1 year Translate
Translation is not possible.

የተወሰኑ ሰሀባዎች መስጅድ ላይ ፈንጠር ብለው ቁጭ በማለት ያወራሉ። ረሱል ሰዐወ ቆም ብለው እያዳመጧቸው ነው።

አንደኛው ሰሀባ፦‹‹የኢብራሂም ዐሰ ጉዳይ ይገርማል! አላህ ባለሟል አድርጎ ያዘው›› እያለ በኢብራሂም መደነቁን ነገራቸው።

አንዱም ሰሀቢይ ቀበል አድርጎ፦‹‹እሱ ምን ይገርምኃል! ሙሳ እንኳን አለ አይደል እንዴ! አላህን ያነጋገረ!›› ብሎ ሌላ አግራሞቱን ሰነዘረ።

ሌላኛው ሰሀቢይም፦‹‹የሙሳ ምን ይደንቅኃል! ኢሳ እንኳ አለ አይደል እንዴ የአላህ የራሱ መንፈስ!›› እያለ መሞገት ጀመረ።

የሁሉንም ንግግር ካደመጠ በኋላ አንዱ ሰሓቢይ፦‹‹የነዚህ ሁሉ አይገርምም እኮ! አደም እንኳ አለ አይደል እንዴ አላህ የመረጠው!›› ሲል አፋቸውን አስያዛቸው። ከጀርባ ይህንን ሲያደምጡ የነበሩት ረሱልም ሰዐወ፦‹‹ሁላችሁም የተናገራችሁትን

ነገር አዳምጫለሁ፤ ትክክልም ናችሁ። ኢብራሂም የአላህ ባለሟል ነው አዎን ልክ ነው ፣ ሙሳ የአላህ አናጋሪ ነው አዎን ልክ ነው፣ ኢሳ'ም የአላህ መንፈስ ነው አዎን ልክ ነው ፣ አደምም የአላህ ምሩጥ ነው አዎን ልክ ነው። አዋጅ! እኔ ኮ የአላህ ወዳጅ ነኝ፤ አልፎክርም እንጂ! የምስጋናን ባንዲራ የቂያማ ለት ይዤ የምቆመው እኮ እኔው ነኝ፤ አልፎክርም እንጂ! እኔ እኮ የመጀመርያው አማላጅ እና ተማላጅ ነኝ፤ አልፎክርም እንጂ!

እኔ እኮ ነኝ የዚያን ዕለት የጀነትን የበር ማንኳኪያውን ለመጀመርያ ግዜ የምይዘው፣ ከዝያም ይከፈትልኝና ድሃ ሙእሚኖችን ይዤ የምገባው፤ አልፎክርም እንጂ! እኔ እኮ ነኝ የመጀመርያዎቹም የመጨረሻዎቹም ክቡር ፍጡር፤ አልፎክርም እንጂ! ›› አሉ። ነቢ አይፎክሩም እንጂ ቢፎክሩማ...!

ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም!!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group