«እኔ ገና ነኝ…»
~በዲናችን ውስጥ «ተዋዱዕ» (መተናነስ) እጅግ የተወደደ እና የላቀ ምግባር ነው። ነቢዩ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) «ለአላህ ብሎ የተናነሰን ሰው አላህ ከፍ ያደርገዋል» ብለዋል። ነገር ግን በዘመናችን በአንዳንድ መድረኮች እና የዳዕዋ ፕሮግራሞች ላይ የምንታዘበው ነገር አለ። እርሱም መተናነስ የመሰለ ነገር ግን ሲደጋገምና ከልክ ሲያልፍ «እኔን አክብሩኝ» ወይም «እኔን ከፍ አድርጉኝ» የሚል ድብቅ መልዕክት ያለው የሚመስል አካሄድ ነው።
🎤 አንድ ወንድም ወይም ኡስታዝ መድረክ ላይ እንዲናገር ከተጋበዘ፣ አዘጋጆቹ በቦታው የመረጡት የሚናገረው ነገር ይጠቅማል ብለው አምነውበት ነው። ነገር ግን ተናጋሪው ማይኩን እንደጨበጠ፡- «እኔ ለዚህ ቦታ የምገባ አይደለሁም»፣ «እዚህ ጋ ሸይኽ እከሌ እያሉ እኔ መናገሬ ስህተት ነው»፣ «እኔ ገና ተማሪ ነኝ»፣ «መሃይሙ ወንድማችሁ»... እያለ ብዙ ደቂቃዎችን ይፈጃል።
ይህ አድማጭን ማሰልቸቱ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ዋናው ቁምነገር ለመግባት እንቅፋት ይሆናል። ስለ ራስ መሃይምነት የሚወራው ወሬ ከዋናው ትምህርት ሲበልጥ ነገሩ ከአደብ ይወጣል። እውነተኛ አደብ የተሰጠንን አደራ በአግባቡ መወጣት እንጂ፣ ራስን በማራከስ ጊዜን ማቃጠል አይደለም።
✅️አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉት፣ሌሎች ሰዎች እንዲያስተባብሉላቸው እና እንዲያሞግሷቸው ፈልገው ሊሆን ይችላል።ለምሳሌ አንድ ሰው «እኔ እኮ ደካማ ነኝ፣ ምንም እውቀት የለኝም»ሲል፣ አድማጮች በውስጣቸው ወይም በአደባባይ «ኧረ እንደውም አንተ እኮ ትልቅ አዋቂ ነህ፣ ማንም የማይችለውን ችለሃል»እንዲሉለት የሚፈልግበት ሁኔታ አለ።
📚ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ረጀብ አል-ሀንበሊ (ረሂመሁላህ) “ዘም አል-ማል ወል-ጃህ” በተሰኘው ኪታባቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፡-
«وَمِنْهُمْ مَنْ يَذُمُّ نَفْسَهُ بَيْنَ النَّاسِ يُرِيدُ بِذَلِكَ أَنْ يَرَوْا تَوَاضُعَهُ، فَيَمْدَحُوهُ بِذَلِكَ، وَهَذَا مِنْ دَقَائِقِ أَبْوَابِ الرِّيَاءِ...»
«ከእነሱም (ከሰዎች) መካከል ሰዎች ትህትናውን ያዩለት ዘንድ በሰዎች ፊት ራሱን የሚወቅስ አለ፤ በዚህም ተግባሩ እንዲያሞግሱት ይፈልጋል። ይህ (ተግባር) ረቂቅ ከሆነ የይዩልኝ (ሪያ) በር ነው።»
📚እንዲሁም ከሰለፎች አንዱ የሆነው ሙጠሪፍ ኢብኑ ዐብዲላህ እንዲህ ይላል፡-
«كفى بالمرءِ تزكيةً لنفسِه أن يذمَّها على الملأ»
«አንድ ሰው በአደባባይ (በሰዎች ፊት) ራሱን መውቀሱ፤ ራሱን ከማጥራት ይበቃዋል።»
ማለትም፡- ሰዎች «እንዴ! እሱ እኮ እንዴት ያለ ትሁት ነው» ብለው እንዲያወድሱት መንገድ እየጠረገላቸው ስለሆነ ነው።
✔️በሌላ አባባል፣ ሰውየው ራሱን ዝቅ የሚያደርገው ሰዎች ከፍ እንዲያደርጉት ነው። ይህ ልብን መፈተሸ የሚያስፈልገው አደገኛ በሽታ ነው።
ምክንያቱም ራስን በአደባባይ ማራከስ፣ «እዩኝ እኔ እኮ ምን ያህል ትሁት (ሙተዋዲዕ) ነኝ» ብሎ እንደመናገር ስለሚቆጠር ነው።
☑እና ውድ ወንድሞቼ…
ትህትና ማለት ራስን መካድ ወይም ያለመቻልን መስበክ ማለት አይደለም። ትህትና ማለት ከአንተ በታች ካለ ሰውም ቢሆን እውነት ሲመጣ መቀበል ነው።ሰዎችን አለመናቅ። ሌሎችን ከራስ በታች አድርጎ አለማየት ነው።
🎤ስለዚህ ሁሌ በመድረክ ላይ ስንወጣ«እኔ ደካማ ነኝ»እያሉ ከማውራት ይልቅ፣ በልብ ወደ አላህ በመተማመን «አላህ ሆይ አንደበቴን ፍታ፣ እውቀትን ጨምርልኝ» ብሎ በዱዓ መጀመር።ከዛም በቀጥታ ወደ ተጠሩበት ርዕስ መግባት። አድማጩ የመጣው መልዕክት ሊሰማ እንጂ የተናጋሪውን የትህትና ደረጃ ለመለካት አይደለም።
✅️እውነትም ታላላቅ ዑለማዎች ባሉበት መድረክ ላይ የመናገር እድል ከተሰጠ፣ «እርሶ እያሉ መናገሬ ባይገባም፣ ባዘዙኝ መሰረት…»ብሎ በአጭሩ ማለፍ እንጂ፣ የረጅም ደቂቃ «እኔኮ አይገባኝም» ንግግር አያስፈልግም።በመድረክ ላይ የሚደረግ የተጋነነ ራስን ዝቅ የማድረግ ዘመቻ፣ ከትህትና ይልቅ ለሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ ሊሆን ስለሚችል መጠንቀቁ ይበጃል።
t.me/AbuSufiyan_Albenan

Comment
Share
Send as a message
Share on my page
Share in the group