Translation is not possible.
#8ቱ_የጀነት_በሮች
ነቢዩ (ﷺ) ስለ ጀነት በሮች ብዛት ሲናገሩ
«ጀነት ስምንት በሮች አሏት። አንደኛው አር-ረያን ሲሆን አጿሚዎች በቀር የሚገባበት የለም።» ብለዋል።
(ቡኻሪይ 3257/ ሙስሊም 1152)
በሌላ ሐዲሳቸው ደግሞ፦
«አንድ ሰው ለአላህ ብሎ ሁለት ነገሮችን ሰደቃ ቢሰጥ አላህ ጀነትን ግባ ይለዋል። እንዲሁ ሶላትን የሚሰግዱ በሶላት በር ግቡ ይባላሉ። በጂሐድ የተሳተፉ በጂሐድ በር ግቡ ይባላሉ። ሰደቃ የሰጡ በሰደቃ በር ግቡ ይባላሉ። ፆም የፆሙ በአር-ረያን በር ግቡ ይባላሉ።» አሉ። አቡበክር ሲዲቅም «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በሁሉም በር እንዲገባ የሚጠራ ይኖራልን?» አሏቸው። ነቢዩም (ﷺ) «አወ! አንዱ አንተ እንደምትሆን ተስፋ አደርጋለሁ።» አሉ።»
(ቡኻሪይ 1897/ ሙስሊም 1027)
ዑለማዎች ከእነዚህ ሌሎች ሰነዶች በመነሳት የስምንቱን በር ስሞች ያስቀመጡ ሲሆን እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦
❶ ባብ አስ-ሶላት
♦️ ሰጋጆች የሚገቡበት
❷ ባብ አል-ጂሐድ
♦️ በጂሐድ የተሳተፉ የሚገቡበት
❸ ባብ አስ-ሰደቃህ
♦️ ሰደቃ የሰጡ የሚገቡበት
❹ ባብ አር-ረያን
♦️ ጿሚዎች የሚገቡበት
❺ ባብ አል-ሐጅ
♦️ ሐጂ ያደረጉ የሚገቡበት
❻ ባብ አል-ኢማን
♦️ ፅኑ ኢማን ያላቸው የሚገቡበት
❼ ባብ አል-ካዚሚን አል-ገይዝ
♦️ ቁጣቸውን የሚቆጣጠሩና ይቅር ባዮች የሚገቡበት
❽ ባብ አዝ-ዚክር
♦️ ዚክር የሚያበዙ የሚገቡበት
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group