መነበብ ያለበት በጣም ወሳኝ ርዕስ ለአላህ ብለው በትኩረት ያምብቡት።
#ዓይን_ቡዳ በማለት የምንጠራው
(Evil Eye)
بــســم الــلــه الــرحــمــن الــرحــيمــ
الحمد الله رب العالمين
ዓይን የአረብኛ ቃሉ ሲሆን ፤ ትርጉሙ በእይታ (አይንን በመጠቀም) ሰውን መጉዳት ማለት ነው፡፡ በአማርኛ ቡዳ ብለው ይጠሩታል ነገር ግን ዓይን ቡዳ ከሚለው የሰፋ ትርጉም አለው፡፡ ብዙ ግዜ በቅናት ይፈጠራል
በተጨማሪም በአንድ ነገር በጣም በመደነቅ የዓይን በሽታ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ዓይን ከዓይን ከሚያደርገው ሰው ወደ ዓይን ሚደረግበት ሰው ልክ እንደሚተኮስ ቀስት ነው፡፡ቀስት ኢላማ እንደሚመታው እና እንደሚስተው
ሁሉ ዓይንም ሰውየውን ሊያጠቃው ወይም ሊስተው ይችላል፡፡ ዓይን ሚደረግበት ሰው ራሱን በዚክር፣በዱዓ እና በሌሎች ዒባዳ የጠበቀ ከሆነ ዓይን አይጎዳዉም እንደዉም ወደ ዓይን የሚያደርገው ሊመለስ ይችላል፡፡
ራሱን ያልጠበቀ ከሆነ ግን ሊያጠቃው ይችላል፡፡ሙስሊሞች ራሳቸን ዚክር፣ዱዓ እና ሌሎች ዒባዳዎችን በአግባቡ በማከናወን መጠበቅ ይኖርብናል፡ ፡አንድ ሰው ራሱን በዓይን ሊያሳምም ይችላል በራሱ በጣም የሚደንቅ እና የሚገረም ከሆነ ራሱን ሊጎዳ ይችላል፡፡ ይህን ለመከላከል መልካም ነገር ባየን ግዜ" ባረከላህ ፊክ ለወንድ” ፤ “ባረከላህ ፊኪ” ለሴት ወይም “አላሁማ ባሪክ ፊህ” ለወንድ “አላሁማ ባሪክ ፊሀ ለሴት። ለራሱ አንዳች ነገር ከፈራ "ማሻ አላህ ላቁወተ ኢላ ቢላህ" ወይም ባረከላህ ፊየ ሀዛ ይበል፡፡ ይችላል፡፡ ሙሸሪኮች ነብዩን(ﷺ)አላህ በቁርአን ገልፆልናል፡፡ በዓይን ለማጥፋት ሲጥሩ እንደነበር
<< እነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ)ይቀርባሉ፡፡›› አል-ቀለም 51
ነብዩ(ﷺ)ኢብን አባስ ባስተላለፉት እና ሙስሊም፣ አህመድ እና ቲርሚዚይ በዘገቡት ሀዲስ፡-
ዓይን እውነት ነው፤ ቀደርን የሚቀድመው ነገር ቢኖር ኖሮ ዓይን ይሆን ነበር፡፡ ለዓይን(በአይን ለጎዳችሁት ሰው )እንድትታጠቡ ስትጠየቁ፤ መታጠብ ይኖርባቹሃል፡፡(ሙስሊም)
ከሀዲሱ የምንማረው ዓይን እውነት እንደሆነ እና ዓይን ያደረገው(ጎጂው)መታጠብ ግዴታው መሆኑን እና የታመመው ስው ደግሞ ዓይን ያደረገው ሰው በታጠበበት ሲታጠብ እንደሚፈወስ ከሀዲሱ እንገነዘባለን፡፡ ዓይን ያደረገው የሚታወቅ ከሆነ ፊቱን፣ እጁን፣ ክንዱን፣ ጉልበቱን፣ እግሩን እና ሽርጡንም(ትንሽ የጨርቁን ክፍል)በእቃ ላይ እንዲታጠብ በመጠየቅ ከታመመው ሰው ላይ በማፍሰስ መፈወስ ይቻላል፡፡ ዓይን ያደረገው ሰው መታጠብ ግዴታው ነው፤ በተጠየቀ ግዜ መታጠብ ይኖርበታል፡፡
አይሻ(ረድየላሁ አንሃ)፡-“ዓይን ያደረገው ሰው እንዲታጠብ ይታዘዛል፤ አይን የተደረገበት ሰው ዓይን ያደረገው በታጠበበት ዉሀ ይታጠባል፡፡" አቡ
ዳዉድ ዘግበዉታል
በነብዩ ዘመን የተከሰተውን እንመልከት አቢ ኡማመታ ኢብን ሰህል ኢብን ሀኒፍ እንዲህ ብለዋል፡- ሰህል ኢብን
ሀኒፋ ሲታጠብ አምር ኢብን ራቢእ ተመለከተው እና “ በአላህ ይሁንብኝ እንዲህ የሚያምር ቆዳ አይቼ አላውቅም በልጃ ገረድ ቢሆን እንኳ" አለ ሳህል ኢብን ሀኒፋም ወደቀ፡፡ ወደ ነብዩ ወሰዱት እና “ አንቱ የአላህ
መልእክተኛ ሆይ ለሰህል ኢብን ሀኒፍ አንዳች የሚያደርጉለት ነገር አለን በአላህ ይሁንብን ራሱን እንኳ አያነሳም አሉ” ነብዩም “የምትጠረጥሩት
ሰው አለ እንዴ?" በማለት ጠየቁ እነሱም “አምር ኢብን ራቢእን ነው የምንጠረጥረው በማለት መለሱ ነብዩም(ﷺ)አምር ኢብን ራቢእን ጠሩት እና አከበዱበት " አንዳችሁ ለምን ወንድሙን ይገድላልን? (ጥሩ ነገር በተመለከታችሁ ግዜ አላህ)ኢንዲባርክለት ዱዓ አታደርግለትምን አሉ በመቀጠልም አምር ኢብን ራቢእ እንዲታጠብ አዘዙት እሱም ፊቱን፣ እጁን፣ ክንዱን፣ ጉልበቱን፣እግሩን እና ሽርጡንም(ትንሽ የጨርቁን ክፍል) በዉሀ መያዣ እቃ ላይ ታጠበ፡፡የታጠበበት ዉሃ በሳህል ኢብን ሀኒፋ ላይ አፈሰሱት ሳህል ኢብን ሀኒፋም ምንም እንዳልሆነ ሰው ተነስቶ፤ ከሰዎች ጋርም ተቀላቀለ፡፡ “ኢማሙ ማሊክ ዘግበዉታል በሌላ ዘገባ ደግሞ ነብዩ(ﷺ)አምር ኢብን ረቢዕን ዉዱእ እንድያደርግ አዘዙት የሚል አለ አሁንም በሌላ ዘገባ በሳህል ኢብን ሀኒፍ በራሱ እና በጀርባው ላይም አፈሰሱበት የሚል አለ፡፡ ሩቅያ እና መታጠብ ለዓይን ፈውስ ናቸው፡፡ ከተቻለ ዓይን አድራጊው በእቃ ላይ ፊቱን እንዲታጠብ ፣ እንዲጉመጠመጥ በተጨማሪም እጁን ፣እግሮቹን እና ጉልበቱን እንዲታጠብ፤ ሽርጡንም(ትንሽ የጨርቁን ክፍል)እንዲያጥብ ይደረጋል ከዚያም ዉሀው በታማሚው ላይ ያፈሰሳል፡፡ ዓይን ያደረገበት ሰው ካልታወቀ ታማሚዉ በሩቅያ ይታከማል፡፡
https://ummalife.com/Meryemhassen