UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ወላሂ አውፍ ብያለሁ‼

===============

✍ ዛሬ ኮልፌ መቃብር ተገኝቻለሁ። በቀብር ስነስርዓት ላይ ነውና የተገኘሁት አስቀብረን ስንመለስ አንድ አባት እንባ እየተናነቃቸው የሚያውቁትን ሰው ስም እየጠሩ ይጮሀሉ። አይናቸው ያረፈው እግርጌያቸው ያለው ቀብር ላይ ነው። ቀብሩ ላይ ለስም መፃፊያ በቆመው ድንጋይ ላይ  የሟች ስምና የተቀበረበት ቀን ተጽፎአል።

"ወይኔ ሱሌ፣ ወይኔ ሱሌ እኔ የት ጠፋህብኝ እላለሁ ለካ አንተ እዚህ ነህ? ወላሂ ወላሂ አውፍ ብዬ አለው!" እንባቸው እርግፍ ማለት ጀመረ።

"ወይኔ ሱሌ!" ይላሉ ደጋግመው።

አብሮኝ የነበረው ሱልጣን ወደ እሳቸው ጠጋ ብሎ "የሚያውቁት ቤተሰብ ነው?" ሲል ጠየቃቸው።

"በሥራ አጋጣሚ ነበር የምንተዋወቀው 160 ሺህ ብር አበድሬው ነበር። ለረጅም ጊዜ ጠፋብኝ ደውዬም ማግኝት አልቻልኩም፣ ብድር የወሰደበትን መዝገብ አልፎ አልፎ እየተመለከትኩና ስሙን ከነአያቱ እየጠራሁ የት ገባ እላለሁ?  ወይኔ ወንድሜ ለካ እዚህ መጥቶ ነው? ወይኔ ሱሌ ሁሉን ነገር ይቅር ብያለሁ።"

የሰውየው ሁኔታ ሟች የእሳቸው እድ ሳይከፈል በመሞቱ ሲሰቃይ እያዩ ለማስጣል የሚማጠኑ ይመስላሉ "ወላሂ አውፍ ብዬዋለሁ! ወላሂ አውፍ ብዬአለሁ ! " አሉ ደጋግመው።

ጎናቸው የቆመው ሱልጣን አይኑ እንባ አቀረረ። ሁላችንም በሁኔታቸው ስሜታችን ተነክቷል።

ባለቤትሽ ገንዘቤን ሳይሰጠኝ ሞተ ብሎ እናቴን በሐሰት የከሰታትንና የአባቴን ንብረት በሐራጅ ሊያሸጥ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደረሶ በኋላ አባቴ የከፈለበት ማስረጃ ተገኝቶ ጎዳና ላይ ከመውጣት የተረፍንበት አጋጣሚ ለቅፅበት ታወሰኝ።

የእኚህ ሰው ሁኔታ ደግሞ ፍፁም የተለየ ነው። እንባዬ የአይኔን በር አልፎ ለመውጣት እየተጋለ ነው።

ይባስ ብለው "ያለ አባት የቀሩት ልጆቹ በምን ሁኔታ ይሆን ያሉት? ያሉበትን አፈላልጌ እጠይቃቸዋለሁ ኢንሻአላህ!" ቁጢጥ ብለው ከተቀመጡበት ብድግ አሉ።

ሱልጣን በተቀመጡበት ረስተውት የተነሱትን የመኪናቸውን ቁልፍ አንስቶ ሰጣቸው።

ከዚያ ሰላማዊና ምንም መሆናችን ከሚያስታውሰን

የሙታን ስፍራ ስለ ነገ ሞታችን እያሰብን ወጣን።

እንዲህም አይነት ሰው አለ።»

©: ጀማል አሕመድ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

በተከበሩት ወራቶች ነብሳችንን ከመበደል እንጠንቀቅ!‼

======================================

✍ «ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት በተከበሩት መልእክተኛ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ሁሉ ይሁን። በመቀጠል፤

ያለንበትን የረጀብ ወር በማስመልከት የሚፈፀሙ የቢድዓ ተግባራት ተበራክተዋል። የረጀብን የመጀመሪያ እለት፣ የመጀመሪያ ጁምዓ፣ አስራ አምስተኛውን እለት እንዲሁም ሀያ ሰባተኛውን ቀን ማክበር ቢድዓ መሆኑን፤ በሌሎች ወሮች  እንደሚፈፀሙት የሰኞና ሀሙስ ወይም አያመልቢድ ፃሞች ካልሆነ ወሩን አስመልክቶ የተደነገገ ልዩ ፆምም ይሁን ሰላት እንደሌለ ገልጫለሁ።   ይህ ማለት ግን ረጀብን ከሌሎች ወራቶች የሚለየው ምንም ነገር የለም ማለት አይደለም። 

የረጀብ ወር፤ በሱረቱል ተዉባህ ቁጥር 36  ከተጠቆሙት የተከበሩ አራት ወራት (አሽሁሩል ሁሩም) አንዱ  ነው።

አላህ እንዲህ ይላል፤ 

[إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِنْدَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْراً فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ذَلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ فَلا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنْفُسَكُمْ] التوبة/36 

« አላህ ዘንድ የወሮች ቁጥር፤  በአላህ መጽሐፍ ዉስጥ (በጥብቁ ሰሌዳ ለውሀልማህፉዝ) ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን (የሰየመው) ዐሥራ ሁለት ወር ነው፤ ከነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፤ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፤ በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፤» አልተውባህ 36

عَنْ أَبِي بَكْرَةَ رضي الله عنه عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ( السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ , ثَلاثٌ مُتَوَالِيَاتٌ : ذُو الْقَعْدَةِ وَذُو الْحِجَّةِ وَالْمُحَرَّمُ , وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ) رواه البخاري ومسلم.

ከአቢ በክራህ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «አመት አስራ ሁለት ወራት ነው፤ ከነሱ ዉስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሶስቱ ተከታታይ ሲሆኑ፤ ዙልቂእዳ ዙልሂጃና ሙሀረም ናቸው። ሌላው ደግሞ በጁማዳና በሻዕባን መካከል ያለው የሙደር (ጎሳዎች የታወቁበት)  የ”ረጀብ” ወር ነው።»

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ዙልሂጃ የታወቀው የሀጅ ወር ነው፤ 

ዙልቂዕዳ ደግሞ ሁጃጆች ወደ መካ የሚያቀኑበት ወር ሲሆን፤ 

ሙሀረምም ከሀጅ ስነስርአት በኋላ ሰዎች ወደቀያቸው የሚመለሱበት ወር ነው።  አላህ ረጀብንም ከእነዚህ  የረከበሩ ወራት  አድርጎታል። 

እነዚህ ወራት (የተከበሩ) ናቸው ስንል፤

1- እነዚህ ወረሰቶች ጦርነት የተከለከለባቸው ወራት ናቸው።  

ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ከፈፀመባቸው እራሳቸውን ለመከላከል ብቻ ካልሆነ በስተቀር ውጊያ አይፈቀድም።

2- በነዚህ ወራት አላህ ክልክል ያደረጋቸውን ነገሮች መፈፀም በሌላ ወራት ወንጀልን እንደመፈፀም አይደለም። ስለዚህም አላህ እነዚህን ወራቶች ለይቶ ነብሳችንን እንዳንበድል አሳስቦናል፤ «በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ» ። 

እራስን መበደል አስከፊ መሀይምነት ነው። በአንድ ሰውና በጌታው መካከል የሚፈፀም እራስን መበደል ለአላህ መፈፀም የሚገባን ሀላፊነት አለመወጣት ነው። በራስ ላይ ከሚፈፀሙ በደሎች ሁሉ ትልቁ  በአምልኮ ፍጥረታትን ከአላህ ጋር ማጋራት “ሽርክ" ነው። ሰዎች ላይ የሚፈፀም በደልም ቢሆን የሚጎዳው ሰሪዉን ነውና እራስን መበደል ነው። ለራሱ ያወቀ በማንኛውም ጊዜ ከበደል ይርቃል። 

ኢባደላህ!

አላህ እነዚህን ወራቶች አክብሯቸዋልና እኛም ከፍተኛ ክብር መስጠት ይገባናል። 

እነዚህ ወራቶች ሲገቡ፤ አላህ ክብርን እንደለገሳቸው ልናስታውስና ከወንጀል ለመራቅ ያለንን ቁርጠኝነት ልናድስ ይገባል። ይህ ልባዊ ኢባዳ ነው። 

ወንጀልን በማንኛውም መፈፀም የተከለከለ ቢሆንም በነዚህ ወራት ግን ክልክልነቱ የበረታ ነው።

ስለዚህም ከምንም አይነት ወንጀሎች መጠንቀቅ እና ወደ አላህ መመለስ ያስፈልገናል።   ከትናንሽም ይሁን ከትላልቅ ወንጀሎች በአላህ እንጠበቅ። 

ሸይጣንን እናሸንፍ!

አላህ ከጥፋት ይጠብቀን..

አሚን!!»

©:አኹኩም ፊላህ አቡ ጁነይድ ሳላሕ አሕመድ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አሏህ ይወፍቀን አሚን 4/5/16

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group