UMMA TOKEN INVESTOR

elham hussen shared a
Татарчага аудару мөмкин түгел.

አደራ አደራ ለፍሊስጤን ወንድሞቻችን በዱአ አንሰስትባቸው ያ ኡመተል ኢስላም👇

የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ዋኤል አል ዳህዱህ፡ አሁን ጋዛ እየደረሰባት ያለው የእስራኤል የቦምብ ጥቃት ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ነው ብሎዋል፣

አደራ አደራ አደራ ለወንድሞቻችን ሌላ ቢያቅተን ዱአእ ሊያቅተን አይገባም በዱአ አንሰስትባቸው የኛው ጅሀድና እገዛችን በዱአእ ላይ የተገነባ ይሁን ሀያ يلا لا تقنطو مين رحمةالله

آخوكم آبو ماحي Mk ነኝ የተማሙ👇

https://t.me/httsibnutemamAbumahi114

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
elham hussen shared a
7 ай Тәрҗемәсе
Татарчага аудару мөмкин түгел.

🔰 ባሮችህ ረገፉ

በፈለስጢን ምድር - በአላህ ቤት

በመስጂደል አቅሳ - ነብዩ ባረፉበት

በካኃዲዋ እስራኤል - ረገፉ ህፃናት

ቦምብ ዘነበባቸው - እንቅልፋቸውን በተኙበት

ዓለምም ችላ አለው - ይህን የዘር ማጥፋት

ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ

ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ

ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ

ሙስሊም የሆኑ - ኢባዱ ራህማን ናቸው

ሰው ናቸውና ያራሂም - ካጠፉም ማራቸው

መንገድ ስተው እንደሆን - መንገድ አሳያቸው

ሙስሊሞቹም ያንተ - ህፃኖች ያንተው

ካንተ ውጭ ሌላ መጠጊያም ዬላቸው!

አዎ ወጀለኞች ነን - ነብሳችንን በዳይ

ድንበር አላፊዎች ነን - በሰጧን አታላይ

ለብልጭልጭ ህይወት - በርከክ ባይ

ለዚህች ለቀን ጤዛ - ደሞም ለዱንያ

ላትሆነን መንገድ - ጀነትን መዝለቂያ

እያጠለቀችልን - የአዛብ ሜዳሊያ

ግን አንገሰፅም - ከዚህ ሁሉም ነገር

በኛ ወንጀል የተነሳ - ሙስሊሙ ሲሸበር

ጠላት ተጠራርተው - ሁሉም ባአንድ ሲያብር

እኛ ስንባላ - በጎሳ በብሄር

እኛ ስንከፋፋል - በቋንቋ በዘር

አስክሬኖች በርክተው - አፈር ሲለብስ በዶዘር

እኛ ቆይ የት ገባን - ቆይ የትስ አለቅን!?

ቆይ ምን ዋጠን - ምንስ ላይ ሰመጥን!?

ሙስሊም ረገፈ እኮ - እኛ በቁም እያለን

ጂሃዱስ አይሳካ - ያአላህ ማለት አቃተን!

የሙስሊም መሣሪያው - ዱዓ ነው እየተባልን፤

ያራህማን ያራሂም - እኛስ ቀሽሞች ነን፤

ሙስሊሞች ነንና - እባክህን ማረን

አዛኝ ነህና - ያአላህ እዘንልን

ውስጣችን ቆሰለ - ደም ዘነበ ከዓይን

ወንድሞቻችን አለቁ - በከሃዲዎች ረገፉብን

እነዛ የሰው አውሬዎች - ያንተን ቤት ደፈሩብን።

ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ

ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ

ያአላህ ያ! ራህማን - ቤቱም ቤትህ

ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ

ከጭንቅ ጠብቃቸው - ከጭንቅ አውጪ ነህ

ብዙዎች ቆሰሉ - ብዙዎች አለፉ

በህይወት እያሉ - ባሮችህ ደም ተፉ

በዘረጋሃው ምድርህ - ሙስሊሞች ተገፉ

እነዛ አውሬዎች - ሬሳን አሰለፉ

ሴትም አልቀራቸው - ህፃንም ቀጠፉ

ገደልን እያሉ - በደስታም ደነፉ

⭕️ በባረከው ምድርህ - *ባሮችህ ረገፉ* ።

በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

ቀን: ጥቅምት 20/2016 E.C [Oct 31/2023 G.C]

Join:-

YouTube.com/@SecretsofTruth

tiktok.com/@secretsof_truth

Twitter.com/Secretsof_Truth

Instagram.com/secretsof_truth

t.me/Secretsof_Truth

Fb.com/SecretsofTruth1

https://ummalife.com/ReshadMuzemil

t.me/ReshadMuzemil

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
elham hussen Changed her profile picture
7 ай
Татарчага аудару мөмкин түгел.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
elham hussen Changed her profile picture
7 ай
Татарчага аудару мөмкин түгел.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group