Translation is not possible.

▫️ጃዕፈር ኢብን አቡጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁ

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

           ክፍል አንድ 1⃣

            ✿•••✿•••✿

《ጀዕፈርን፥ ጀነት ውስጥ ሁለት በደም የደመቀ ክንፎች ባለቤት ሆኖ አየሁት።》

       «🎤ነብዩ ሙሐመድ ﷺ»

ምንም እንኳን በቁረይሾች ታላቅ የክብር አይን ቢታዩም የረሱል ﷺ አጎት አቡ-ጧሊብ በሀብት ረገድ ድሀ ነበሩ።

ቤተሰባቸውን መቀለብ የተሳናቸው የብዙ ልጆች አባት የሆኑት አቡጧሊብ ምድረ ዓረቢያን ድርቅ ሲመታት ችግሩ ተባባሰባቸው። ሰብሎችን ያጠፋውና ከብቶችን የፈጀው ረሃብ፥ ህዝቡ ከሞት ለማምለጥ ሲል አጥንት እንዲቆረጥም አስገድዶት ነበር። ነብዩ ረሱል ﷺ ለነብይነት ገና ባልታጩበት በዚህ ቀውጢ ወቅት አጎታቸውን አባስን «የወንድምህ የአቡ-ጧሊብ ቤተሰቦች ብዙ ናቸው።   ሰው በረሃብ እያለቀ ስለሆነ የተወሰኑትን በመውሰድ እንርዳው»  በማለት ሀሳብ አቀረቡ።

   አባስም በሀሳቡ ተስማማ አባስ ከረሱል ﷺ ጋር ወደ አቡ ጧሊብ ሄደው ሀሳባቸውን አቀረቡ። አቡ ጧሊብ የዓሊይን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ታላቅን አቂልን ትተው ከሌሎቹ መርጠው መውሰድ እንደ ሚችሉ ነገሯቸው።

   ረሱል ﷺ #ዓሊይን ረ.ዐ  አባስ ደግሞ #ጃዕፈርን ረዲየሏሁ ዐንሁን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል ወሰዷቸው።

ከሃሺም ጎሳ #አምስት ሰወች ነብዩ ሙሀመድን ﷺ በመልክ በጣም ይመስሉ ነበር ይባላል።

    ያጎታቸው ልጆች #አቡሱፍያን ኢብን አል-ሃሪስና #ቁሳም ኢብን አል አባስ፤ የኢማሙ ሻፊኢይ አያት #አስ-ሳኢብ ኢብን ኡበይድ እንዲሁም ከሁሉም በጣም የሚመስሏቸው የልጃቸ ው ልጅ #ሐሰን ኢብን ዓሊይና የአጎታቸው ልጅ #ጀዕፈር ኢብን አቡ ጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁም ነበሩ።

   የትዳር እና የኢስላም ህይወት

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

   ጀዕፈር ረዲየሏሁ ዐንሁ በወጣት እድሜው #አስማ ቢንትዑመይስን ረዲየሏሁ ዐንሀ አግብቶ ከአባስ በመለየት ጎጆ መሰረተ። በአቡበክር አስ-ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ አማካኝነት ከሚስቱ ጋር ኢስላምን በመቀበል ከመጀመሪያወቹ ሙስሊሞች ሆነ። የጀነት መንገድ በሾክ መሞላቷን የተረዱት ጀዕፈርና ሚስቱ ረዲየሏሁ ዐንሁም በቁረይሽ የሚደርስባቸውን ጭካኔና ግፍ በትዕግስት ሊወጡት ቢሞክሩም ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ የመጣው የ ቁረይሽ ሴራ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ፦

«ጌታችን አላህ አንድ ነው» ስላሉ ብቻ በደል እየተፈፀመባቸው ያሉት ንፁሃን ሰዎች ዕጣ ያሳዘናቸው ነብይ ﷺ ወደ ሀበሻ እንዲሰደዱ ትዕዛዝ ሰጡ።

▫️     ስደት ወደ ሐበሻ  ▫️

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

  

🌹 ክፍል ሁለት ይቀጥላል🌹

https://t.me/UmuNuhBintdarsema

Telegram: Contact @UmuNuhBintdarsema

Telegram: Contact @UmuNuhBintdarsema

አስተያየትም ሆነ ስህተት ካለዎት ✍️?? @Haymanot_Darsema_Umu_Nuh
Send as a message
Share on my page
Share in the group
zahara mohammed Changed her profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
zahara mohammed Changed her profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
zahara mohammed Changed her profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group