UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

የነብዩ ﷺ ሚስቶች - ረዲየላ፞ሁ ዐንሁን።

1. ዓኢሻ ቢንት አቢ በክር

2. ሰውዳህ ቢንት ዘምዐህ

3. መይሙና ቢንቲል ሐሪስ

4. ዘይነብ ቢንት ኹዘይማህ

5. ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ

6. ዘይነብ ቢንት ጀህሽ አልሂላሊያ

7. ሐፍሷ ቢንት ዑመር ብኒል ኸጧብ

8. ሶፊያህ ቢንት ሑየይ ብኒ አኽጦብ

9. ጁወይሪያ ቢንቲል ሐሪሥ አልኹዛዒያ

10. ኡሙ ሰለማህ ሂንድ ቢንት አቢ ኡመያ

11. ኡሙ ሐቢባህ ረምላ ቢንት አቢ ሱፊያን

https://t.me/MOhamedAljawi

Telegram: Contact @MOhamedAljawi

Telegram: Contact @MOhamedAljawi

على مِنهاجِ النُّبوَّة
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሰዎች እንደ ሚሉት ባለቤቴን እወዳታለሁ ብቻ አትበል። ወደሀት፣ ተንከባክበሃት ፣ ደግፈሃት ቃልህን ተግባራዊ አድርገህ ተገኝ።

≈ሚስትህ የኢማንህ ግማሽ ተደርጋለች ፣ #የጎንክማረፊያናት፣ የልብክ መስከኛ ናት፣ የአይንህ ከለላ ናት፣ የስሜትህ መርኪያ ናት፣ እራስህ በረካህበት ስሜት አላህ ሀጅርን ያጎናፀፍሀል፣ዱኒያ ከያዘችው መልካም ነገር አንዷ ሴት ናት ፣ ወደ ጀነት መቃረቢያህ ናት፣ የልጆችህ እናት ናት።

፨ ባጠቀላይ ሚስትህ ከሃራም መጠበቂያህ ናት!

ሚስትህ የውስጥ ልብስህ ናት ፣

የደስታህ ምንጭ ናት ፣ #ፍቅርያስፈልጋታልናተንከባከባት!!

ባሎች ሆይ!

ሁላችሁም እራሳችሁን ጠይቁ!! እውነት የሚስታችሁን ሀቅ እየተወጣችሁ ነው???

አላህ ለእኛም በስራችን ዝናን ሳይሆን ኢኽላስ ይስጠን!! ለቤተሰባችን መልካም ያድርገን፤ ላላገቡ መልካም ትዳርን ላገቡም አላህ የሚወደውን መልካም ህይወት ይለግሳቸው!!

#gaza #palestine #freepalestine #quran

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሰዎች እንደ ሚሉት ባለቤቴን እወዳታለሁ ብቻ አትበል። ወደሀት፣ ተንከባክበሃት ፣ ደግፈሃት ቃልህን ተግባራዊ አድርገህ ተገኝ።

≈ሚስትህ የኢማንህ ግማሽ ተደርጋለች ፣ #የጎንክማረፊያናት፣ የልብክ መስከኛ ናት፣ የአይንህ ከለላ ናት፣ የስሜትህ መርኪያ ናት፣ እራስህ በረካህበት ስሜት አላህ ሀጅርን ያጎናፀፍሀል፣ዱኒያ ከያዘችው መልካም ነገር አንዷ ሴት ናት ፣ ወደ ጀነት መቃረቢያህ ናት፣ የልጆችህ እናት ናት።

፨ ባጠቀላይ ሚስትህ ከሃራም መጠበቂያህ ናት!

ሚስትህ የውስጥ ልብስህ ናት ፣

የደስታህ ምንጭ ናት ፣ #ፍቅርያስፈልጋታልናተንከባከባት!!

ባሎች ሆይ!

ሁላችሁም እራሳችሁን ጠይቁ!! እውነት የሚስታችሁን ሀቅ እየተወጣችሁ ነው???

አላህ ለእኛም በስራችን ዝናን ሳይሆን ኢኽላስ ይስጠን!! ለቤተሰባችን መልካም ያድርገን፤ ላላገቡ መልካም ትዳርን ላገቡም አላህ የሚወደውን መልካም ህይወት ይለግሳቸው!!

#gaza #palestine #freepalestine #quran

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد فى الاولين والاخرين ﷺ 🤲🤲

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#ልዩ_ልዩ_አጀንዳዎችና_ጣፋጭ_መልዕክቶች

#ክፍል_1

#ሐዲሥ 370 / 1080

ነዋስ ኢብኑ ሰምዓን እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋ፤፦ የአላህ መልዕክተኛ አንድ ቀን ጠዋት ድምጻቸውን ከፍና ዝቅ እያደረጉ ከተምር ዛፎች መሐል (ከአጠገባችን) ያለ መስሎ እስኪሰማን ስለ ደጃል ተረኩ። ተመልሰን በሔድን ጊዜ ይህን ስሜታችንን ተረዱ። \"ምን ሆናችሁ?\" አሉን። \"የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ጠዋት ስለ ደጃል አውስተውልን ነበር። ድምጽዎትን ከፍና ዝቅ እያደረጉ ሲናገሩ ከተምር ዛፎች መሐል (ከአጠገባችን) ያለ ያህል ተሰማን።\" አልናቸው። እንዲህ አሉን፦ \"ይበልጥ የምፈራላችሁ ደጃልን ሳይሆን ሌሎች ነገሮችን ነው። እኔ በሕይወት እያለሁ ከመጣ እናንተን ወክዬ ራሴው እሟገተዋለሁ። እኔ ከእናንተ በሌለሁበት ዘመን ከመጣ ግን እያንዳንዱ ሰው ስለ ራሱ ይሟገታል። አላህ እያንዳንዱን ሙስሊም ስለኔ ሆኖ ይጠብቀዋል። ደጃል ፀጉሩ የተቋጠረ ወጣት ነው። ዓይኑ ወጣ ወጣ ያለ ነው። ዐብዱልዑዝዛ ኢብኑ ቀጠን በተባለው ሰው እመስለዋለሁ (እርሱን ይመስላል)። ከመካከላችሁ እርሱን ያገኘ የአል ከህፍ ምዕራፍ መግቢያዎችን ይቅራበት። በሻምና በዒራቅ መካከል ባለ ቦታ ላይ ነው የሚመጣው። በስተቀኝም በስተግራም ብክለትን ያስፋፋል። የአላህ ባሮች ሆይ! ጽኑ።\" እኛም፦ \"የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ምድር ላይ ምን ያህል ጊዜ ይቆያል?\" አልናቸው። \"አርባ ቀናት ይቆያል። አንድ ቀን እንደ አንድ ዓመት፣ አንድ ቀን እንደ አንድ ወርና አንድ ቀን ደግሞ እንደ አንድ ሳምንት። ቀሪዎቹ ቀናት የተለመዱ ዓይነት ቀኖች ይሆናሉ\" አሉ። \"የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በዚያ እንደ ዓመት በሚሆነው ቀን የአንድ ቀን ሶላት ይበቃናልን?\" አልናቸው። \"አይበቃችሁም፣ ግና ጊዜውን እየገመታችሁ ስገዱ\" አሉን። \"የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ምድር ላይ ምን ያህል ይፈጥናል?\" አልናቸው። \"አፈጣጠኑ ነፋስ እንደተከተለው ዝናብ ነው። ከሰዎች ዘንድ ይመጣና ጥሪ ያደርግላቸዋል። በርሱ ያምናሉ። ይቀበሉታልም። ሰማይን ያዝዛትና ታዘንባለች። ምድርም ታበቅላለች። እንስሳዎቻቸው ጋቶቻቸው ሞልተውና ጠግበው ይመለሳሉ። ከሌሎች ሰዎች ዘንድ ይሔድና ጥሪ ያደርግላቸዋል። ንግግሩን ሳይቀበሉት ይቀራሉ። እርሱም ጥሏቸው ይሔዳል። ወዲያውም ድርቅ ይመታቸዋል። ከእጃቸው ላይ የምቀር ሃብት አይኖራቸውም። በሞተች ምድር አጠገብ ያልፍና \'ድልብሽን አውጭ\' ሲል ያዝዛታል። ድልቧን እንደንብ አውራ ታግተለትልለታለች። አንድን ወጣት ይጠራውና በሰይፍ በመምታት ከሁለት ይበጥሰዋል። ከዚያም ይጠራዋል። ፊቱ በሳቅ ተሞልቶ ጥሪውን በመቀበል ይመጣል።በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ አላህ የመርየምን ልጅ አልመሲሒን ያስነሳዋል። በደማስቆ በስተምስራቅ በኩል ከአንድ ነጭ ሚናራዎች ላይ ሁለት ያማሩ አልባሳት ተጎናጽፎና መዳፎቹን ከመላእክት ክንፍ ላይ አሳርፎ ይወርዳል። አንገቱን ሲደፋ ውሃ ከርሱ ይንጠባጠባል። ቀና ሲያደርገውም ልክ እንደ ሉል ሆኖ እየተንኳለለ ይወርዳል። ትንፋሹን ያሸተተ ከሐዲ ሁሉ ወዲያውም ይሞታል። ትንፋሹ ዓይኑ እስከሚያየው ክልል ድረስ ይደርሳል። ዒሳ ደጃልን ያሳድደዋል። \"ሉድ\" ከተባለው በር ላይ ያገኘውና ይገድለዋል። ከዚያም የመርየም ልጅ ዒሳ አላህ ከደጃል ፈተና ከጠበቃቸው ሰዎች ዘንድ ይመጣል። ፊታቸውንም ያብሳል። ጀነት ውስጥ ያላቸውን ደረጃም ይነግራቸዋል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ አላህ እንዲህ የሚል መልዕክት ያስተላልፍለታል። አንድም ሰው ሊዋጋቸው የማይደፍር ባሮቼን አውጥቻለሁና የኔን አገልጋዮች ወደ ጡር ጋራ ይዘሐቸው ዝለቅ።\" አላህ የእጁጅና መእጁጅ (ጎግ ማንጉግ) የተባሉ ፍጡራንን ያስነሳል። ከየከፍታ ቦታው ይወርዳሉ። የመጀመሪያው በጠበሪይያህ ሐይቅ አጠገብ ያልፋል። ከውስጡ ያለውን ውሃም ምጥጥ አድርጎ ይጠጣል። የመጨረሻዎቹ በሐይቁ አጠገብ ሲያልፉ፦ \"ከዚህ ቦታ ላይ ውሃ ነበረበት\" በማለት (እንደታሪክ) እስኪያስቡት ድረስ ውሃው ይደርቃል። የአላህ ነቢይ ዒሳ እና ባልንጀሮቻቸው ይከበባሉ። ያንዬ ለነርሱ የአንድ በሬ ራስ ዛሬ ለናንተ መቶ ዲናር ከሚኖረው የበለጠ ዋጋ ይኖረዋል። ዒሳና ባልንጀሮቹ አላህን ይማጸናሉ። አላህም አንገቶቻቸውን የምነድፉ ትሎች (ተባዮችን) ይልክባቸዋል። ሁሉም እንደ አንድ ሰው ይሞታሉ።ከዚያም የአላህ ነቢይ አሥር ባልንጀሮቻቸው ወደ መሬት ይወርዳሉ። ስፍራው ሁሉ ስንዝር ቦታ ሳይቀር በነርሱ ጥንብና መጥፎ ሽታ ተሞልቶ ያገኙታል። የአላህ ነቢይ ዒሳ እና አሥር ባልንጀሮቻቸው አላህን ይማጸናሉ። አላህም የግመል አንገት የመሰሉ በራሪዎችን ይልካል። እነዚህ በራሪዎች ሬሳዎቻቸውን እያነሱ አላህ ከሻው ቦታ ላይ ይጥሉታል። ከዚያም አላህ ዝናብ ይልካል። ይህ ዝናብ አንድም ቤት ሳይቀር ሁሉንም ያደርሳል። ምድርንም ልክ እንደ መስታወት እስክትጸዳ ድረስ ያነጣል። ከዚያም ምድር፦ \"አትክልቶችሽን አብቅይ። በረከትሽንም መልሺ\" ትባላለች። በዚህ ጊዜ ሁሉም ሮማን ይመገባሉ። በቆዳዋም ይጠለላሉ። ወተቱም ይበረክታል። የምትታለብ ግመል ለብዙ ሰዎች የሚበቃ ወተት ትሰጣለች። የምትታለብ ላም ለአንድ ጎሣ የሚበቃ ወተት ትሰጣለች። የምትትታለብ ፍየል ለአንድ ነገድ የሚበቃ ወተት ትሰጣለች። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ አላህ በጎ ነፋስ ያስነሳል። ከብብታቸውም ሥርም ታጠቃቸዋለች። የአማኞቹን ነፍስም ታወጣለች። ልክ እንደ አህያ በአደባባይ ወሲብ የሚፈጽሙ እኩይ ሰዎች ብቻ ይቀራሉ። በነርሱ ላይ ትንሳኤ ትቆማለች (ትከሰታለች)።\" (ሙስሊም)

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group