UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ሩሕህ ወጥታ በድን ሁነህ ቤተሰቦችሁ ሲጯጯሁ ሙስሊም ወንድሞችህ

አልያም እድርተኛህ ከፍኖህ ከምድር ታች ማንም የማያይህ ቦታ ሊቀብሩህ

ይወስዱኃል።

ጀናዛህን ለመሸኘት ከቦታው የተገኙ ሰዎች እንደ እቃ በተጠቀለልክበት

እየተቀባበሉ በር እንጂ መስኮት ከሌለው የቀብር ቤት ውስጥ አስገብተውህ

መውጫ ቀዳዳ እንዳይኖር አድርገው ከከረቻቸሙብህ በኋለ አፈሩን እየተረባረቡ

ይደፉብኃል።

አንተን እሚያህል ክቡር ሰው ከጉድጓድ ወርውረው መቆፈርያ እና አካፋዎቻቸውን

ይዘው በጥድፍያ ከቦታው ይሄዳሉ።

ለዘመናት ይፎክርብህ የነበረው ቀብርም ዛሬ ለብቻህ አግኝቶህ ፉከራውን

በተግባር ሊያስቃኝህ አንድ ግዜ በሀይል ከሁለት በኩል ያላትምኃል።(ሙእሚን

መሆንህ ግድ አይሰጠውም)

ትነቃለህም።

በከፈን ተጠቅልለህ ቀብር ውስጥ መክተምህን፣ ዘመድ አዝማድህን ዳግም

ላትገናኝ መለያየትህንም ትረዳለህ። ፅልመቱ ያርድኃል፣ ጭርታው ያደነዝዝኃል፣

ብቸኝነቱ መላ አንተነትህን በፍርሀት ይቆጣጠርኃል።

ማዕዘናቱን በማትመለከትበት በፀሊሙ ጉድጓድህ ተጋድመህ በፍርሀት

ስትብሰለሰል ድንገት አንዳች ዱብዳ የወረደ ይመስል ያለህበት ጉድጓድ

በመብረቅ ነጎድጓድ መሰል ድምፅ ይጠለቀለቃል።

ትበረግጋለህ፣ ትውረገረጋለህ፣ ትንዘፈዘፋለህ...ግና መሸሻ የለህም። ዘመድ

አዝማዶችህ በከፈን ከፍነው እጅ እግርህን ጠፍረው ማምለጥ እንዳትችል

ከጉድጓድ ከተው በሩን ዘግተውብኃላ! ወዴት ትሸሻለህ!?

ያን አስፈሪ ድምፅ ሲያወጡ የነበሩት ፍጥረታቱም ድንገት ከፊትህ ተከስተው

ከተጋደምክበት አንስተው ያስቀምጡኃል።

ልታያቸው ስትሞክር የእሳት ፍም ይመስል ቀልቶ እሚፍነገነግ አይናቸው ላይ

አይንህ ያርፋል፣ ፈርተህ ብታጎነብስ የጥፍራቸው ርዝመት በፍርሀት

ያንቀጠቅጥኃል።

ገና ሳይናገሩ ከአፋቸው የሚወጣው የጭስ ነበልባል ንግግራቸው ምን ያህል

እንደሚከብድ ከወዲሁ ያሳብቃል።

የመብረቅ ነጎድጓድ በሚመስለው ድምፃቸው ድንገት ባለሰብክበት፦‹‹ጌታህ

ማን ነው?›› ብለው ያስበረግጉኃል። ምላሹን እያወቅክ ንግግር ይጠፋኃል።

አንተነትህ አንደበትህን መቆጣጠር ተስኖት ታለከልካለህ።

ጠያቂዎችህ ከፀሊሙ ክፍልህ ሁነህ ምላሽህን እያፈጠጡ በመጠባበቅ ላይ

ሳሉ ድንገት የጌታህ የእዝነት ፅናት ያገኝህ ና፦‹‹ጌታዬ አላህ ነው›› ብለህ

ትመልሳልህ።

ጥያቄውን የሳትክ ይመስል እያዋከቡህ ዳግም በጩኸት ያንኑ ጥያቄ

ይጠይቁኃል። እማትቋቋመውን ትዕይንት በረበል አለሚን ፅናት ታግዘህ፦‹‹ጌታዬ

አላህ ነው›› በማለት ዳግም ትመልስላቸዋለህ።

ሀሳብ በሚበትነው ድምፃቸው እየጩኹ፦‹‹ሀይማኖትህ ምንድነው›› ብለው

ያጓሩብኻል።

መለኮታዊ ፅናቱ አካብቦኃል፣ ፍርሀቱን መቋቋም ባትችል እንኳ ለምላሾችህ ፅናት

አለህ። ለጩኸታዊው ጥያቄም በሰከነ ልሳን፦‹‹ሀይማኖቴ ኢስላም ነው››

ትላለህ።

ያምታቱብኃል፣ እርግጠኛ መሆንህን ለማረጋገጥ ናላህ እስኪናወዝ ጥያቄውን

በመደጋገም ይጠይቁኃል። ፅናቱ አልተለየህም ና በምላሽህ ትፀናለህ።

የምላሾችህን ትክክለኛነት እና ስህተት ሳያረጋግጡልህ ቀጣዩን ጥያቄ በጩኸት

ይጠይቁኃል፦‹‹ያ ወደ እናንተ የተላከው ሰውዬ ማን ነው?››

ነፍስህ በዘመናት ናፍቆት ስትዋልልበት የነበረው ያ ሰው ይታወስኃል፣ የሰው ልጅ

አይነታ፣ የነብያቱ ጌጥ፣ የፍጡር ምክንያት፣ የፍቅር ተምሳሌት፣ ሳይታይ

ሚናፈቅ...ያ ሙሐመድ ትዝ ይልኃል።

‹‹ያ ሰው ሙሐመድ ነው›› ትላለህ።

በዱንያ ህይወትህ በናፍቆት እንዳላነባህ ሁላ ዛሬ ላይ እንደ ወዛ ‹‹የት

ታውቀዋለህ?›› ተብለህ ትጠየቃለህ።

‹‹መፅሀፉን አነበብኩ አመንኩበትም›› ስትል ትመልላቸዋለህ። የምላሽህን

ሰሌዳ ጠቅለለው ሳይጨርሱ፦‹‹ባርያዬ ዕውነት ተናገረ! ገጀነት የሆነን ፍራሽ

ፈርሹለት፣ ከጀነት የሆነን ልብስም አልብሱት፣ የጀነትንም በሮች ክፈቱለት››

የሚል ድምፅ ከጌታህ አውራጃ ይደመጣል። ትዕዛዛቱም ላንተ ክብር ተፈፃሚ

ይሆናሉ።

አንተም ከቀብርህ ውስጥ ከተዘጋጀልህ የጀነት ጨፌ እየተዝናናህ ቂያማን

እንድትጠብቅ ይደረጋል። የጌታህም ፀጋ ያን ቀን አንተ ላይ ሙሉ ይሆናል።

ያም እሚሆነው አንተ ሙስሊም ስትሆን ብቻ ነው!!!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group

Abdlkerim Kemal Mohammed Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group