለም። በብሄር መለኪያ ከአማርኛ ተናጋሪው ክርስቲያን ጋር አንድ የሆኑ ሙስሊሞችን "አማራ አይደላችሁም" አይባልም። ብሄሩ ውስጥ የመሸጉ ገፊ አካላት መኖራቸውም የሚቀይረው ነገር የለም። "ትግሬ ብሎ ሙስሊም የለም" ብለው የሚያምኑ አግኣዚያን ስለኖሩ ሙስሊም ትግሬዎችን ትግሬነታቸውን መግፈፍ አይቻልም። "የኦሮሞ ነባር እምነት ዋቄፈና ነው" የሚሉ አካላት ስላሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊምና ክርስቲያን ኦሮሞዎችን ኦሮሞነታቸውን መግፈፍ ይቻላል? አይሆንም። በብሄርና በቋንቋ የለየንኮ ፈጣሪ እንጂ ፖለቲከኞች አይደሉም። ከአፋር ቤተሰቦች የተወለደን አካል አፋርነቱን መፋቅ ይቻላልን? እንኳን ሌሎች ራሱም መቀየር አይችልም። የአማራ ሙስሊሞችም ጉዳይ እንደዚያ ነው።

ጉዳዩ በቁጥር ማነስና መብዛት የሚወሰንም አይደለም። በዐረቡ ዓለም ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች 5% አይሞሉም። ቁጥራቸው ስላነሰ ዐረብነታቸውን መንጠቅ እንችላለን? አይሆንምኮ! በአማራ ፖለቲከኞች አግላይ አካሄድ ሰበብ በክልሉ ውስጥ ያሉ ከ17% (በመንግስት ህዝብና ቤት ቆጠራ ከተቀመጠው) በላይ ሙስሊሞችን ብሄር የለሽ ናቸው ልንል ነውን? አንችልምኮ! ደግሞም ራሱን በሆነ ብሄር የሚገልፅ አካል "እናንተ ግን ብሄር የላችሁም" ማለት አለበት ወይ? አይባልም። ስለሆነም ሙስሊም ወገኖቻችንን ራሳቸውን በአማራነት ስለገለፁ የምንተችበት አካሄድ ፈፅሞ የተሳሳተ ነው። ማድረግ ያለብን ዘረኝነት ሲጎትታቸው ካየን ከየትም ብሄር ቢሆኑ አላህን እንዲፈሩ ማስታወስ ብቻ ነው። እንጂ አማራ ተብለው እየተገደሉበት፣ እየተገፉበት ያለን ማንነት የለም አይደላችሁም አይባልም።

ስለዚህ  ዛሬ አማራነትን ክርስቲያን ማለት አድርጎ የሚገልፅ ካለ ምሁርም ይሁን መሀይም፣ ደጋፊም ሆነ ነቃፊ ያለ ጥርጥር ተሳስቷል። ይሄ አተረጓጎም የህዝቦችን ማንነትና ማህበራዊ ውቅር ተለዋዋጭነት (dynamism) ከግንዛቤ ያላስገባ ግልብ ድምዳሜ ነው። ስያሜዎች በዘመናት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች እንደ አካባቢው ሁኔታ ይለዋወጣሉ።

* ትናንት ቱርክ፣ ደይለም፣ ፋርስ የሚሉት መጠሪያዎች ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦችን ለመግለፅ የዋሉበት ዘመን ነበር፣ ለሚታወቅ ምክንያት። ያ ዘመን ካለፈ በኋላ እነዚህ ስያሜዎች ሃይማኖትን ገላጭ የነበረው ይዘታቸው ቀርቷል። አማራም ላይ ያለው እውነታ ተመሳሳይ ነው።

* በፊት አጎራባቾቹ አማራና አርጎባ መሀል የነበረው እውነታም ይህንን አጉልቶ ያሳያል። ሰሜን ሸዋ ላይ አንድ ክርስቲያን አማራ ወደ ኢስላም ሲገባ "እከሌ አርጎባ ሆነ" ነበር የሚባለው። አንድ አርጎባ ወደ ክርስትና ሲገባ ደግሞ "አማራ ሆነ" ነበር የሚባለው። ዛሬ ግን አርጎባነት ዘር እንጂ ሃይማኖት እንዳልሆነ ግልፅ ነው። አንድ ሰው ሃይማኖቱ ስለተቀየረ ዘሩ እንደማይቀየር ማወቅኮ ያን ያህል ውስብስብ ሂሳብ አይደለም።

* ሲዳማ የሚለው ቃል ሃይማኖትን ሲገልፅ የነበረበት ዘመንም ነበር። ዛሬ የሲዳማ መስሊሞችን "ሲዳማ አይደላችሁም፣ ሙስሊሞች ናችሁ" ልንላቸው አንችልም። ምክንያቱም ሲዳማነት እንደ ትላንቱ ሃይማኖትን ሳይሆን የሲዳማ ቋንቋ በወል የሚያገናኛቸው ህዝቦችን የሚገልፅ የብሄር ስያሜ እንደሆነ ግልፅ ነውና። ይሄ ቀላል ግንዛቤ አማራ ዘንድ ሲደርስ መልኩን የሚቀይርበት ስሌት የለም።

ስለዚህ የአማራ ሙስሊሞች ከብሄር አንፃር እንዴት ራሳቸውን አማራ ብለው ይጠራሉ የሚል አተካራ ውስጥ መግባት አያስፈልግም። ይሄ ብሄር ተኮር ጥላቻና መነቋቆርን ከማምጣት ባለፈ የሚያመጣው ኸይር የለም። ማድረግ ያለብን በየትኛውም ብሄር ውስጥ ያደፈጡ ዘረኛ ቡድኖች መጠቀሚያ እንዳንሆን ተቆርቋሪነት በሚታይበት መልኩ እርስ በርሳችን መመካከር ነው። ዋናው ነገር ኢስላማዊ ወንድማማችነታችን የዘር አጥር የሚገድበው አለመሆኑ ነው። የላ ኢላሀ ኢለላህ ገመድ ከዘርና ከቋንቋ በላይ ነው። ዛሬ ስለታመምን እንጂ ለሙስሊሙ አማራ ከነሷራው አማራ በላይ ሙስሊሙ ኦሮሞ ነው የሚቀርበው። ለሙስሊሙ ኦሮሞ ከነሷራው ኦሮሞ በላይ ሙስሊሙ አማራ ነው የሚቀርበው። በጠጣነው ፖለቲካዊ መርዝ ሳቢያ ቢተናንቀንም እውነታው ያ ነው። በዘር ቢሆን ለውዱ ነብያችን ﷺ ከሐበሻው ቢላል በላይ አጎታቸው አቡ ለሃብ በስጋ ይቀርባቸው ነበር። ኢስላማዊው መለኪያ ግን ሌላ ነው። ኢማንና ዘር እኩል ሚዛን ላይ አይቀመጡምና።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 27/1445፣ (ታህሳስ ዐ1/2016))

=

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#አንቺ-ሀገር-እንዴት-ነሽ

*******

{ፅናት ከፊት ሰልፍ ቀዳሚ አድርጎ ያላሰለፈው ሰው፤ ስንፍና ከመጨረሻ ሰልፍ ላይ ያሰልፈዋል }

መልካም ቀን

#ህዳር-16-2016

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group

🛍ጀግኖችን እንተዋወቅ🛍

<===========>

إشتهر كثير من العلماء بغير اسمهم الأول، ولايعرف كثير من الناس اسمهم الصريح، ومنهم 

አብዛኞቹ የኢስላም ዑለማወች እና ሊቆች ከመጀመሪያ ስማቸው ውጭ በሆነ መጠሪያቸው ነው የሚታወቁት አብዛኛው ሰው ትክክለኛ ስማቸውን አያውቀውም።

<======================>

ከነዚህ የኢስላም ፈርጦች መካከል የተወሰኑትን እነሆ ላስተዋውቃችሁ፡–

 

(١)‏➖ابن تيمية :  أحمد بن عبدالحليم  .

①➖🌺ኢብኑ ተይምያ=> አህመድ ኢብኑ አብደል ሀሊም

(٢)‏ا➖بن القيم  :  محمد بن أبي بكر  .

②➖🌺ኢብኑል ቀይም=> ሙሀመድ ኢብኑ አቢ በክር

(٣)‏➖ابن رجب   :  عبدالرحمن بن أحمد.

③➖🌺ኢብኑ ረጀብ =>አብደረህማን ኢብኑ አህመድ

(٤)‏➖ابن حزم   :  علي بن أحمد.

④➖🌺ኢብኑ ሀዝም=> አልይ ኢብኑ አህመድ

(٥)‏➖ابن حجر   :  أحمد بن علي.

⑤➖🌺ኢብኑ ሀጀር => አህመድ ኢብኑ አልይ

(٦)‏➖ابن كثير   :  إسماعيل بن عمر  .

⑥➖🌺ኢብኑ ከሲር =>ኢስማዒል ኢብኑ ዑመር

(٧)‏➖ابن الجوزي:  عبدالرحمن بن علي  .

⑦➖🌺ኢብኑል ጀውዚ=> አብደረህማን ኢብኑ አልይ

(٨)➖البخاري     :  محمد بن إسماعيل  .

⑧➖🌺ቡኻሪ => ሙሀመድ ኢብኑ ኢስማዒል

(٩)‏➖أبو داود     :  سليمان بن الأشعث  .

⑨➖🌺አቡ ዳውድ=> ሱለይማን ኢብኑ አሽዐስ

(١٠)‏➖الترمذي    :  محمد بن عيسى  .

(①0🌺➖ቲርሚዚይ=> ሙሀመድ ኢብኑ ዒሳ

(١١)‏➖النسائي    :  أحمد بن شعيب  .

(11)🌺➖ነሳዒይ => አህመድ ኢብኑ ሹዐይብ

(١٢)‏➖ابن ماجه  :  محمد بن يزيد  .

(12)🌺➖ኢብኑ ማጀህ=> ሙሀመድ ዒብኑ የዚድ

(١٣)‏➖أبوحنيفة :  النعمان بن ثابت  .

(13)🌺➖አቡ ሀኒፋ => ኑዕማን ኢብን ሣቢት

(١٤)‏➖الشافعي    :  محمد بن إدريس  .

(14)🌺➖ሻፍዕይ=> ሙሀመድ ኢብኑ ኢድሪስ

(١٥)‏➖الذهبي     :  محمد بن أحمد  .

(15)🌺➖ዘሀቢይ=> ሙሀመድ ዒብኑ አህመድ

(١٦)‏➖القرطبي   :  محمد بن أحمد  .

(16)🌺➖ቁርጡብይ=> ሙሀመድ ኢብኑ አህመድ 

(١٧)➖الصنعاني  :محمد بن اسماعيل

(17)🌺➖ሶነዐኒይ=> ሙሀመድ ኢብኑ ኢስማዒል

(١٨)➖الشوكاني  :محمد بن علي ‏

(18)🌺➖ሸውካኒይ=> ሙሀመድ ኢብኑ አልይ

(١٩)➖السيوطي  :  عبدالرحمن بن أبي بكر

(19)🌺➖ሲዩጥይ=> አብደረህማን ኢብን አቢ በክር

<===========================>

رحمهم الله جميعا ورضي عنهم

ሁላቸውንም አላህ ይዘንላቸው አላህ ይውደዳቸው ጀነትንም ያጎናፅፋቸው አሚን።

https://t.me/deawaselefyah_behabesha

https://t.me/deawaselefyah_behabesha

Send as a message
Share on my page
Share in the group