UMMA TOKEN INVESTOR

kedeir shukur shared a
Translation is not possible.

ያሳዝናል‼

========

✍ የአማራ ክልል ሙስሊም ማኅበረሰብ አሁን ያለበት አጣብቂኝ ተጨባጭ ያሳዝናል።

በአንድ በኩል «ዐቢይ አሕመድ ሙስሊም ነው፤ የዚህ እስላም መንግስት ደጋፊና ተላላኪ ነህ፤ ካልሆንክ ከኛ ጋር ዝመትና ተዋጋ!» ተብሎ ያለ ወንጀሉ ይታገታል፣ ይዘረፋል፣ ይደበደባል፣ አለፍ ሲል ደግሞ በዘግናኝ ሁኔታ ይገደላል።

በሌላ በኩል ራሱን እንዳይከላከል እንኳ የመንግስት መከላከያ በጥርጣሬ ዓይን ሙስሊሙን ተመልክቶ ፋኖ የተሰኘው ኃይል ከዘረፈው የተረፈውን መሳሪያ ወስዶባቸዋል።

በሞጣ፣ በባህር ዳርና አካባቢዋ፣ በጎንደር፣ በወሎ፣ በሸዋ… አላስፈላጊ ጫና ውስጥ ይገኛል።

በተለይም በጎጃምና በጎንደር ከባድ አጣብቂኝ ውስጥ ነው። የጎጃም ኃይል በዚያ አካባቢ አንድም ሙስሊም በሰላም መኖር የለበትም የሚል እቅድ ያነገበ ይመስል፤ ሰሞኑን በባህር ዳርና በምስራቅ ጎጃሟ ሞጣ ተከታታይ እገታና የግድያ ወንጀል በመፈፀም ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለትም ወንድማችን ገደፋው ሐሰንን ሞጣ ላይ ገድለውታል።

መንግስት ይህንን ሰላማዊ ሙስሊም ማኅበረሰብ ደህንነቱን ማስጠበቅ አልቻለም። አቅም አጥቶ ነው እንዳንል በቦታው የመንግስት ኃይሎች ይታያሉ። የሙስሊሙን ህጋዊ መሳሪያ ከመግፈፍ ንጹሐኑን ሙስሊም እያገተና እየገደለ የሚገኝን ጽንፈኛ ኃይል ስርዓት ማስያዝ ይበልጥ ነበር።

አሁንም ቢሆን የሚመለከተው የመንግስት አካል በዚያ አካባቢ የሚገኝን የራሱን ኃይል ጭምር ፈትሾ የክልሉን ሙስሊም ማኅበረሰብና ሰላማዊ ዜጋ ደህንነትና ህልውና ሊያስጠብቅ ይገባል።

የዚህ ክልል ሙስሊም በክልሉና ከክልሉ ውጭ በሁለት ቢላዋ መታረዱ የሚቆምበት ጊዜ ይናፍቃል። አላህ ሰላሙን ይመልስለትና!

አሁንም እንላለን፤ ፍትሕ ለአማራ ክልል ሙስሊሞች‼

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
kedeir shukur shared a
1 month Translate
Translation is not possible.

በቅርቡ እስልምና የተቀበለው ወንድማችን በኢስላም / ዳውድ ኪም Daud Kim በደቡብ ኮሪያ ኢንቼዮን ከተማ መስጅድ ለመገንባት የቦታ ውል ተፈራረመ ይህ ቦታ በቅርቡ መስጂድም ይሆናል።

ዴቪድ ኪም ይለናል

"የዛሬን ቀን ማመን አልችልም...

ኮሪያውያንን ለመጋበዝ የመስገጃ ቦታ እና ኢስላማዊ ፖድካስት ስቱዲዮ ለመገንባት እያሰብኩ ነው።

ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች ይኖራሉ ግን እንደምችል አምናለሁ

የኮሪያ ጎዳናዎች ሁሉ በሚያምር የአዛን ድምፅ እስኪሞላ ድረስ

የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ።"

"አላህን ፅናቱንና ስኬቱን እንጠይቀዋለን"

መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!

የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇

https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
kedeir shukur shared a
Translation is not possible.

🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸

"በሶስት ልጆቼና በሶስት

የልጅ ልጆቼ ሸሒድነት

አላህ አላቀን"

የሐመሱ መሪ ዒስማኢል ሀኒያ

ሐዘኑን ዋጥ አድርጎ ሲናገር

🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸

#gazagenocide

#israelaterroriststate

1 view
Send as a message
Share on my page
Share in the group
kedeir shukur shared a
Translation is not possible.

🌹ሚስት ለባሏ ማድረግ የሚጠበቅባት 15 ነገሮች 🌹

ኢማሙ ዘሀቢይ እንዲህ አሉ፦

አንዲት ሚስት ለባሏ መድረግ ከሚጠበቅባት ነገሮች መካከል ፡

1. ሁሌም ከርሱ ሀያዕ ሊኖራት ይገባል

2. እርሱ ፊት ስትሆን አይኗን መስበር አለባት

3. የርሱን ትዕዛዝ እሺ ብላ መታዘዝ አለባት

4. እርሱ በሚናገር ሰአት ፀጥ ማለት አለባት

5. እርሱ ከውጭ ወደቤት በሚገባ ጊዜ ቁማ መቀበል አለባት

6. እርሱን ከሚያስቆጡ ነገሮች ሁሉ መራቅ አለባት

7. እርሱ ከቤት በሚወጣ ጊዜ ሲቆም አብራው ቁማ ልትሸኘው ይገባል

8. እርሱ ልክ ማታ ላይ ሊተኛ ሲል ነፍሷን ልታቀርብለት ይገባል (ማለትም ያን ነገር ማድረግ ሚፈልግ ከሆነ ይሄው አለሁልህ ... ሃሃ)

9. እርሱ ከቤት ወይንም ከሀገር በሚርቅ ጊዜ ክብሯን፣ ገንዘቡን እና ቤቱን በስርአት መጠበቅ አለባት / በዚህ ነገር ላይ ፈፅሞ ክህደት ልትፈፅምበት አይገባም

10. ሁሌም ጥሩ ጠረን ሽታ ሊኖራት ይገባል

11. አፏንና ጥርሶችዋን ሁሌም በሲዋክ ልትቆጣጠር ይገባል

12. እርሱ ፊት ሁሌም በቻለችው አቅም ውብ ሁና ልትገኝ ይገባል

13. ሀሜትን በጣም ልትጠነቀቅ ይገባል / ከርሱም ርቃ ልትቀመጥ አይገባም

14. ቤተሰቡንና የቅርብ ዘመዶቹን ልታከብርለት ይገባል

15. እርሱ የሚውልላትን ጥቂት ነገር ልክ ትልቅ ውሌታ እንደዋለላት አድርጋ ልትቆጥር ይገባል ።

ምንጭ፦ ኪታቡል ከባኢር (66/1)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
kedeir shukur shared a

~ሸይኽ አልባኒ(ረሒመሁሏህ) በሸሪዐው ከሚወገዙ የሴት ስሞች ብለው ከጠቀሷቸው ስሞች ዉስጥ ሲሃም አንዱ ነው። አንዳንዶች ሱሃም ሌሎች ሰሀም ነው የተከለከለው ይላሉ። ትርጉሙም ጦሮች፣ ቀስቶች፣ መርዞች ወይም ደግሞ የግመል በሽታ ማለት ነው። እንድህ አይነት ጥሩ መልእክት የሌላቸው ስሞች ደግሞ በሸሪዐው ይወገዛሉ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group