#ሁለት_ሰዎች_ሦስተኛው_ሳይፈቅድ #መንሾካሾክ_አስፈላጊ_ካልሆነ_በቀር፣ #ማለትም_ምስጢር_ማውራት #ፈልገው_እንዳይሰማቸው #ካልፈለጉ_በቀር፣ #ስለመከልከሉ፥ #ሦስተኛው_ሰው_በማያውቀው #ቋንቋ_ማውጋትም #እንደዚሁ_ስለመሆኑ
#ክፍል_1
አላህ እንዲህ ብሏል፦
"(በመጥፎ) መንሾካሾክ ከሰይጣን ብቻ ነው።" (አል ሙጃደላህ፡ 10)
ሐዲሥ 281 / 1598
ኢብኑ ዑመር እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ "ሦስት ሰዎች አብረው ካሉ ሁለቱ ብቻቸውን ሦስተኛውን አግልለው አይንሾካሾኩ።" (ቡኻሪና ሙስሊም)
አቡ ዳውድ ባሰፈሩት ዘገባ አቡ ሷሊሕ እንዳሉት፥ ኢብኑ ዑመርን፦ "አራት ከሆኑስ?" በማለት ጠየቅኳቸው። "አይጎዳህም" አሉኝ።
ማሊክ "ሙወጠእ" በተሰኘ መጽሐፋቸው እንደ ጠቀሱት ዐብደላህ ኢብኑ ዲናር እንዲህ ብለዋል፦ "እኔና ኢብኑ ዑመር ገበያው መሐከል ካለው የኻሊድ ኢብኑ ዑቅባህ ቤት ሔድን። አንድ ሰው መጣና በሹክሹክታ ሊያናግራቸው ፈለገ። ከኢብኑ ዑመር ጋር ከኔ ውጭ ሌላ ሰው አልነበረም። ኢብኑ ዑመር ሌላ ሰው ጠሩና አራት ስንሆን ለኔና ለጠሩት ሰው እንዲህ አሉን፦ "ጥቂት ጊዜ ገለል በሉ። የአላህ መልዕክተኛ ፦ ሁለት ሰዎች ሦስተኛ ሰው አስቀምጠው አይንሾካሾኩ፤ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ።
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ ኢስላም እያንዳንዱን የሕይወት ክፍል ሥርዓት ለማስያዝና ለመምራት የሚያደርገውን ጥረት እናስተውላለን። ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ስሜታቸው እንዳይጎዳ እንዴት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብን እንኳ ያስተምረናል።
2/ ሦስት ሰዎች እያሉ አንዱን ነጥለው ሁለቱ ብቻ፣ አራት ከሆኑ ደግሞ አንዱን ነጥሎ ሦስቱ ብቻ ማንሾካሾካቸውና ምስጢር ማውራታቸው ተገቢ አይደለም። ክልክል ነው። ይህ ጥብቅ ድንጋጌ ሐላል ለሆኑና ለተፈቀዱ ምስጢራዊ ወሬዎች ሲሆን፥ ሐራም የሆነ መንሾካሾክ ግን ክልክልነቱ እጥፍ ይሆናል።
3/ ይህ ድርጊት ክልክል የሆነበት ምክንያት ሁለት ሰዎች ሦስተኛውን አግልለው በሚያንሾካሾኩበት ጊዜ እርሱ ብቻኝነት ሊሰማውና ሐዘንና ጥርጣሬ ሊገባው ስለሚችል ያን ለመከልከል ነው። ሌላ የሚያጫውተው ሰው ካለ ግን ይህ ስሜት አይፈጥርበትም። ኢብኑ ዑመር ያደረጉትም ይህንኑ ነው።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1