Ahmed TH Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ሰዎች ይንኩህና ይውጣልህ፣ አለዚያ መነካትን እንደፈራህ፣ ስትነካ ደግሞ እንዳመመህ ትኖራለህ፡፡

ሰዎች ይግፉህና ይውጣልህ፣ አለዚያ መገፋትን እንደፈራህ፣ ሲገፉህ ደግሞ እንደተፍገመገምክ ትኖራለህ፡፡

ሰዎች ትተውህ ይሂዱና ይውጣልህ፣ አለዚያ ገና ለገና ይተውኛል እያልክ እንደተሸማቀክ፣ ትተውህ ሲሄዱ ደግሞ እንዳለቃቀስክ ትኖራለህ፡፡

ሰዎች ይጥሉህና ይውጣልህ፣ አለዚያ ሰው እንዳይጠላህ ለማድረግ እንደጦዝክ፣ እንደጠሉህ ስታውቅ ደግሞ እንደቆዘምክ ትኖራለህ፡፡

ሰዎች ያውሩብህና ይውጣልህ፣ አለዚያ “ማን ምን እያወራብኝ ይሆን” በማለት ስታብሰለስል እንቅልፍ አጥተህ፣ እንዳወሩብህ ስታውቅ ደግሞ የተወራብህን ነገር ለማስተካከል እንደጦዝክ ትኖራለህ፡፡

እየተነካህ፣ እየተገፋህ፣ እየተተውክ፣ እየተጠላህ፣ እያወሩብህ . . . ሙሉ ሰው መሆን ትችላለህ!

የማይቀረውን እንዲመጣ፣ ከመሆን የማይከለከለውን እንዲሆን ስትፈቅድለትና በማንነትህ ላይ ግን አጉል ጫና እንደማያመጣ ሲገባህ፣ ከዚያ በኋላ የመጣውን ነገር ሁሉ ለመጋፈጥ የሚያስችል ብቃትንና ጥንካሬን ታዳብራለህ፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

<< ስልጣኑ ቢኖረኝ ኖሮ በ ኡመር ቦታ እሾምህ ነበር >>

ምርጥ ታሪክ

ወላሂ ይህቺ ምድር እኮ እንደነ ሰይድና ዑመር ያሉ ምርጥ ትውልዶች አልፈውባታል። የሰሩትን ተግባር ስንሰማ እኮ ኢስላም ባይነግረን ኖሮ አምኖ ለመቀበል ያስቸግረን ነበር።

እንደተለመደው ኡመር ኢብን አል ከጣብ ዞር ዞር እያሉ የሙስሊሞችን ቤት እየጎበኙ ነው መዲና ከተማ ውስጥ ከሩቁ እሳት ሲነድ ያዩና ሰው መኖር አለበት ብለው ወደዚያው ይሄዳሉ:እዛም ሲደርሱ አንዲት ሴትና ህፃናት ተቀምጠዋል ህፃናቱ ግን እያለቀሱ ነበር ሴትየዋ ውሀውን እሳተ ላይ ጥዳው እያፈላች ነው: ህፃናቶቹ አሁንም ያለቅሳሉ

ኡመር ጠጋ አሉና:ሰዎች መምጣታቸውን እንዲያውቁላቸው ጉሮሮዋቸውን እንደ መጥረግ አድርገው ድምፅ አሰሙ መልስ አላገኙም ኡመር ,ቤቶች ቀረብ ማለት እችላለሁ? በማለት ፍርድ ጠየቁ ሴትዩዋም አቤት ይቻላል አለቻቸው

ኡመር, ምን ሆናችሁ ነው ህፃናቱ ለምን ያለቅሳሉ ሲሉ ጠየቁ ሴትየዋም ወላሂ እኛ መንገደኞች ነን ምንም የሚበላ የሚቀመስ ነገር የለንም አለቻቸው የተጣደውስ ውሀ ምንድን ነው? በማለት ጠየቁ :

ሰትዩዋም ምንም ነገር የለውም ዝም ብዬ ልጆቹ እንቅልፍ እስኪወስዳቸው እያባበልኩበት ነው ( ምግቡ ካሁን አሁን ይደርሳል ብለው ሲጠብቁ እንዲተኙ ) ብላ መለሰችላቸው ኡመር ረ,አ, መሆናቸውን አላወቀችም ቀጥላ እንዲህ አለች

ኡመር ስለሁኔታችን ቢያውቅ ኖሮ እንዲህ አንሆንም ነበር አለች:

ኡመርም ጥቂት ጠብቂኝ ብለዋት ሄዱ "የረፈእ" የተባለ ትንሽ ልጅ ከኡመር ጋር አብሮ ተከተላቸው: እስቲ በይተል ማል (ግምጃ ቤት) ድረስ ተከተለኝ አሉት: ልጁም ፈጠን ፈጠን እያለ ቢከተላቸውም ከርሳቸው እኩል መራመድ አልቻለም ኡመር በይተል ማል ደረሱና በዱቄት የተሞላ ከረጢት አውጥተው በጀርባቸው ተሸከሙት ምግብና ገብስም ጨምረው ያዙ አሚረል ሙእሚኒን እኔ ልሸከምሎት አላቸው

ትንሹ ልጅ የቂያም ቀን ማን ይሸከምልኛል አሉ: የረፈእ ( ልጁን) ና አብህኝ ሁን ሁሉንም ነገር ሲያዘጋጁ አግዛቸዋለሁ በማለት እየተከታተሉ ወጡ ከሴትየዋ ቤትም እንደደረሱ ከሴትየዋ ጋር ሆነው ምግብ በጋራ ያዘጋጁ ጀመር የሚሰሩትን ስራ ሁሉ አገዟቸው እሳት በትንፋሻቸው እንዲቀጣጠል እስከማድረግ ደረሱ የተከበሩ ታላቁ ኡመር ህፃናቱንም እያጎረሱ መገቧቸው

ይህን ሁሉ አድርገው ሲጨርሱ ለሴትየዋ እንዲህ አሏት ሲነጋ አሚረል ሙእሚኒን ዘንድ እንድትመጪ ምናልባት እዛ ታገኚኝ ይሆናል: ብለዋት ሊወጡ ሲሉ ወላሂ አንተ ከኡመር የተሻልክ ሰው ነህ ወላሂ ስልጣኑ ቢኖረኝ ኖሮ በኡመር ቢን አል ከጣብ ቦታ በሾምኩህ ነበር: አለቻቸው ኡመር ረ,አ, መሆናቸውን አላወቀችምና ::

አሚረል ሙእሚኒን ኡመር ረ,አ በሰአቱ የሙስሊሙ ኡማ

ኘሬዝዳንት ነበሩ : አንድ መሪ የተራበን ለመመገብ እሳት አንድዶ ምግብ አብስሎ ሁሉን አዘጋጅቶ ሲካድም : አጁብ ይሄን ስርአት ነበር ኢስላም ያስተማረን:

ያ ወርቃማ ትውልድ እንዲህ ነበር

የአላህ ሰላምና እዝነት በነሱና

ቅኑን መንገድ በተከተሉት ላይ ይሁን ።

አሚን

Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

ጃፓን ውስጥ አንድ ሬስቶራንት አለ ።

እና የምግቡን ዝርዝር ወደኛ ቀይረን እንቀጥል

.....

በመጀመሪያ ቀን በዚህ ሬስቶራንት የተጠቀመ ሰው ሲናገር ፡ ወደ ምግብ ቤቱ ገብቶ አረፍ እንዳለ ፡ አንድ በእድሜ የገፉ አስተናጋጅ ተቀበሉት ።

ምን ልታዘዝ

" ምሳ ምን አላችሁ ? "

ትልቋ አስተናጋጅ ለሰውየው የሚፈልገውን ምግብ እንዲያዝ ሜኒውን ሰጡት

አተኩሮ ካየ በኋላ ፡ ...

"እሽ አንድ ጥብስና ፡ የሚጠጣ ደግሞ አምቦውሀ ያምጡልኝ "

....

አስተናጋጇ ትእዛዙን ተቀብለው ሄዱና ፡ ትንሽ ቆይተው ተመለሱ ። ምግቡን ያዘዘው ሰው ፡ ባዶ እጃቸውን የመጡትን አስተናጋጅ እያየ ፡....

" ምነው አልደረሰም ? " ብሎ ጠየቀ .

ኸረ ደርሷል ይኸው ይዤ መጥቻለሁ አሉና የሂሳብ መጠየቂያ ቢሉን አቀበሉት ።

" ምንድነው ይሄ ፡ ከምግቡ በፊት ነው እንዴ ሂሳብ ? "

አስተናጋጇ ፈገግ እያሉ .... ኸረ በፍፁም ፡ አሁን የበላኸው ቅቅልና የለስላሳ መጠጡ ሂሳብ ነው

" እንዴ እኔ ያዘዝኩት ጥብስና አምቦውሀ ነው ፡ እሱም አልመጣልኝምኮ "

የዚህ ጊዜ ትልቋ አስተናጋጅ ስህተት እንደሰሩ ገባቸውና ፡ ይቅርታ ለካ ያንተ አይደለም ብለው ቢሉን ከሱ አጠገብ ላሉ ተስተናጋጆች ሰጧቸውና

ያንተን አሁን ይዤ እመጣለሁ ብለውት እየተቻኮሉ ወደ ኪችን ተመለሱ ።

.....

እና ብዙም ሳይቆዩ በእጃቸው ምግብ የያዘ ሰሀን ይዘው መጡና ጠረጴዛው ላይ አስቀምጠው ፡ ቆይ የሚጠጣውን ይዤልህ ልምጣ ብለው ሄዱ ።

......

ሰውየው የመጣለትን ምግብ አየው ። በቅቤ ያበደ የቋንጣ ፍርፍር ነበር ፡ አሁን ተናደደ እሱ ያዘዘው ጥብስና አምቦውሀ ነው ። በዚህ መሀል እያለ አስተናጋጇ የቀዘቀዘ ቢራ ይዘው ተመለሱና እየከፈቱ መልካም ምግብ ብለውት ሊመለሱ ሲሉ ፡ ጠራቸው ።

" እየውሎት እኔኮ ያዘዝኩት " .....ብሎ እየተናገረ እያለ ፡ አለመግባባት መኖሩን ያስተዋለው የሬስቶራንቱ ሃላፊ መጣና ቀረብ ብሎ የሆነ ነገር ነገረው ።

ሰውየው ልክ ይህን እንደሰማ መከፋቱን ትቶ እየሳቀ ምግቡን ተመገበ ።

........

በቃ እዚህ ቤት እንዲህ ነው ። የዚህ ቤት ደንበኞች በብዛት ስለቤቱ የሚያውቁና ፡ ዝናውን ሰምተው የሚመጡ ሰወች ናቸው ።

እና ምሳህን ቁርጥ ልትበላ ገብተህ ፡ ዱለት ሊቀርብልህ ይችላል ። የመጣልህን መመገብ ነው ። ብዙ ሰወች ፡ ክትፎ አዘው ፡ ተጋቢኖ መጥቶላቸው ያውቃል ።

እየሳቅህ በልተህ ትወጣለህ ።

......

ይህ ምግብ ቤት የተሳሳቱ ትእዛዞች ምግብ ቤት ( Restaurant of Mistaken Orders ) በመባል ይታወቃል ። የዚህ ምግብ ቤት አስተናጋጆች ፡ Dementia በሚባል ፡ መርሳትን በሚያስከትል በሽታ የተያዙ ሰወች ናቸው ።

የምግብ ቤቱ ባለቤት በዚህ ህመም የተጠቁ ሰወች የሚደርስባቸውን መገለልና ጭንቀት ለማስወገድ ሲል የከፈተው ነበር ።

.....

አላማውም ሰወች እነዚህን ወገኖች ከማግለል ይልቅ ፍቅር እየሰጧቸው የሳቅና የደስታ ምንጭ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ለማድረግ ነው ።

.......

እና በዚህ ቤት ስትመገብ እድለኛ ከሆንክ ከስንት አንዴ በትክክል ያዘዝከው ሊመጣልህ ይችላል ። ብዙ ጊዜ ግን ፡ ኬክ አዘህ ፡ ቁርጥ ከቢላ ጋር ወይም እንደሰውየው ጥብስ አዘህ ሳትመገብ የሂሳብ ቢል ይመጣልሀል ።

....

አሁን ላይ ይህ ሬስቶራንት በጃፓን ብዙ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ፡ ከሀገሬው ነዋሪ ሌላ ፡ ስለምግብ ቤቱ በሰሙ ቱሪስቶችም ይጎበኛል ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

የተወሰኑ ሰሀባዎች መስጅድ ላይ ፈንጠር ብለው ቁጭ በማለት ያወራሉ። ረሱል ሰዐወ ቆም ብለው እያዳመጧቸው ነው።

አንደኛው ሰሀባ፦‹‹የኢብራሂም ዐሰ ጉዳይ ይገርማል! አላህ ባለሟል አድርጎ ያዘው›› እያለ በኢብራሂም መደነቁን ነገራቸው።

አንዱም ሰሀቢይ ቀበል አድርጎ፦‹‹እሱ ምን ይገርምኃል! ሙሳ እንኳን አለ አይደል እንዴ! አላህን ያነጋገረ!›› ብሎ ሌላ አግራሞቱን ሰነዘረ።

ሌላኛው ሰሀቢይም፦‹‹የሙሳ ምን ይደንቅኃል! ኢሳ እንኳ አለ አይደል እንዴ የአላህ የራሱ መንፈስ!›› እያለ መሞገት ጀመረ።

የሁሉንም ንግግር ካደመጠ በኋላ አንዱ ሰሓቢይ፦‹‹የነዚህ ሁሉ አይገርምም እኮ! አደም እንኳ አለ አይደል እንዴ አላህ የመረጠው!›› ሲል አፋቸውን አስያዛቸው። ከጀርባ ይህንን ሲያደምጡ የነበሩት ረሱልም ሰዐወ፦‹‹ሁላችሁም የተናገራችሁትን

ነገር አዳምጫለሁ፤ ትክክልም ናችሁ። ኢብራሂም የአላህ ባለሟል ነው አዎን ልክ ነው ፣ ሙሳ የአላህ አናጋሪ ነው አዎን ልክ ነው፣ ኢሳ'ም የአላህ መንፈስ ነው አዎን ልክ ነው ፣ አደምም የአላህ ምሩጥ ነው አዎን ልክ ነው። አዋጅ! እኔ ኮ የአላህ ወዳጅ ነኝ፤ አልፎክርም እንጂ! የምስጋናን ባንዲራ የቂያማ ለት ይዤ የምቆመው እኮ እኔው ነኝ፤ አልፎክርም እንጂ! እኔ እኮ የመጀመርያው አማላጅ እና ተማላጅ ነኝ፤ አልፎክርም እንጂ!

እኔ እኮ ነኝ የዚያን ዕለት የጀነትን የበር ማንኳኪያውን ለመጀመርያ ግዜ የምይዘው፣ ከዝያም ይከፈትልኝና ድሃ ሙእሚኖችን ይዤ የምገባው፤ አልፎክርም እንጂ! እኔ እኮ ነኝ የመጀመርያዎቹም የመጨረሻዎቹም ክቡር ፍጡር፤ አልፎክርም እንጂ! ›› አሉ። ነቢ አይፎክሩም እንጂ ቢፎክሩማ...!

ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም!!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

I have to ...... ማድረግ አለብኝ

✅ I have to go.

መሔድ አለብኝ።

✅ I have to read

ማንበብ አለብኝ።

✅ I have to pee.

መሽናት አለብኝ።

✅ I have to play.

መጫወት አለብኝ።

✅ I have to eat.

መብላት አለብኝ።

✅ I have to call.

መደወል አለብኝ።

✅ I have to sleep.

መተኛት አለብኝ።

I have to bow.

👆____ ??? እናንተ ሞክሩት

Send as a message
Share on my page
Share in the group