UMMA TOKEN INVESTOR

bintmoshe shared a
Translation is not possible.

🥀 Daily Reminder 103🥀

وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِأَعۡدَآئِكُمۡۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَلِيّٗا وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ نَصِيرٗا(45)

"አላህም ጠላቶቻችሁን ዐዋቂ ነው፡፡ ጠባቂነትም በአላህ በቃ፡፡ ረዳትነትም በአላህ በቃ!!"

Surah Al-Nisa'; 45

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🥀 Daily Reminder 103🥀

وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِأَعۡدَآئِكُمۡۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَلِيّٗا وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ نَصِيرٗا(45)

"አላህም ጠላቶቻችሁን ዐዋቂ ነው፡፡ ጠባቂነትም በአላህ በቃ፡፡ ረዳትነትም በአላህ በቃ!!"

Surah Al-Nisa'; 45

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አላህ ሰብስቦ ይግደላችሁ!

ከሙሐመድ ሰዒድ (ABX) የተመከርኩት!

በ44 አመቱ ከ50 በላይ መፅሐፍትን ደርሶ ለአንባቢ አቅርቧል:: ህይዎትን ቀለል አድርጎ የተረዳና የሚኖር ሰው እንደሆነ ከገፅታው መረዳት ችያለሁ:: ለመጀመሪያ ጊዜ "ሶባሐል ኸይር!" የሚለው መፅሐፉን ከእርሱ በኩል በተገኘ ስፖንሰርሺፕ ለተማሪዎች አመጣ ዘንድ ከጓደኛጋ በመሆን አገኘሁት:: የጠበኩትና ያገኘሁት ሙሐመድ እጅግ የተለያዩ ነበሩ:: ልስልስ ያለ ዛሂድ መሆኑ ከፊቱ ይነበባል:: "መፅሐፍ ለመውሰድ እዚህ ድረስ በመምጣታችሁ ጎበዝ ናችሁ::" አለን :: ግራ ገባኝ:: እሱ መፅሐፉን ለመፃፍ ስንት ሌሊት ቁጭ ብሎ ውሎ ማደሩ ሳይበቃው የደረሰውን መፅሐፍ ለማከፋፈል ከቤት ቤት እየተዘዋወረ እኛ በነፃ ወስደን ለማንበብ ከእሱ ዘንድ ካልሄድን ምኑን ሰው ነን?" የሚል ጥያቄ በልቦናዬ ውስጥ ተርመሰመሰ :: ብቻ የዚያኔ ከገፅታው ዱንያን በመተውና ጊዜን ለአላህ በመስጠት ውስጥ የሚገኝ ውበት ምን እንደሚመስል ተመልክቼ ተለያየን::

ዛሬ በአላህ ፈቃድ መስጂድ ላይ አገኘሁትና ይመክረን ዘንድ ከጓደኞቼ ጋር በዙሪያው ተቀመጥን:: ምክሩን "አያቴ! አላህ ሰብስቦ ይግደላችሁ!" ትል ነበር በማለት ጀመረ:: በመቀጠልም "ሰብስቦ ስትል ግን በእርሱ መንገድ ላይ ሰብስቦ ለማለት ነው:: አሁን ላይ የወጣቱ ሀሳብ በብዙ መንገድ ተበታትኗል:: በየሶሻል ሚዲያው ተበታትኗል:: ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ነጋ ጠባ የሚሰማው ነገር ደስ አይልም:: ለወደፊትም ደስ አይልም:: በዚህ ውስጥ እናንተ ሀሳባችሁን ወደ አላህ መንገድ መሰብሰብ አለባችሁ:: ለዚህ ደግሞ ለራሳችሁ ቦታ በመስጠት ነገ መሆን ለምትፈልጉት መስዋዕትነት መክፈል አለባችሁ:: እኔ ዛሬ 44 አመቴ ነው:: በእናንተ እድሜ ሆኜ ግን 40 አመት ለእኔ ሩቅ ነበር:: አሁን ላይ ግን የአንድ ቀን ልዩነት እንኳ ያለው አይመስለኝም:: ለእናንተም ተመሳሳይ ነው:: መጪ ነገር ሁሉ ቅርብ ነው:: ሞትም ማለት ነው:: ያለፈ ነገር ደግሞ ሩቅ ነው:: ከስህተታችሁ ተማሩ:: ለወንጀላችሁ ጌታችሁን መሐርታ ጠይቁ:: መሆን የምትችሉትን ትልቁን ለመሆን በመጣር ውስጥ ለመሞት ስሩ:: አላህ በሀሳባችሁ ነው የሚመነዳችሁ:: ተዋብ ነው:: መቶ ሰው ገድሎ ጀነት የገባው ሰው ተውበት በማድረጉ ነው:: በሀሳቡ ነው:: በአላህ መሐርታ ነው::" አለን ::

ከዚህም በተጨማሪ "ንባብ ላይ ተጠናከሩ:: ንባብ ብዙ ነገራችሁን ያሻሽላል:: እኔ ጌታዬ ቢያጎድልብኝ እንኳ ሌላውን ወስዶ አይኔ ለንባቡ እስከኖርኩ ድረስ እንዲያቆይልኝ ዱዓዬ ነው ::" አለን ::

አላህ ሁሉንም ይሙላልህ ያ ሙሐመድ! እድሜውን ያስረዝምልን! ብርታቱን ይስጠው! ብርታቱን ይስጠን!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

👉   የሴትና የዱንያ ፊትና

          ክፍል አንድ

       የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – ሁለት አጥፊ ነገሮችን እንድንጠነቀቅ እንዲህ ብለው  መክረውናል : –

عن أبي سعيد الخدري – رضي الله عنه – قال : قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم –

" إنَّ الدُّنْيَا حُلْوَةٌ خَضِرَةٌ، وإنَّ اللَّهَ مُسْتَخْلِفُكُمْ فِيهَا، فَيَنْظُرُ كيفَ تَعْمَلُونَ، فَاتَّقُوا الدُّنْيَا وَاتَّقُوا النِّسَاءَ؛ فإنَّ أَوَّلَ فِتْنَةِ بَنِي إِسْرَائِيلَ كَانَتْ في النِّسَاءِ. وفي روايةٍ: لِيَنْظُرَ كيفَ تَعْمَلُونَ ".

              رواه  مسلم

    🔹  አቡ ሰዒድ አል ኹድርይ የተባለ ሶሐብይ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል: –

" ዱንያ  ( ሲበሉት) ጣፋጭና ( ሲያዩት ) አረንጓዴ ነው ።  አላህ በሷ ( በዱንያ ) ላይ ምትክ አድራጊያችሁ ነው ። እንዴት እንደምትሰሩ ያያል ። ( በሌላ ዘገባ እንዴት እንደምትሰሩ ሊያይ ተብሏል ) ።  ዱንያን ተጠንቀቁ ሴቶችንም ተጠንቀቁ ። የኢስራኢላዊያን የመጀመሪያ ፈተና በሴቶች ነበር ።

     በዚህ ነብያዊ ምክር የአላህ መልእክተኛ ከዱንያና ከሴቶች እንድንጠነቀቅ መክረውናል ። የአላህ መልእክተኛ ከዛሬ 1400 አመት በፊት የተናገሩት ንግግር ዛሬ ያለውን ሁኔታ ላየ ለዚህ ተውልድ ብቻ ነው ይል ነበር ።

     ከእነዚህ ሁለት ፈተናዎች ለዛሬ አንዱን እንመልከት ።

➡️  የሴቶችን ፈተና : –

    የሴቶች ፈተና ሲባል ብዙ ጊዜ ተራቁተው የሚሄዱ ሴቶች የወንዶችን ደመነፍሳዊ ስሜት በመቀስቀስ የሚያመጡትን ፈተና ነው በሰዎች ልቦና ላይ ውል የሚለው ። ነገር ግን የሴቶች ፈተና ሲባል አድማሱ በጣም ሰፊ አይነቱም ብዙ ነው ። ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑትን ለማየት ያክል የሚከተሉትን ነጥቦች እንመልከት : –

– የሚስት ፈተና

     ከሴት ፈተና ውስጥ ትልቁ ሚና የሚጫወተው የሚስት ፈተና ነው ። ሚስት አላህን የማትፈራ ከሆነች በባልዋ ላይ በብዙ መልኩ ፈተና ትሆናለች ። ከእነዚህ ውስጥ : –

– ትእዛዙን አለመቀበል

     ራስዋን ከሱ እኩል ባለመብት በማድረግ ሌላው ቀርቶ ሶላት እንኳን ስገጂ ሲላት አሻፈረኝ ትላለች ።

– ሐዘን ቢኖር ፈተና ናት ።

– ሰርግ ቢኖር ፈተና ነ ።

– መጣለት ቢኖር ፈተና ናት።

–በንብረት ላይ ባለት አቋም ፈተና ናት ።

– የሱን ቤተሰቦች በማግለል ፈተና ናት ።

– የልጆቿን ስብእና በማበላሸት ፈተና ናት ።

– ክብሯን በማስደፈር ፈተና ናት ።

–  ወሬ በማመላለስ ፈተና ናት ።

– የሌላውን ኑሮ እያየች እቤት ውስጥ ሚጥሚጣ በመሆን ፈተና ናት ። ፈተናዋ ተቆጥሮ አያልቅም ። አላህን የምትፈራ ከሆነች በተቃራኒው የደስታና እርካታ ቁልፍ ናት ።

– የልጅ ፈተና

    አላህን የማትፈራ ሴት ልጅም ፈተና ናት ። ሴት ልጅ አላህን የማትፈራ ከሆነች አላህ የከለከለውን ተግባር በመፈፀም በወላጅዋ ላይ ፈተና ናት ። በአለባበስዋ ፣ በአዋዋልዋ ፣ በአወጣጥዋ ፣ በአገባብዋ ፣ በጓደኛ አያያዝዋ ፣ በየአንዳንዱ እንቅስቃሴዋ ፈተና ናት ።

– የአጅ ነብይ ( ከባዳ ሴት ጋር ) የመቀራረብ ፈተና

     ይሄኛው ፈተና በተለይ በአሁኑ ጊዜ በጣም አስፈሪ ደረጃ ላይ የደረሰበት ሁኔታ ነው ያለው ። በየመንገዱ የሚታየው ፈተና ትተን ዲን አለን ብለው ለዛው ወደ ሱና እንጣራለን በሚሉ ወንድምና እህቶች የባሰ ይመስላል ።

   እንደሚታወቀው ኢስላም አንድን ነገር ሲከለክል ወደዛ ክልክል የሚያዳርሱ ነገሮችንም ክልክል አድርጓል ። ዝሙትን ሲከለክል ወደ ዝሙት የሚያዳርሱ መንገዶችንም ክልክል አድርጓል ።

   ከነዚህ ውስጥ ለሸሪዓዊ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር መተያየትን ፣ መሕረም ያለሆነችን ሴት መጨበጥን ፣ ማንም ሰው ቢሰማው ችግር የሌለው አይነት ንግግር ካልሆ በስተቀር መነጋገርን ፣ ድምፅ ማቅለስለስን ፣ ሁለት ሆኖ አንድ ክፍል ላይ መሆንን ወይም ከወንድ ጋር መቀላቀልንና የመሳሰሉትን ከልክሏል ።

   ይህ ከመሆኑ ጋር በኡኑ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ አማካይነት እነዚህ ሁሉ ክልከላዎች ተጥሰው እናገኛለን ።

    ግሩፕ ይከፈታል ወንድና ሴት ይደበላለቃል ። በዚህ አያበቃም አንድ የሱና ኡስታዝ የተባለን ኡስታዝ በውስጥ መስመር ገብታ ሴቷ ታነጋግረዋለች ‼ ። መጀመሪያ ጥያቄ ነበረኝ ተብሎ ይጀመራል ። ይቀጥላል ምከረኝ ይመጣል ። ምክር ይጀመራል ። ይቀጥላል ድምፅ መነፋፈቅ ይከተላል እየተባለ ወደ ቀይ መስመር ይገባል ።

    በዚህን ጊዜ ሁሉ ኸልዋ ተገኝቷል ማለት ነው ። ምክንያቱም ሁለቱ ከግሩፑ ተነጥለው ወጥተው ዐለመል ጂኒ ውስጥ ባለ ክፍል ውስጥ ሆነው ነው የሚያወሩትና ። በዚህ ጊዜ ምናልባትም ኡስታዙ ሚስትና ልጅ ያለው ይሆናል በዚህም ምክንያት ትዳሩ ሊፈርስ ይችላል ። በሴትዋም በኩል እንደዚሁ ።

    የሚገርመው በዚህ መልኩ ያገኘችውን ወይም ያገኛትን በዛኑ መንገድ ሌላ ሊወስደውና ይሄኛውንም ትዳር ሊያፈርሰው ይችላል ብለው ሳያስቡ ትዳር ብለው መግባታቸው ነው  ። መጨረሻው በሰፈሩበት ቁና መሰፈር ነውና የሚሆነው ።

     ምናልባትም ወደ ትዳር ሳይደርስ በተለይ ኡስታዝ ተብዬው ወይም ዲን አለው የተባለው ጎረምሳ የሷን ላብ አሟጦ የሌሎችንም በርሷ አማካይነት በዲን ስም ሰብስቦ በዛው ሊጠፋ ይችላል ። ይሄኛው በብዛት የሚከሰት ነው ።

    ይህ ሁሉ የሚሆነው ሸሪዓ ከላይ እንዳስቀመጥነው በአጅ ነብዮች መካከል ለሸሪዓዊ ምክንያት ካልሆ በስተቀር መቀራረብን ከልክሎ ሳለ ነው ። ይህ ክልክል የሁለት አጅ ነብዮች ለሸሪዓዊ ምክንያት ካልሆ በስተቀር ስልክ ሴቭ መደራረግን ጭምር ይከለክላል ።

    ይህን አይተን ዛሬ ዱዓቶችና ኡስታዞች ከሚባሉት አብዛኞቹ ያሉበትን ብንመለከት ምን ያክል ከሸሪዓ መራቅ እንዳለ እናያለን ።

   – የሴቶች ፊትና መድረሳዎች አካባቢ :–

      መድረሳዎች አካባቢ ያለው የሴቶች ፊትና የሰለፍዮችን ጀማዓ እስከማፍረስና እስከመበታተን ይደርሳል ። ይህም የሚሆነው ሴቶቹ በኮሚቴዎች መካከል ወሬ በማመላለስና የቤት ውስጥ ችግርን ወደ ጀማዓ በማውጣት ሊሆን ይችላል ። ሌላኛው መድረሳ አካባቢ ባሉ ወንድሞችና ሴቶች መካከል ክልክል የሆኑ ነገሮች ባለመጠንቀቅ በሚደረግ መቀራረብ ይሆናል ። ከዚህም ሲያልፍ ኡስታዙ ከተወሰኑ ሴቶች ጋር በሚኖረው ሸሪዓን የጣሰ መቀራረብ ሊሆን ይችላል ።  ከተማሪዎቹ ውስጥ የተወሰኑትን ስልካቸውን በመያዝ በግል ደውሎ በማዋራትና የመሳሰሉት መንገዶች ።‼

   እነዚህ እንደምሳሌ ማሳያዎች እንጂ መሬት ላይ ያለው ጉድ ከዚህ በጣም የከፋ ነው የራስንም የዲንንም ክብር ለመጠበቅ መጠንቀቁ ይበጃል ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group