UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

6 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
jemal kebede shared a
Translation is not possible.

🍀ትልቅ ብሥራት!🍀

~

ለአንድ ወንድምህ ብድር አበድረህ በሆነ የጊዜ ገደብ እንዲመልስልህ ብትስማሙ

🎈 ካበደርክበት ጊዜ አንስቶ እስከተስማማችሁበት ጊዜ ድረስ በገንዘቡ ልክ በየቀኑ እንደምትሰድቅ ይታሰብልሀል።

🎈 የጊዜ ገደቡ ተጠናቆ "ሌላ ጊዜ ስጠኝ" ቢልህና ብትስማማ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ደግሞ በየቀኑ በመጠኑ ሁለት እጥፍ እንደምትሰድቅ ይቆጠርልሀል።

ማስረጃውስ?

~~~~

🛑 ሶሐባው ቡረይዳ ረዲየላሁ ዐንሁ ነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል: –

(مَنْ أَنْظَرَ مُعْسِرًا فَلَهُ بِكُلِّ يَوْمٍ مِثْلِهِ صَدَقَةٌ)

"ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ አምሳያውን ሶደቃ አለው።"

🛑 ከዚያም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ:–

"ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ ሁለት አምሳያውን ሶደቃ አለው።"

በዚህን ጊዜ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ‘ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ አምሳያውን ሶደቃ አለው’ ስትል ሰምቼህ ነበር። ከዚያ ደግሞ ‘ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ ሁለት አምሳያውን ሶደቃ አለው’ ስትል ሰማሁህ?" አልኳቸው።

🛑 እሳቸውም እንዲህ አሉ: –

"የእዳው መክፈያ ጊዜ እስከሚደርስ ድረስ ለሱ በየቀኑ አምሳያውን ሶደቃ አለው። ጊዜ ገደቡ ደርሶ ተጨማሪ ጊዜ ከሰጠው ደግሞ ለሱ በየ እለቱ ሁለት አምሳያውን ሶደቃ አለው።"

📚 ኢማሙ አሕመድ የዘገቡት "ሶሒሕ" ሐዲሥ ነው።

ከዚህም የበለጠውን ደግሞ ተመልከት!

ከአቢል የሰር ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል: –

( مَنْ أَنْظَرَ مُعْسِرًا أَوْ وَضَعَ عَنْهُ أَظَلَّهُ اللَّهُ فِي ظِلِّهِ )

"ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ወይም የተወለት አላህ በጥላው ስር ያስጠልለዋል።"

📚 ሙስሊም ዘግበውታል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
jemal kebede shared a
Translation is not possible.

ኦባማ እስራኤል በጋዛ በንጹሃን ላይ የምትወስደውን እርምጃ ተቃወሙ!!

እስራኤል ከሃማስ ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት በፍልስጤማውያን ንጹሃን ላይ የወሰደችው እርምጃ ዋጋ እንደሚያስከፍላት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ተናገሩ።

ቴል አቪቭ በጋዛ ምግብ፣ ውሃ እና ኤሌክትሪክ ማቋረጥ የፍልስጤማውያንን የትግል አመለካከት ይበልጥ እያጠነከረው እንደሚሄድም ገልጸዋል።

የሰብአዊ ኪሳራን ታሳቢ ያላደረገ የእስራኤል ወታደራዊ ስትራቴጂም በመጨረሻ ውጤቱ በተቃራኒው መሆኑ አይቀርም ብለዋል።

የጋዛ ነዋሪዎችን መሰረታዊ አገልግሎቶች ማቋረጥ የሰብአዊ ቀውሱን ከማባባሱ ባሻገር “እስራኤል በአለማቀፍ ደረጃ ድጋፍ እንድታጣ እና ጠላቶቿ እንዲበዙ ያደርጋል” ሲሉም ተደምጠዋል።ይህም በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ለአመታት ሲደረጉ የቆዩ ጥረቶችን ወደኋላ ይመልሳል ነው ያሉት። 

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሃማስን ጥቃት ባወገዙበት ንግግራቸው እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት ቢገልጹም ጦርነቱ በንጹሃን ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ሊታሰብበት እንደሚገባ አሳስበዋል።ኦባማ በዋይትሃውስ የስምንት አመት ቆይታቸው እስራኤል ከሃማስ ለሚሰነዘርባት ጥቃት ምላሽ እንድትሰጥ ድጋፍ ማድረጋቸውን ሬውተርስ በዘገባው አስታውሷል።

አሜሪካ ከኢራን ጋር በ2015 ያደረገችው የኒዩክሌር ስምምነት ግን የኦባማ እና ኔታንያሁ ግንኙነትን ማሻከሩ አይዘነጋም።

የኦባማ ምክትል የነበሩት የአሁኑ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም ሁለቱን መሪዎች ለማቀራረብ ሲሞክሩ የቆዩ ሲሆን፥ አሁን ላይ ዋነኛ የኔታንያሁ አጋር ሆነዋል።

    ድል ለንፁሀኖች

ፍልፅጤም

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
jemal kebede Сhanged his profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group