Translation is not possible.

🔰 ባሮችህ ረገፉ

በፈለስጢን ምድር - በአላህ ቤት

በመስጂደል አቅሳ - ነብዩ ባረፉበት

በካኃዲዋ እስራኤል - ረገፉ ህፃናት

ቦምብ ዘነበባቸው - እንቅልፋቸውን በተኙበት

ዓለምም ችላ አለው - ይህን የዘር ማጥፋት

ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ

ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ

ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ

ሙስሊም የሆኑ - ኢባዱ ራህማን ናቸው

ሰው ናቸውና ያራሂም - ካጠፉም ማራቸው

መንገድ ስተው እንደሆን - መንገድ አሳያቸው

ሙስሊሞቹም ያንተ - ህፃኖች ያንተው

ካንተ ውጭ ሌላ መጠጊያም ዬላቸው!

አዎ ወጀለኞች ነን - ነብሳችንን በዳይ

ድንበር አላፊዎች ነን - በሰጧን አታላይ

ለብልጭልጭ ህይወት - በርከክ ባይ

ለዚህች ለቀን ጤዛ - ደሞም ለዱንያ

ላትሆነን መንገድ - ጀነትን መዝለቂያ

እያጠለቀችልን - የአዛብ ሜዳሊያ

ግን አንገሰፅም - ከዚህ ሁሉም ነገር

በኛ ወንጀል የተነሳ - ሙስሊሙ ሲሸበር

ጠላት ተጠራርተው - ሁሉም ባአንድ ሲያብር

እኛ ስንባላ - በጎሳ በብሄር

እኛ ስንከፋፋል - በቋንቋ በዘር

አስክሬኖች በርክተው - አፈር ሲለብስ በዶዘር

እኛ ቆይ የት ገባን - ቆይ የትስ አለቅን!?

ቆይ ምን ዋጠን - ምንስ ላይ ሰመጥን!?

ሙስሊም ረገፈ እኮ - እኛ በቁም እያለን

ጂሃዱስ አይሳካ - ያአላህ ማለት አቃተን!

የሙስሊም መሣሪያው - ዱዓ ነው እየተባልን፤

ያራህማን ያራሂም - እኛስ ቀሽሞች ነን፤

ሙስሊሞች ነንና - እባክህን ማረን

አዛኝ ነህና - ያአላህ እዘንልን

ውስጣችን ቆሰለ - ደም ዘነበ ከዓይን

ወንድሞቻችን አለቁ - በከሃዲዎች ረገፉብን

እነዛ የሰው አውሬዎች - ያንተን ቤት ደፈሩብን።

ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ

ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ

ያአላህ ያ! ራህማን - ቤቱም ቤትህ

ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ

ከጭንቅ ጠብቃቸው - ከጭንቅ አውጪ ነህ

ብዙዎች ቆሰሉ - ብዙዎች አለፉ

በህይወት እያሉ - ባሮችህ ደም ተፉ

በዘረጋሃው ምድርህ - ሙስሊሞች ተገፉ

እነዛ አውሬዎች - ሬሳን አሰለፉ

ሴትም አልቀራቸው - ህፃንም ቀጠፉ

ገደልን እያሉ - በደስታም ደነፉ

⭕️ በባረከው ምድርህ - *ባሮችህ ረገፉ* ።

በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

ቀን: ጥቅምት 20/2016 E.C [Oct 31/2023 G.C]

Join:-

YouTube.com/@SecretsofTruth

tiktok.com/@secretsof_truth

Twitter.com/Secretsof_Truth

Instagram.com/secretsof_truth

t.me/Secretsof_Truth

Fb.com/SecretsofTruth1

https://ummalife.com/ReshadMuzemil

t.me/ReshadMuzemil

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group