Çeviri imkansız.

ያሳዝናል‼

========

✍ የአማራ ክልል ሙስሊም ማኅበረሰብ አሁን ያለበት አጣብቂኝ ተጨባጭ ያሳዝናል።

በአንድ በኩል «ዐቢይ አሕመድ ሙስሊም ነው፤ የዚህ እስላም መንግስት ደጋፊና ተላላኪ ነህ፤ ካልሆንክ ከኛ ጋር ዝመትና ተዋጋ!» ተብሎ ያለ ወንጀሉ ይታገታል፣ ይዘረፋል፣ ይደበደባል፣ አለፍ ሲል ደግሞ በዘግናኝ ሁኔታ ይገደላል።

በሌላ በኩል ራሱን እንዳይከላከል እንኳ የመንግስት መከላከያ በጥርጣሬ ዓይን ሙስሊሙን ተመልክቶ ፋኖ የተሰኘው ኃይል ከዘረፈው የተረፈውን መሳሪያ ወስዶባቸዋል።

በሞጣ፣ በባህር ዳርና አካባቢዋ፣ በጎንደር፣ በወሎ፣ በሸዋ… አላስፈላጊ ጫና ውስጥ ይገኛል።

በተለይም በጎጃምና በጎንደር ከባድ አጣብቂኝ ውስጥ ነው። የጎጃም ኃይል በዚያ አካባቢ አንድም ሙስሊም በሰላም መኖር የለበትም የሚል እቅድ ያነገበ ይመስል፤ ሰሞኑን በባህር ዳርና በምስራቅ ጎጃሟ ሞጣ ተከታታይ እገታና የግድያ ወንጀል በመፈፀም ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለትም ወንድማችን ገደፋው ሐሰንን ሞጣ ላይ ገድለውታል።

መንግስት ይህንን ሰላማዊ ሙስሊም ማኅበረሰብ ደህንነቱን ማስጠበቅ አልቻለም። አቅም አጥቶ ነው እንዳንል በቦታው የመንግስት ኃይሎች ይታያሉ። የሙስሊሙን ህጋዊ መሳሪያ ከመግፈፍ ንጹሐኑን ሙስሊም እያገተና እየገደለ የሚገኝን ጽንፈኛ ኃይል ስርዓት ማስያዝ ይበልጥ ነበር።

አሁንም ቢሆን የሚመለከተው የመንግስት አካል በዚያ አካባቢ የሚገኝን የራሱን ኃይል ጭምር ፈትሾ የክልሉን ሙስሊም ማኅበረሰብና ሰላማዊ ዜጋ ደህንነትና ህልውና ሊያስጠብቅ ይገባል።

የዚህ ክልል ሙስሊም በክልሉና ከክልሉ ውጭ በሁለት ቢላዋ መታረዱ የሚቆምበት ጊዜ ይናፍቃል። አላህ ሰላሙን ይመልስለትና!

አሁንም እንላለን፤ ፍትሕ ለአማራ ክልል ሙስሊሞች‼

||

t.me/MuradTadesse

image
Mesaj olarak gönder
Sayfamda paylaş
Grupta paylaş