UMMA TOKEN INVESTOR

About me

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

Translation is not possible.

የሱብሒ አዛን!

• ከሌሎች የሶላት አዛኖች በተለየ መልኩ በሱብሒ አዛን ላይ የምትጨመር ቃል አለች፡፡ «አሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም» ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፡፡― የምትል፡፡ አዎን ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፡፡

▶እንቅልፍ የሥጋ ጥሪ ነው፤ ደከመኝ አሳርፉኝ ይላል። ሶላት የአላህ ጥሪ ነው፡፡ አላህ ወደኔ ኑ እረፉ ይለናል፡፡

▶ እንቅልፍ ሞት ነው፤ ሶላት ደግሞ ሕይወት፡፡ በሶላትህ ነፍስ ዝራ፣ ከነፍስህ ጌታ ጋር ተገናኝ፡፡

▶ እንቅልፍን አካልን ያሳርፋል፤ ሶላት ግን ቀልብን ያረጋጋል፣ መንፈስን ያሰክናል፡፡

▶ ሶላት የአማኞች መለያ ናት፤ ጌታ እንደሌለው ባሪያ ያለ ሀሳብ ዥው ብለህ አትተኛ፡፡ ተለይተህ ተነሳ፡፡

▶ እንቅልፍ ሲበዛ ያሰንፋል፣ ለድካምም ለዱካክም ያጋልጣል፡፡ተነስቶ መስገድ ንቃትን ይሠጣል፣ አካልን ያፍታታል፣ ፊትን ያበራል፣ ወዝን ይመልሳል፡፡

▶ የማለዳ አየር የተለየና ፀጥ ያለ ነው፡፡ ለዒባዳም፣ ሀሳብን አሰባስቦ አላህን ለመማፀንም ምቹ ነው፡፡

▶ በሶላት የተከፈተ ቀን ድል አለው፣ በረከትና ስኬት አለው፡፡

▶ ሱብሒ ላይ የሚተኛ የሸይጣን ምርኮኛ ነው፤ ለሸይጧን ጆሮ የሠጠ ነው፡፡ አልነጋም ተኛ ይለዋል፡፡

የሱብሒ ጊዜ እንዴት ያማረ ጊዜና ዉብ ሰዓት መሠላችሁ!

☞ የሱብሒ ሶላት ሱንናው በዱንያ እና በዉስጡ ካሉ ነገሮች ሁሉ በላጭ ነው፡፡

☞ የሱብሒ ሶላት ግዴታው የአላህን ጥበቃና ዋስትና ያስገኛል፡፡

በርግጥም «አሶላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም\'ን» እየሰሙ «ሐይየ ዐላ ሶላህ፣ ሐይየ ዐለል ፈላሕ\'ን» እያዳመጡ መተኛት ይከብዳል።

ወዳጆቼ ለይል ቢያቅተን አሁን ላይ ሆነን ሱብሒን ብናስብ ምን ይለናል!?

=t.me/Sle_qelbachn1

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የሰዎችን ሐጃ መፈፀም ምን ያህል የላቀ አጅር አለው?

~

የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

\"ከወንድሜ ጋር በሆነ ጉዳይ ላይ (ሐጃውን ልፈፅምለት) ብንቀሳቀስ ለኔ በዚህ መስጂድ (የመዲናው መስጂድ) አንድ ወር ኢዕቲካፍ ከማድረግ ይልቅ ይበልጥ የተወደደ ነው።\" አሶሒሐህ፡ 906]

=

የቴሌግራም ቻናል:-

https://t.me/IbnuMunewor

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

~ወዳጆቼ ምሽታችሁ የቀናችሁ መጨረሻ መሆኑን ልብ በሉ። ይህ ምሽት የቀናችሁ መጨረሻ እንደሆነ ሁሉ የዕድሜያችሁ መጨረሻም ሊሆን ይችላልና አስተውሉ።

ሰለዚህ  ቀናችሁን በመልካም ነገር አሳርጉ፤ ፋይላችሁን በጥሩ ነገር ዝጉ። ዐይናችሁን ከመጥፎ ፊልምና ምስል ተጠንቀቁለት። የወንጀል ተፅእኖው እጅግ ከባድ ነው።ከሚታይ ነገርም የዐይንን ዕድሜ የሚያሳጥር፣ እይታዋን የሚያደበዝዝ አለ። አሲድ የተደፋበትን ልብስና ሰውነት እንደሚበጣጥሰው ሁሉ መጥፎ ማየትም ኢማንን ይበጣጥሳል።ጆሯችሁንም ከመጥፎ ነገር፣ ከሙዚቃና ከምሽት ፆታዊ የስልክ ወሬ ተጠንቀቁለት። ከንግግርም ልብን የሚያፈስ፣ አካልን የሚያዝል፣ ከጆሮ አልፎ ልብ ላይ የሚታተም አለ።እጃችሁንም ለመጥፎ ቻት አትጠቀሙበት። ከቻትም ልብን ዘልቆ የሚሰረስር፤ ኢማንን የሚሸረሽር አለ።

ሰው በኖረበት ነገር ላይ ይሞታል። በሞተበት ሁኔታ ላይ ይቀሰቀሳልና ፈፅሞ ወንጀልን በዐይናችን፣ በጆሯችን፣ በእጃችን ... ይዘን እንዳንተኛ። ከመተኛት በፊት አካላዊም ሆነ መንፈሳዊ ንፅህና ግድ ነው። ካልሆነ ፀፀቱ እጅግ ከባድ ነው።

=t.me/AbuSufiyan_Albenan

Send as a message
Share on my page
Share in the group

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group