fozia Adem Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

fozia Adem shared a
Translation is not possible.

💡የተሻለ ማንነት እንዲኖረን የሚረዱን ምክሮች 💡

❖•◐ 1.ምንጊዜም ካለህበት የ ትምህርትና የእውቀት ደረጃ ከፍ ለማለት ሞክር ።

❖•◐ 2.ሚስጥርህን ለ ራስህ ብቻ ደብቀህ ያዝ ።ከ ልፍለፋና ከ ክርክር ራስህን አርቅ ።

❖•◐ 3.ጥፋት በምታጠፋበት ጊዜ ብቻ እንጂ ተደጋጋሚ የሆነ ይቅርታ አትጠይቅ ።

❖•◐ 4. በተፈጥሮህ ሁን ። ሰዎች ላይ ተፅዕኖ መፍጠር ከሚወዱ ሰዎች ጋር አትመደብ ።

❖•◐ 5. ራስህንና የፈፀምካቸውን መልካም ተግባራት አትናቅ ። ለሌላም ሰው አሳንሶ እንዲመለከትህ አትፍቀድ ።

❖•◐ 6. ማንንም ሰው አትለምን ። የሰው ልጅ ክብር በገንዘብ ና በቁሳቁስ የማይለካ ትልቀ ሀብት ነውና።

❖•◐ 7. አብዛኛውን የሕይወት ውሳኔዎችህን ራስህ ምረጣቸው ። ከ አንተው ውጭ ስለራስህ ሊያስብልህ የሚችል ሰው የለምና።

❖•◐ 8. ሕይወትን ተጨባጭ ላይ ባለው ሁኔታና በፈገግታ ተመልከታት ። በራስህ የተለየህ ሁን እንጂ ሰዎችን አትከተል።

❖•◐ 9.ጥንካሬና ሃይለኝነት ፍትሐዊ በመሆን እንጂ አምባ ገነን በመሆን የማይገኝ መሆኑን አስታወስ።

❖•◐ 10. የጊዜህን አሳሳቢነት አትዘንጋ ። በማይሆን ዛዛታና የውሸታሞችን ቅዠት በመስማት አታጥፋው።

❖•◐ 11. ብዙ ከማውራት ይልቅ ብዙ አዳምጥ ። ስለ ግል ሕይወትህም ብዙ ጊዜ ከማውራት ተቆጠብ ።

❖•◐ 12. ያገኘኸውን ሁሉ መውሰድና መጠቀም አይኖርብህም ። ላንተ የሚጠቅምህንና መልካምን ነገር ለመስራት የሚረዳህን ብቻ ውሰድ ።

❖•◐ 13.የተሻለ ህይወት መኖርና የምትፈልገውን ነገር ማሳካት ትችላለህ ይገባሃልም ። ነገር ግን ይህ በአንዴ የሚሆን ነገር ሳይሆን በራስህ ጥረት የምታሳካው ነገር ነው።

❖•◐ 14.ከሌሎች ሊያጋጥሙህ የሚችሉ እንቅፋቶችን ጠብቅ ። ሊያበሳጩህና ሊረብሹህ ለሚችሉ ነገሮች ትኩረት ሳትሰጥ ለማለፍ ሞክር

Send as a message
Share on my page
Share in the group
fozia Adem shared a
Translation is not possible.

ፍልስጤን ልጅ አላት

-------------------

የወንድነት ሚዛን የጀግነት መጠን፡

የሰላም ተምሳሌት አርማ የመሰልጠን፡

-----------------

የአይሁድን አርማ ዘሎ የሚበጥስ፡

በዳይ ግፈኞችን በደም የሚያስነጥስ፡

----------------------

ጊዜው ቢዘገይም በድም የሚመለስ፡

ለአሏህ ጠላቶች የማይለሳለስ፡

--------------------------

በየደረሱበት አይሁድን አሳዳጅ፡

አንገት የሚያስደፊ ጠላትን በግዳጅ፡

-------------------

ለመስጂደል-አቅሷ ሁሌ እሚሞትላት፡

አሞተ-መራራ ፍልስጤን ልጅ አላት፡

----------------------------

Send as a message
Share on my page
Share in the group
7 month Translate - Youtube
Translation is not possible.
Send as a message
Share on my page
Share in the group
fozia Adem shared a
Translation is not possible.

☑️ እስካሁን የማይከፈል የስንቱ እዳ ተሸክመናል……

📍ሀሰነል በስርይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል። «ሀሜት ከእዳ የባሰ የከፋ ነው። እዳ ይከፈላል ሀሜት ግን አይከፈልም።»

ያማኸው ሰው አግኝተህ አፋቷ ካልጠየክና ይቅር ካላለህ በስተቀር እዳ ሆና እላይህ ላይ ይቀመጣል። የምትከፍለው የውመልቂያማ በመልካም ስራህ ብቻ ነው።

ሰዎች ሲያሙህ በመጥፎ ሲያነሱህና ስምህ ሲያጠፋ ሰው ነህና ሊከፋህና ሊሰማህ ይችላል። ነገር ግን ነገ የውመል ቂያማ ወደዱም ጠሉም ከመልካም ስራቸው የሚያካፍሉህ አልያም ወንጀልህ የሚሸከሙ መሆኑን ስትረዳ ውስጥህ ቀዝቀዝ ይላል። የምታገኘውን ምንዳ ስታስብ ካልሰለቻቸው ሁሌም ስለኔ ቢያወሩ ምንአሻኝ ያስብላል። ግን ሶብር ይፈልጋል።

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

Telegram: Contact @Sadik_Ibnu_Heyru

Telegram: Contact @Sadik_Ibnu_Heyru

➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች ➲የአቂዳ ኪታቦች ➲የፊቅህ ግንዛቤዎች ➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ ➲ወቅታዊ ምክሮች ➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Send as a message
Share on my page
Share in the group
fozia Adem shared a
Translation is not possible.

💎የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«ሙስሊም ለሙስሊም ወንድሙ ነው፣ አይበድለውም፣ ለጠላት አሳልፎም አይሰጠውም።»

ሸይኽ ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል።

«ወንድሞቼ ሆይ! አላህን ፍሩ፣ ለራሳችሁም መልካም አድርጉ፣ አላህ ያዘዘውን የእምነት ወንድማማችነት አሳኩ፣ እውነት የተናገረን፤ እውነት ተናግራሃል ፣

አበጀህ በሉት፣  መልካሙን ጠቁሙት፣ አመስግኑት አስፈላጊውን ድጋፍ አድርጉለት።

ጥፋተኛውን፣ “ልክ አይደለህም፣ ተሳስተሃል” በማለት በእርጋታ እና በጥበብ ንገሩት። አቅጣጫም ስጡት ምከሩትም። በዚህም የተነሳ ጥራት ይገባውና ከአላህ ታላቅ ሽልማት፣ ከሰዎች መልካም ውዳሴ እና በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር መልካም ስም ታተርፋላችሁ።  ከመጥፎ ዝንባሌ እና አክራሪነት፣ እንዲሁም ከጨለምተኝነት ተጠንቀቁ። አትራፊ ትሆናላችሁ፣ ጥሩውን ውጤት ታገኛላችሁ።”

📕መጅሙዕ አልፈታዋ (4/165)

Send as a message
Share on my page
Share in the group