<< ስልጣኑ ቢኖረኝ ኖሮ በ ኡመር ቦታ እሾምህ ነበር >>
ምርጥ ታሪክ
ወላሂ ይህቺ ምድር እኮ እንደነ ሰይድና ዑመር ያሉ ምርጥ ትውልዶች አልፈውባታል። የሰሩትን ተግባር ስንሰማ እኮ ኢስላም ባይነግረን ኖሮ አምኖ ለመቀበል ያስቸግረን ነበር።
እንደተለመደው ኡመር ኢብን አል ከጣብ ዞር ዞር እያሉ የሙስሊሞችን ቤት እየጎበኙ ነው መዲና ከተማ ውስጥ ከሩቁ እሳት ሲነድ ያዩና ሰው መኖር አለበት ብለው ወደዚያው ይሄዳሉ:እዛም ሲደርሱ አንዲት ሴትና ህፃናት ተቀምጠዋል ህፃናቱ ግን እያለቀሱ ነበር ሴትየዋ ውሀውን እሳተ ላይ ጥዳው እያፈላች ነው: ህፃናቶቹ አሁንም ያለቅሳሉ
ኡመር ጠጋ አሉና:ሰዎች መምጣታቸውን እንዲያውቁላቸው ጉሮሮዋቸውን እንደ መጥረግ አድርገው ድምፅ አሰሙ መልስ አላገኙም ኡመር ,ቤቶች ቀረብ ማለት እችላለሁ? በማለት ፍርድ ጠየቁ ሴትዩዋም አቤት ይቻላል አለቻቸው
ኡመር, ምን ሆናችሁ ነው ህፃናቱ ለምን ያለቅሳሉ ሲሉ ጠየቁ ሴትየዋም ወላሂ እኛ መንገደኞች ነን ምንም የሚበላ የሚቀመስ ነገር የለንም አለቻቸው የተጣደውስ ውሀ ምንድን ነው? በማለት ጠየቁ :
ሰትዩዋም ምንም ነገር የለውም ዝም ብዬ ልጆቹ እንቅልፍ እስኪወስዳቸው እያባበልኩበት ነው ( ምግቡ ካሁን አሁን ይደርሳል ብለው ሲጠብቁ እንዲተኙ ) ብላ መለሰችላቸው ኡመር ረ,አ, መሆናቸውን አላወቀችም ቀጥላ እንዲህ አለች
ኡመር ስለሁኔታችን ቢያውቅ ኖሮ እንዲህ አንሆንም ነበር አለች:
ኡመርም ጥቂት ጠብቂኝ ብለዋት ሄዱ "የረፈእ" የተባለ ትንሽ ልጅ ከኡመር ጋር አብሮ ተከተላቸው: እስቲ በይተል ማል (ግምጃ ቤት) ድረስ ተከተለኝ አሉት: ልጁም ፈጠን ፈጠን እያለ ቢከተላቸውም ከርሳቸው እኩል መራመድ አልቻለም ኡመር በይተል ማል ደረሱና በዱቄት የተሞላ ከረጢት አውጥተው በጀርባቸው ተሸከሙት ምግብና ገብስም ጨምረው ያዙ አሚረል ሙእሚኒን እኔ ልሸከምሎት አላቸው
ትንሹ ልጅ የቂያም ቀን ማን ይሸከምልኛል አሉ: የረፈእ ( ልጁን) ና አብህኝ ሁን ሁሉንም ነገር ሲያዘጋጁ አግዛቸዋለሁ በማለት እየተከታተሉ ወጡ ከሴትየዋ ቤትም እንደደረሱ ከሴትየዋ ጋር ሆነው ምግብ በጋራ ያዘጋጁ ጀመር የሚሰሩትን ስራ ሁሉ አገዟቸው እሳት በትንፋሻቸው እንዲቀጣጠል እስከማድረግ ደረሱ የተከበሩ ታላቁ ኡመር ህፃናቱንም እያጎረሱ መገቧቸው
ይህን ሁሉ አድርገው ሲጨርሱ ለሴትየዋ እንዲህ አሏት ሲነጋ አሚረል ሙእሚኒን ዘንድ እንድትመጪ ምናልባት እዛ ታገኚኝ ይሆናል: ብለዋት ሊወጡ ሲሉ ወላሂ አንተ ከኡመር የተሻልክ ሰው ነህ ወላሂ ስልጣኑ ቢኖረኝ ኖሮ በኡመር ቢን አል ከጣብ ቦታ በሾምኩህ ነበር: አለቻቸው ኡመር ረ,አ, መሆናቸውን አላወቀችምና ::
አሚረል ሙእሚኒን ኡመር ረ,አ በሰአቱ የሙስሊሙ ኡማ
ኘሬዝዳንት ነበሩ : አንድ መሪ የተራበን ለመመገብ እሳት አንድዶ ምግብ አብስሎ ሁሉን አዘጋጅቶ ሲካድም : አጁብ ይሄን ስርአት ነበር ኢስላም ያስተማረን:
ያ ወርቃማ ትውልድ እንዲህ ነበር
የአላህ ሰላምና እዝነት በነሱና
ቅኑን መንገድ በተከተሉት ላይ ይሁን ።
አሚን