1 year Translate
Translation is not possible.

ጃፓን ውስጥ አንድ ሬስቶራንት አለ ።

እና የምግቡን ዝርዝር ወደኛ ቀይረን እንቀጥል

.....

በመጀመሪያ ቀን በዚህ ሬስቶራንት የተጠቀመ ሰው ሲናገር ፡ ወደ ምግብ ቤቱ ገብቶ አረፍ እንዳለ ፡ አንድ በእድሜ የገፉ አስተናጋጅ ተቀበሉት ።

ምን ልታዘዝ

" ምሳ ምን አላችሁ ? "

ትልቋ አስተናጋጅ ለሰውየው የሚፈልገውን ምግብ እንዲያዝ ሜኒውን ሰጡት

አተኩሮ ካየ በኋላ ፡ ...

"እሽ አንድ ጥብስና ፡ የሚጠጣ ደግሞ አምቦውሀ ያምጡልኝ "

....

አስተናጋጇ ትእዛዙን ተቀብለው ሄዱና ፡ ትንሽ ቆይተው ተመለሱ ። ምግቡን ያዘዘው ሰው ፡ ባዶ እጃቸውን የመጡትን አስተናጋጅ እያየ ፡....

" ምነው አልደረሰም ? " ብሎ ጠየቀ .

ኸረ ደርሷል ይኸው ይዤ መጥቻለሁ አሉና የሂሳብ መጠየቂያ ቢሉን አቀበሉት ።

" ምንድነው ይሄ ፡ ከምግቡ በፊት ነው እንዴ ሂሳብ ? "

አስተናጋጇ ፈገግ እያሉ .... ኸረ በፍፁም ፡ አሁን የበላኸው ቅቅልና የለስላሳ መጠጡ ሂሳብ ነው

" እንዴ እኔ ያዘዝኩት ጥብስና አምቦውሀ ነው ፡ እሱም አልመጣልኝምኮ "

የዚህ ጊዜ ትልቋ አስተናጋጅ ስህተት እንደሰሩ ገባቸውና ፡ ይቅርታ ለካ ያንተ አይደለም ብለው ቢሉን ከሱ አጠገብ ላሉ ተስተናጋጆች ሰጧቸውና

ያንተን አሁን ይዤ እመጣለሁ ብለውት እየተቻኮሉ ወደ ኪችን ተመለሱ ።

.....

እና ብዙም ሳይቆዩ በእጃቸው ምግብ የያዘ ሰሀን ይዘው መጡና ጠረጴዛው ላይ አስቀምጠው ፡ ቆይ የሚጠጣውን ይዤልህ ልምጣ ብለው ሄዱ ።

......

ሰውየው የመጣለትን ምግብ አየው ። በቅቤ ያበደ የቋንጣ ፍርፍር ነበር ፡ አሁን ተናደደ እሱ ያዘዘው ጥብስና አምቦውሀ ነው ። በዚህ መሀል እያለ አስተናጋጇ የቀዘቀዘ ቢራ ይዘው ተመለሱና እየከፈቱ መልካም ምግብ ብለውት ሊመለሱ ሲሉ ፡ ጠራቸው ።

" እየውሎት እኔኮ ያዘዝኩት " .....ብሎ እየተናገረ እያለ ፡ አለመግባባት መኖሩን ያስተዋለው የሬስቶራንቱ ሃላፊ መጣና ቀረብ ብሎ የሆነ ነገር ነገረው ።

ሰውየው ልክ ይህን እንደሰማ መከፋቱን ትቶ እየሳቀ ምግቡን ተመገበ ።

........

በቃ እዚህ ቤት እንዲህ ነው ። የዚህ ቤት ደንበኞች በብዛት ስለቤቱ የሚያውቁና ፡ ዝናውን ሰምተው የሚመጡ ሰወች ናቸው ።

እና ምሳህን ቁርጥ ልትበላ ገብተህ ፡ ዱለት ሊቀርብልህ ይችላል ። የመጣልህን መመገብ ነው ። ብዙ ሰወች ፡ ክትፎ አዘው ፡ ተጋቢኖ መጥቶላቸው ያውቃል ።

እየሳቅህ በልተህ ትወጣለህ ።

......

ይህ ምግብ ቤት የተሳሳቱ ትእዛዞች ምግብ ቤት ( Restaurant of Mistaken Orders ) በመባል ይታወቃል ። የዚህ ምግብ ቤት አስተናጋጆች ፡ Dementia በሚባል ፡ መርሳትን በሚያስከትል በሽታ የተያዙ ሰወች ናቸው ።

የምግብ ቤቱ ባለቤት በዚህ ህመም የተጠቁ ሰወች የሚደርስባቸውን መገለልና ጭንቀት ለማስወገድ ሲል የከፈተው ነበር ።

.....

አላማውም ሰወች እነዚህን ወገኖች ከማግለል ይልቅ ፍቅር እየሰጧቸው የሳቅና የደስታ ምንጭ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ለማድረግ ነው ።

.......

እና በዚህ ቤት ስትመገብ እድለኛ ከሆንክ ከስንት አንዴ በትክክል ያዘዝከው ሊመጣልህ ይችላል ። ብዙ ጊዜ ግን ፡ ኬክ አዘህ ፡ ቁርጥ ከቢላ ጋር ወይም እንደሰውየው ጥብስ አዘህ ሳትመገብ የሂሳብ ቢል ይመጣልሀል ።

....

አሁን ላይ ይህ ሬስቶራንት በጃፓን ብዙ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ፡ ከሀገሬው ነዋሪ ሌላ ፡ ስለምግብ ቤቱ በሰሙ ቱሪስቶችም ይጎበኛል ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group