አምስት ነገሮችን ከረመዷን በፊት!!
በ አቡ ሀይደር
1ኛ) የረመዷን ወር ከመጣልህና በበሩም ደጅ ላይ ከደረስህ አላህ ላንተ በማሰብ የዚህ ወር ተካፋይ እንድትሆን የላከልህ ጸጋ መሆኑን ልታስብ ይገባሀል፡፡ ዕድሜና ጤናን ሰጥቶህ ይህን የተባረከ ወር እንድትቋደስ ማድረግ ትልቅ ኒዕማ (ጸጋ) ነውና፡፡ ስንትና ስንት ልቦች ይህን ወር ተመኝተውት ነበር? የቀደር ጉዳይ ሆኖ ግን ስንቶች ወደ አኼራ ተሸኙ? አሁን እነሱ ከአፈር በታች በቀብር ይገኛሉ፡፡ አንተ ግን ሕያው ኾነህ የረመዷንን ወር ከተገኘህ የጌታህ ጸጋ መሆኑን ዐውቀህ ለዚህ ያደረሰህን አላህ አመስግነው፡፡ በልብህም በአንደበትህም፡- "ጌታዬ አምላኬ አላህ ሆይ! የረመዷንን ወር በሰላም በጤና ስላደረስከኝ እንዲሁም ስለማይቆጠረው ውለታህ ከልቤ አመሰግንሀለሁ" በል፡፡ ይህንን ካልክ ከልብህም ለወሩ ከተዘጋጀህ ጌታህ ደግሞ ሌላንም እንደሚጨምርልህ እንዲህ በማለት በቃሉ አስታውቆሀል፡-
"ጌታችሁም፦ ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም (እቀጣችኋላሁ)፤ ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና በማለት ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሱ)።" (ሱረቱ ኢብራሂም 14፡7)፡፡
በተጨማሪም ሌላ ልታስታውሰው የሚገባህ ነገር እንዳንተው ስንቶች ረመዷንን ተገኝተው ግን ህመምና እርጅና እንዲሁም ሌላ ምክንያት ከጾምና ከቂያሙ-ለይል ያገዳቸው መኖራቸውን ነው፡፡ ታዲያ አንተ ጤናማና ጠንካራ ከሆንክ ጌታህን አመስግነውና በዚህ አካልህም ጾሙንና ዒባዳውን በአግባቡ እንድታከናውን ጌታህን እገዛ ለምነው፡፡ ያለሱ እገዛ የትም እንደማትደርስም እንዲህ በማለት ይነግርሀል፡-
"አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን (በሉ)።" (ሱረቱል ፋቲሓ 5)፡፡
ይቀጥላል...
ኢስላማዊ ዳእዋ በቴሌ ግራም ለመከታታል ሊንኩን ይጫኑት!
https://telegram.me/islamictrueth