UMMA TOKEN INVESTOR

3 day Translate
Translation is not possible.
#የበጐ #ተግባራት #መንገዶች #በርካታ #ስለመሆናቸው
#ክፍል_14
#ሐዲሥ 13 / 130
የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ተከታዩን መናገራቸውን አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) አስተላልፈዋል፦ “አምስት ወቅት ሶላቶች፥ ከጁሙዐህ እስከ ጁሙዐህ፥ ከአንዱ ረመዷን እስከ ሌላኛው ረመዷን በመካከላቸው ለሚፈጸሙ (ጥቃቅን) ወንጀሎች ማበሻዎች ናቸው፤ ታላላቅ ወንጀሎች እስካልተፈጸሙ ድረስ።” (ቡኻሪ ዘግበውታል)
ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር
፨ እነኝህን ግዳጆች በአግባቡ መፈጸም ለጥቃቅን ወንጀሎች መሰረይ ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ በአላህ እዝነት (ረሕመት) እና ትሩፋት፡፡ ሰውየው ታላላቅ ወንጀሎችን ካልፈጸመ ከወንጀል የጸዳ ይሆናል። ታላላቅና ታናናሽ ወንጀሎችን የፈጸመ ከሆነ ግን በታላላቅ ወንጀሎች ብቻ ይጠየቃል። ታላላቅ ወንጀሎችንም ቢሆን አላህ ያቀልለታል ተብሎም ይታሰባል። ግን እውነተኛ ተውበት የግድ አስፈላጊው ነው።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
4 day Translate
Translation is not possible.
#የበጐ #ተግባራት #መንገዶች #በርካታ #ስለመሆናቸው
#ክፍል_13
#ሐዲሥ 13 / 129
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕከትኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፦ “አንድ ሙስሊም ወይም ሙእሚን ውዱእ በሚያደርግበት ወቅት ፊቱን ሲታጠብ በዓይን የፈጸመውን ወንጀል ሁሉ በፊቱ ላይ ከውሃው ወይም ከመጨረሻው የውሃው ምልስታ እንጥፍጣፊ ጋር ይወገድለታል። እጁን ሲታጠብ እጆቹ በመጨበጥ የፈጸሟቸው ወንጀሎች ሁሉ ከውሃው ወይም ከመጨረሻው የውሃው እንጥፍጣፊ ጋር ይወገዳሉ። እግሩን በሚታጠብበት ወቅት እግሮቹ የሄዷቸው ወንጀሎች ሁሉ ከውሃው ወይም ከመጨረሻው የውሃው እንጥፍጣፊ ጋር ከእግሮቹ ይወገዳሉ፤ (ከዚህች ዓለም) ከወንጀል የጸዳ ሆኖ እስኪወጣ ድረስ።” (ሙስሊም ዘግበውታል)
ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር
፨ የውዱእ ትሩፋት፤ አዘውትሮ ውዱእ ማድረግ ከወንጀል ለመጽዳት ሰበብ ነው። ይህ የአላህን የላቀ ትሩፋት ያሳያል።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
5 days Translate
Translation is not possible.
#የበጐ #ተግባራት #መንገዶች #በርካታ #ስለመሆናቸው
#ክፍል_12
#ሐዲሥ 13 / 128
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕከተኛ (ሶ.ዐ.ወ)፦ “በተሟላ ሁኔታ ዉዱእ ያደረገ፥ ከዚያም ወደ ጁሙዐህ ሶላት የመጣና (የሚነገረውን) በፀጥታ ያደመጠ በሁለቱ ጁሙዓዎች መካከልና የተጨማሪ ሦሥት ቀናት ወንጀሎቹ ይማሩለታል። ጠጠር የነካካ፥ (ለሚነገረው ነገር ሙሉ ትኩረት ያልሰጠ) ረብ የለሽ ተግባር ፈጽሟል።” (ሙስሊም ዘግበውታል)
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
→ ዉዱእን በተሟላ መልኩ መፈጸምና ጁሙዐን ወቅቱን ጠብቆ መስገድ የሚያስገኘው ትሩፋት።
1/ የጁሙዐህ ሶላት እያንዳንዱ ለአቅመ-አዳም በደረሰ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። መስጊድ ውስጥ በጀማዓ እንጅ አይሰገድም።
2/ ጁሙዐ ሶላት የአስር ቀናት ጥቃቅን ወንጀሎችን ያስምራል።
3/ በጁሙዐ ሶላት ወቅት ኹጥባ በሚነገርበት ሰዓት በፀጥታ ማዳመጥ ግዲታ (ዋጂብ) ነው።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
6 days Translate
Translation is not possible.
#የበጐ #ተግባራት #መንገዶች #በርካታ #ስለመሆናቸው
#ክፍል_11
አላህ እንዲህ ብሏል፦
"...ከበጐ ሥራ የምትሠሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል፤..." አል በቀራህ፡ 197"
#ሐዲሥ 13 / 127
ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ተከታዩን መናገራቸውን አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) አስተላልፈዋል፦ “መንገድ ላይ ሙስሊሞችን ያስቸግር የነበረን ዛፍ በመቁረጡ ሰበብ ጀንነት ውስጥ ሲዘዋወር አንድን ሰውዬ ተመልክቻለሁ።” (ሙስሊም ዘግበውታል)
በሌላ ዘገባ ደግሞ፦
“አንድ ሰው መንገድ ላይ በነበረ አንድ የዛፍ ዝንጣፊ አጠገብ አለፈ። “በአላህ ይሁንብኝ! ይህንን ሙስሊሞችን እንዳያስቸግር አስወግደዋለሁ” አለ። (በዚሁ ድርጊቱ) ጀንነት እንዲገባ ተደረገ” የሚል ተወስቷል።
በሌላ የሐዲስ ዘገባ እንደተወሳው፦
“ሰውየው በአንድ መንገድ በመጓዝ ላይ እያለ የሾህ ዝንጣፊ ያገኛል። ከመንገዱ ያስወግዳዋል። አላህ ይህንኑ መልካም ተግባሩን ተቀበለው። ምህረትንም ለገሰው።”
ከሐዲሡ የምንማረው ቁምነገር
፨ ከመንገድ ላይ ሰዎችን የሚያውክን ነገር የማስወገድ ትሩፋት፤ ሙስሊሞችን የሚጠቅምና ከጉዳት የሚከላከልን ተግባር የመከወን ጠቀሜታ።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
7 days Translate
Translation is not possible.
#የበጐ #ተግባራት #መንገዶች #በርካታ #ስለመሆናቸው
#ክፍል_10
#ሐዲሥ 13 / 126
አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ፦ "አንድ ሰው በጉዞ ላይ እያለ ጥም ያቃጥለዋል። የውሃ ጉድጓድ አገኘና ከውስጡ ገብቶ ጠጣ። ከጉድጓድ ሲወጣ የሚያለከልክ ውሻ ተመለከተ። ከደረሰበት የውሃ ጥም ብርታት የተነሳ እርጥብ አፈር ይልሳል። "እኔን ያጋጠመኝ ዓይነት የውሃ ጥም ይህንንም ውሻ አጋጥሞታል" በማለት አሰበ። ወደ ጉድጓዱ በመውረድ ጫማውን ውሃ ሞላው። በአፉ ይዞ ወደ ላይ ዘለቀ። ለውሻውም አጠጣው። አላህ ይህን ጽድቅ ተግባሩን ተቀበለው። ምሕረትንም አደረገለት" በማለት ተናገሩ። "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ለእንስሳት ጽድቅ በመፈጸም ምንዳ እናገኛለን ?" ሲሉ ጠየቋቸው። "እርጥብ በሆነች (በሕያውያን) ሆድ ሁሉ ምንዳ ይገኛል" በማለት መለሱ። (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
በቡኻሪና ዘገባ ላይ፦ "አላህ መልካም አድራጐቱን ተቀበለለት። ምሕረት አደረገለት። ጀንነትም አስገባው" የሚል ተወስቷል።
በሌላ የቡኻሪና ሙስሊም ዘገባ ላይ ደግሞ፦ "ውሻው ጥም ሊገለው ቀረበ። ጉድጓዱን በመዞር ላይ እያለ ከበኒ ኢስራኢል ሴተኛ አዳሪዎች አንዷ ተመለከተችው። ጫማውን አውልቃ ውሃ በመቅዳት ለውሻው አጠጣችው። ምሕረት ተደረላት" የሚል ተወስቷል።
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ ሕይወት ላላቸው ነገሮች በጐ የመዋል ጠቀሜታ። የአላህን ምንዳ ከሚያስገኙና ምሕረቱንም ለመጐናጸፍ ከሚያስችሉ መልካም ተግባራት ውስጥ የሚካተት ነው።
2/ ውሃን የማጠጣት ትሩፋት፤ በተለይም ከራስና ከቤተሰብ መሠረት ፍላጐቶች የተረፈ ሆኖ ከተገኘ ለሚፈልጉት ፍጡራን መስጠት ግዴታ ይሆናል። ወደ አላህ ለመቃረብ ከሚያስችሉ ተግባራትም አንዱ ነው።
3/ የአላህ እዝነት (ረሕመት) በአነስተኛ ተግባር ታላቅ ወንጀልን ይምራል።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group