Translation is not possible.

•ህመምተኛ እናቷን ለማስታመም በዝሙት ትነግዳለች ።

•ታላላቆቹ ስለሚሰርቁ እርሱም ይሰርቃል።

•በእድሜ ለሚበልጣት ሰው ስለተዳረች ከሌላ ወጣት ጋር ትዘሙታለች ።

•እጁን የሚጠብቁ ልጆቹን ለመንከባከብ ሲል በጉቦና በወለድ ይሰራል ።

•ወላጆቿን አምፃ « ከፍቀረኛዋ» ጋር ትጠፋለች ምክንያቱም «ፍቅር» ከሁሉም ነገር በላይ ስለሆነ።

•አስካሪ እፆችን ለማስገባት ይስማማል ምክንያቱም ጥሩ ገንዘብ ስለሚከፍሉትና ህይወት ደግሞ እድል ስለሆነች።

•ከቤተሰቧ ተደብቃ ከ«ፍቅረኛዋ» ጋር ትገናኛለች፣ ነፍሷንም ትፈቅደለታለች– ምክንያቱም ስለምታምነው።

•አባቱን አይታዘዝም ምክንያቱም አባቴ በልጅነቴ አልተንከባከበኝም ብሎ ስለሚያምን ።

•ባሏ ፍቅር ስላልሰጣት በባሏ ላይ የአጎቷን ልጅ ታፈቅራለች።

የቱርክ፣የሳኡዲ፣የኳታር፣የግብፅ ፣የኢትዮጲያ .... አጠቃላይ የዓለም ተከታታይ ድራማዎች (ሙሰልሰላት) እና ፊልሞች በሙስሊሞች ልቦና ውስጥ ማስረፅ የሚፈልጉት እሳቤ ይህ ነው። አላህን የሚያምፅ ሰው እርሱን የሚያምፅበት በቂ ምክንያት አለው ብለን እንድናስብ ማድረግ።

በዚህም ሰዎች ሐራም ላይ (ዝሙት፣ስርቆት፣ክህደት፣ማጭበርበር ወዘተ) ላይ ሲወድቁ አሳማኝ ምክንያት ይኖራቸዋል ብሎ ጀስቲፋይ የሚያደርግ ትውልድ እንዲፈጠር ማድረግ ችለዋል። ፈፃሚውን ማስታመም ስንጀምር ድርጊቱ በቀልባችን ውስጥ ወንጀልነቱን ዝቅ አድርገን እናየዋለን። አላህ ይጠብቀንና ወንጀልነቱን ዝቅ ያደረግነውን ነገር ደግሞ ለመዳፈር እንቀርባለን።

አላህ እንዲህ ይላል፦

«አላህም በእናንተ ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል፡፡ እነዚያም ፍላጎታቸውን የሚከተሉት (ከውነት) ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ፡፡» (አን ኒሳእ 27)

Send as a message
Share on my page
Share in the group