Translation is not possible.

#የዱሐን_ሶላት #ፀሐይ_ከፍ_ካለችበት_ሰዓት_ጀምሮ #እስክትዘነበል_ድረስ #መስገድ_ስለመፈቀዱና #ፀሐይዋ_ከበረታች_በኋላ #እኩለ_ቀን_ሊደርስ #አካባቢ_መስገድ_በላጭ_ስለመሆኑ

#ሐዲሥ 207 / 1143

ዘይድ ኢብኑ አርቀም እንዳስተላለፉት ሰዎች ከረፋዱ የመጀመሪያ ወቅት ላይ የዱሐን ሶላት ሲሰግድ ተመለከቱና፦ “ከዚህ ሰዓት ውጭ ባሉ ሰዓቶች መስገድ በላጭ መሆኑን አላወቁምን?” ካሉ በኋላ፥ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ማለታቸውን ገለጹ፦ “ወደ አላህ የሚመለሱ ሰዎች ሶላት፥ ግልግል ግመሎች የፀሐዩ ሙቀት በሚሰማቸው ወቅት ነው።” (ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ “ወደ አላህ ተመላሾች” የተባሉት በተውባና ምሕረትን በመለመን ወደርሱ የሚመለሱ ሰዎች ናቸው።

2/ የዱሐን ሶላት ፀሐይ ከወጣችበትና ከፍ ካለችበት ሰዓት አንስቶ እኩለ ቀን እስኪሆን ድረስ የሚፈቀድ ቢሆንም በደንብ ረፈድፈድ ካለ በኋላ መስገዱ የበለጠ ነው።

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

#gaza

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group