abdurezak jemal Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Наган дахаан йохтахам.

የዓለም ህዝብ ግን አይገርምም⁉️

=======================

(ዓለም በዚህ ዘመን አይታው የማታውቀው የጦር ወንጀልና የዘር ጭፍጨፋ በጘዝ'ዛ)

||

✍ 365 km² ስፋት ባላት አነስተኛ ከተማ ውስጥ 2.3+ ሚሊዮን ዜጎች ተጠጋግተው ይኖሩባታል። በዚህች densely populated በሆነች ከተማ ላይ ለተከታታይ 3 ሳምንታት ያላባራ ከ12 ሺህ ቶን በላይ ቦምብ ሲዘንብ፤ በዚህም ሳቢያ፦

1) በትንሹ 7,028 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙስሊሞች ሲገደሉ፣

2) ከ70% በላይ የሚሆኑት ህፃናትና ሴቶች ሲሆኑ (2,913 ህፃናትና 1,709 ሴቶች)፣

3) 18,482 የሚሆኑት ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ሲዳረጉ፣

4) ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 481 የሚሆኑት ሲገደሉ (ከመካከላቸው 209 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው።)፣

5) ከ1,650 በላይ የሚሆኑት ጀናዛቸው እንኳ ሳይገኝ እስካሁን ድረስ በቦምብ በፈራረሱት ህንፃዎች ስር ሲሆኑ (ከመካከላቸው 940 ህፃናት አሉበት።)፣

6) 731 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙሉ ቤተሰቦች ሲገደሉ፣

⑦) 101 የጤና ባለሙያዎች ሲገደሉና 100 የሚሆኑት ሲቆስሉ፣

⑧) 12 ሆስፒታሎችና 32 የጤና ማዕከላት በነዳጅ እጥረትና በቦምብ ጥቃት ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ፣

9) በኢንኩቤተር ውስጥ የሚገኙ ከ130 በላይ የሚሆኑ ህፃናት ያሉበት ሆስፒታል ባጋጠመው በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ነፍሳቸው በእንጥልጥል ላይ ሲገኝ፣

⑩) ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ንጹሐን ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች፣ በት/ቤቶች፣ በሆስፒታል ግቢዎች፣ በመስጂዶችና ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ሳለ በዛው ባሉበት ጥቃቱ ሲያገኛቸው…

(ከሰው ነፍስ አይበልጥምና ወደ አመድነት ስለተቀየሩት ውብ ህንፃዎችና መሠረተ ልማቶችማ አውርተን አንዘልቀውም።)

የሰለጠነ ተብዬው ዓለም አሁንም «ጦርነቱ ይቁም!» ከማለት ይልቅ «እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት አላት፣ ሐማስ መጥፋቱን ማረጋገጥ አለባት፣ ከጎንሽ ነን፣ ሐማስ ሽብርተኛ ነው፣ በሐማስ ጥቃት ለሞቱተረ እስራኤላዊያን አዝነናል!…» እያሉ ነው።

ትንሽ አሻሻልን የሚሉት ደግሞ ጦርነቱ መቆም የለበትም፤ ግን የተወሰነች እርዳታ ይግባላቸው ይላሉ።

እስካሁን በጋዛ መብራት የለ፣ ውሃ የለ፣ ምግብ የለ፣ ነዳጅ የለ…። በዚህ የተነሳ የቆሰሉትና መደበኛ ህመም የሚታመሙትም መታከም አልቻሉም።

ዙሪያውን በከበባ ስለሆነ ለጠናበት ታማሚ የውጭ ሕክምና እንዲያገኝ ማድረግ አልተቻለም።

እስራኤል ከላይ በአየር ከምታዘንበው የቦምብ ዝናብ ባሻገር ከምግብና ውሃ እንዲሁም ከሕክምና ከልክላ በጅምላ ጭፍጨፋ የጦር ወንጀልና የዘር ማፅዳት ወንጀል በመፈጸም ላይ ትገኛለች። ይህ ሁሉ የሚሆነው ዓለም እያዬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ተመድ ተብዬውም ሆነ የትኛውም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚል ተቋም ሁሉ የውሃ ሽታ ሆኗል። የነርሱ ህግ እነርሱን ለማዳን እንጂ ለሌላው አይሠራም። እነርሱ ዘንድ የሙስሊም፣ የዓረብና የአፍሪካዊ ሞት ከውሻቸው ሞት በታች ነው።

ግን ነፍስ ሁሉ እኩል ናትና የእጃቸውን አንድ ቀን ማግኘት አይችሉም። ነገ ላይ በሌላ የነርሱ አካል ላይ ጥቃት ሲፈጸም በሚዲያቸውም ሆነ ባልተጻፈው ህጋቸው ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ሲለፍፉ እናገኛቸዋለን።

አላህ ውርደታቸውን ያቅርበው፤ ለተበዳዮች ነስሩን ያፍጥነው።

አላህ የአሸናፊዎች ሁሉ አሸናፊ የሆነ ጥበበኛና ታጋሽ ጌታ ነው። አንድ ቀን አይርላቸውም።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

ለዉዷ ሙስሊም እህቴ

እህቴ በፌስቡክ እና በመሰል መገናኛ ዘዴዎች ተገናኝተሸው አገባሻለው ኒካህ አስርልሻለው ትንሽ ታገሺኝ ብሎ በተስፋ ቃል እየሞላ በሃራም ግንኙነት ዘፍቆሽ የውስጥ ሂጃባሸን ገፎ የሚያባልግሽን፣ ከአላህም ሆነ ከሰው ዘንድ የነበረሽን ክብር እንድታጪ እና እንድትዋረጂ እያደረገሽ ካለ የወንድ ተኩላ እራስሽን መጠበቅ ይኖርብሻል፡፡

ዛሬ አላህን ፈርቶ ከዝሙት መዳረሻ ከሆነው የሃራም ግንኙነት እንድትቆጠቢ ያላገዘሽ ተኩላ ወንድ ነገ አላህን የሚፈራ ባል ይሆነኛል ብለሽ እራሰሽን አታሞኚ፡፡ እስላማዊ ትዳር የሚገነባው አላህ ባዘዘው መልኩ በመጓዝ እንጂ በሃራም ግንኙነት በመጨማለቅ አይደለም፡፡

Abdulaziz Aliiy

ዝሙትን_እንጠየፍ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

•ህመምተኛ እናቷን ለማስታመም በዝሙት ትነግዳለች ።

•ታላላቆቹ ስለሚሰርቁ እርሱም ይሰርቃል።

•በእድሜ ለሚበልጣት ሰው ስለተዳረች ከሌላ ወጣት ጋር ትዘሙታለች ።

•እጁን የሚጠብቁ ልጆቹን ለመንከባከብ ሲል በጉቦና በወለድ ይሰራል ።

•ወላጆቿን አምፃ « ከፍቀረኛዋ» ጋር ትጠፋለች ምክንያቱም «ፍቅር» ከሁሉም ነገር በላይ ስለሆነ።

•አስካሪ እፆችን ለማስገባት ይስማማል ምክንያቱም ጥሩ ገንዘብ ስለሚከፍሉትና ህይወት ደግሞ እድል ስለሆነች።

•ከቤተሰቧ ተደብቃ ከ«ፍቅረኛዋ» ጋር ትገናኛለች፣ ነፍሷንም ትፈቅደለታለች– ምክንያቱም ስለምታምነው።

•አባቱን አይታዘዝም ምክንያቱም አባቴ በልጅነቴ አልተንከባከበኝም ብሎ ስለሚያምን ።

•ባሏ ፍቅር ስላልሰጣት በባሏ ላይ የአጎቷን ልጅ ታፈቅራለች።

የቱርክ፣የሳኡዲ፣የኳታር፣የግብፅ ፣የኢትዮጲያ .... አጠቃላይ የዓለም ተከታታይ ድራማዎች (ሙሰልሰላት) እና ፊልሞች በሙስሊሞች ልቦና ውስጥ ማስረፅ የሚፈልጉት እሳቤ ይህ ነው። አላህን የሚያምፅ ሰው እርሱን የሚያምፅበት በቂ ምክንያት አለው ብለን እንድናስብ ማድረግ።

በዚህም ሰዎች ሐራም ላይ (ዝሙት፣ስርቆት፣ክህደት፣ማጭበርበር ወዘተ) ላይ ሲወድቁ አሳማኝ ምክንያት ይኖራቸዋል ብሎ ጀስቲፋይ የሚያደርግ ትውልድ እንዲፈጠር ማድረግ ችለዋል። ፈፃሚውን ማስታመም ስንጀምር ድርጊቱ በቀልባችን ውስጥ ወንጀልነቱን ዝቅ አድርገን እናየዋለን። አላህ ይጠብቀንና ወንጀልነቱን ዝቅ ያደረግነውን ነገር ደግሞ ለመዳፈር እንቀርባለን።

አላህ እንዲህ ይላል፦

«አላህም በእናንተ ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል፡፡ እነዚያም ፍላጎታቸውን የሚከተሉት (ከውነት) ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ፡፡» (አን ኒሳእ 27)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Наган дахаан йохтахам.

አራት ወሳኝ የሪዝቅ ሰበቦች

➖➖➖➖➖➖➖➖➖

💦ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

✅ አራት ነገራቶች መልካም ሪዝቅ (ሲሳይ) አብዝተው እንዲመጣ ያደርጋሉ። እነሱም፦

①) ሌሊት መቆም (ሌሊት ተነስቶ መስገድ)

②) የሌሊቱ መጨረሻ አካባቢ እስቲግፋር ማብዛት

③) ሰደቃ ማብዛትና

④) የጠዋትና የማታ ዚክር ናቸው።

📚 زاد المعاد (372/4)

Send as a message
Share on my page
Share in the group