Translation is not possible.

አላህ ሰብስቦ ይግደላችሁ!

ከሙሐመድ ሰዒድ (ABX) የተመከርኩት!

በ44 አመቱ ከ50 በላይ መፅሐፍትን ደርሶ ለአንባቢ አቅርቧል:: ህይዎትን ቀለል አድርጎ የተረዳና የሚኖር ሰው እንደሆነ ከገፅታው መረዳት ችያለሁ:: ለመጀመሪያ ጊዜ "ሶባሐል ኸይር!" የሚለው መፅሐፉን ከእርሱ በኩል በተገኘ ስፖንሰርሺፕ ለተማሪዎች አመጣ ዘንድ ከጓደኛጋ በመሆን አገኘሁት:: የጠበኩትና ያገኘሁት ሙሐመድ እጅግ የተለያዩ ነበሩ:: ልስልስ ያለ ዛሂድ መሆኑ ከፊቱ ይነበባል:: "መፅሐፍ ለመውሰድ እዚህ ድረስ በመምጣታችሁ ጎበዝ ናችሁ::" አለን :: ግራ ገባኝ:: እሱ መፅሐፉን ለመፃፍ ስንት ሌሊት ቁጭ ብሎ ውሎ ማደሩ ሳይበቃው የደረሰውን መፅሐፍ ለማከፋፈል ከቤት ቤት እየተዘዋወረ እኛ በነፃ ወስደን ለማንበብ ከእሱ ዘንድ ካልሄድን ምኑን ሰው ነን?" የሚል ጥያቄ በልቦናዬ ውስጥ ተርመሰመሰ :: ብቻ የዚያኔ ከገፅታው ዱንያን በመተውና ጊዜን ለአላህ በመስጠት ውስጥ የሚገኝ ውበት ምን እንደሚመስል ተመልክቼ ተለያየን::

ዛሬ በአላህ ፈቃድ መስጂድ ላይ አገኘሁትና ይመክረን ዘንድ ከጓደኞቼ ጋር በዙሪያው ተቀመጥን:: ምክሩን "አያቴ! አላህ ሰብስቦ ይግደላችሁ!" ትል ነበር በማለት ጀመረ:: በመቀጠልም "ሰብስቦ ስትል ግን በእርሱ መንገድ ላይ ሰብስቦ ለማለት ነው:: አሁን ላይ የወጣቱ ሀሳብ በብዙ መንገድ ተበታትኗል:: በየሶሻል ሚዲያው ተበታትኗል:: ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ነጋ ጠባ የሚሰማው ነገር ደስ አይልም:: ለወደፊትም ደስ አይልም:: በዚህ ውስጥ እናንተ ሀሳባችሁን ወደ አላህ መንገድ መሰብሰብ አለባችሁ:: ለዚህ ደግሞ ለራሳችሁ ቦታ በመስጠት ነገ መሆን ለምትፈልጉት መስዋዕትነት መክፈል አለባችሁ:: እኔ ዛሬ 44 አመቴ ነው:: በእናንተ እድሜ ሆኜ ግን 40 አመት ለእኔ ሩቅ ነበር:: አሁን ላይ ግን የአንድ ቀን ልዩነት እንኳ ያለው አይመስለኝም:: ለእናንተም ተመሳሳይ ነው:: መጪ ነገር ሁሉ ቅርብ ነው:: ሞትም ማለት ነው:: ያለፈ ነገር ደግሞ ሩቅ ነው:: ከስህተታችሁ ተማሩ:: ለወንጀላችሁ ጌታችሁን መሐርታ ጠይቁ:: መሆን የምትችሉትን ትልቁን ለመሆን በመጣር ውስጥ ለመሞት ስሩ:: አላህ በሀሳባችሁ ነው የሚመነዳችሁ:: ተዋብ ነው:: መቶ ሰው ገድሎ ጀነት የገባው ሰው ተውበት በማድረጉ ነው:: በሀሳቡ ነው:: በአላህ መሐርታ ነው::" አለን ::

ከዚህም በተጨማሪ "ንባብ ላይ ተጠናከሩ:: ንባብ ብዙ ነገራችሁን ያሻሽላል:: እኔ ጌታዬ ቢያጎድልብኝ እንኳ ሌላውን ወስዶ አይኔ ለንባቡ እስከኖርኩ ድረስ እንዲያቆይልኝ ዱዓዬ ነው ::" አለን ::

አላህ ሁሉንም ይሙላልህ ያ ሙሐመድ! እድሜውን ያስረዝምልን! ብርታቱን ይስጠው! ብርታቱን ይስጠን!

Send as a message
Share on my page
Share in the group