UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አንዲት ሴት ባሏ ካልሆነ ወንድ ብትወልድ እና ወንዱ ከተቀበለ ልጁ ወደሱ ይጠጋልን?

~

ብዙሃኑ ዑለማእ "ልጅ ለባለ ፍራሽ ነው" የሚለውን ሐዲሥ በመያዝ ልጁ ወደዚህ ሰው እንደማይጠጋ ይገልፃሉ። ከፊል ዓሊሞች ግን የኔ ነው ባይ ተቃዋሚ እስከሌለና ሰውየው እስካመነ ድረስ ልጁ ወደሱ መጠጋት ይችላል ይላሉ። ይሄ አቋም የኢስሓቅ፣ የሐሰኑል በስሪይ፣ የሱለይማን ብኑ የሳር፣ የዑርዋህ ብኑ ዙበይር አቋም ነው። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እና ኢብኑል ቀዪምም ይህንን ነው የመረጡት። ምክንያቱም:-

1ኛ፦ ሰውየው በተጨባጭ የልጁ አባት ነው። ማለትም ከሱ ነው የተገኘው። የጁረይጅ ሐዲሥ ላይ ከዝሙት የተገኘውን ህፃን "አባትህ ማነው?" ሲለው "እረኛው እከሌ ነው" በማለት ከእናቱ ጋር ዝሙት የፈፀመውን ሰው ነው የተናገረው። [ቡኻሪ፡ 3436] [ሙስሊም፡ 2550]

2ኛ፦ ከዝሙት ከመገኘቱ ጋር እናቱ እናት ተደርጋ እንደምትቆጠረው አባትም ላይ ተቃዋሚ እስካልመጣ ድረስ እንደ አባት ከመቆጠር የሚከልክል የለም።

(ልጅ ለባለ ፍራሽ እንጂ ለዝሙተኛ አይደለም) የሚለውን ማንሳት የሚቻለው ልጁ የኔ ነው ባይ ተቃዋሚ ባለቤት ሲኖር ነው። ይሄ በሌለበት ሁኔታ ወላጁን የልጁ አባት አይደለም የሚለው ከመረጃ አንፃር ልክ አይሆንም። ወላሁ አዕለም።

ዝርዝር የፈለገ የኢብኑል ቀዪምን ዛዱል መዓድ፡ [5/425] ይመልከት።

Ibnu Munewor

=

የቴሌግራም ቻናል፡-

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor
t.me

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

4 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group