🌴የምር በአላህ መመካት መጨረሻው ተመልከት🌴
ሙሳ(ዓ.ሰ) እና ህዝቦቹ በዲናቸው ምክንያት ከግብፅ ምድር ሸሽተው ሲወጡ ፊርዓውን ደረሰባቸው። ከፊርዓውንም ጋር በጭራሽ የማይችሉት የሆነ ብዛት ያለው ሰራዊትና መሳርያ አለ። ሙሳ(ዐ.ሰ) እና ህዝባቸው ከፊታቸው ግዙፍ ባህር ገጠማቸው ወደኋላ ሲዞሩ ፈፅሞ ሊቋቋሙት የማይችሉት የታጠቁና ሀይል ያላቸው ሰራዊቶች በፊርዓውን እየተመራ ወደነሱ ቀርቧል። የሙሳም(ዐ.ሰ) ህዞቦቹ ስሞታ አቀረቡ እንዲህም አሉ{"እኛ የሚደርሱብን ነን"}(26:61)። ማለትም ባህሩ ፊት ለፉታችን ነው ሙሳና ሰራዊቱ ከኋላችን ናቸው እዚህ ጋር ሌላ መንገድ የለም። ወዴት መሄጃ አለን? መጥፋታችን መምታችን የማይቀር ነው ማለታቸው ነው።
ሙሳም (ዐ.ሰ) ሙሉ በአሏህ የመመካትና የመተማመንን ንግግር ተናገረ{"በጭራሽ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው። በእርግጥ ይመራኛል" አለ።}(26:62) ሙሉ በአላህ በመተማመን፣በማመን እና በመመካት ይህን ተናገረ። አላህም አለው{በህሩን በበትርህ ምታው}(26:63)። ሙሳም ባህሩን በበትሩ መታው {(መታውና)ተከፈለም።ክፍሉም ሁሉ እንደ ትልቅ ጋራ ሆነ።}(24:63) ሁሉም የጋራው ክፍልፋይ እንደግዙፍ ተራራ ሆነ።
ወንድሞቼ ላኢላሀኢለላህ!!! ውሃ እንደ ተራራ ቆመ። ያቺ ውሀ የነበረባት ምድር ውሀ የሌለባት የብስ ሆነች። ይህ ሁሉ የሆነው በአንድ ቅፅበት ነው።
___
ከሼይኽ ዓብዱረዛቅ አልበድር (ዓሸረቱ አስባብ ሊል ዊቃየቲ ሚነ ሲህር ወልዓይን) ከተሰኘው ኪታብ ከገፅ 33-35 የተወሰደ። ትርጉም ቃል በቃል አይደለም።
ኡማ ላይፍ ላይ ፎሎ በማድረግ ይከታተሉን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://ummalife.com/marufabadir