IbnuTemam Mohammed Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

ተመጣጣኝ ካልሆነ አካል ጋር ውጊያ ማካሄድ እና ሐማስ

በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

#islam

2 views
1 view
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

#ወሳኝ_ዱዓዕ

~~~~~~~

የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ይሉ ነበር

አላህ ሆይ ላንተ እጅ እግሬን ሰጥቻለሁ፣ በአንተም አምኛለሁ፣

በአንተ ላይ ተመክቻለሁ፣ ከሰራሁት ወንጀል ወደ አንተ ተመልሻለሁ፣ ባአንተም ተከራክሬለሁ፣ አላህ ሆይ በአሸናፊነትህ እጠበቃለሁ ከአንተ ውጭ በእውነት የሚመለክ የለም ከትክክለኛው ጎዳና እንዳታስወጣኝ(እንዳታጠመኝ)

አንተ ህያው ነህ አትሞትም

ጅኖች እና የሰው ልጆች (ግን) ይሞታሉ(ሞትን ይቀምሳሉ)

#ምንጭ [ሙስሊም]

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

🛑 ታላቅ የምስራች

🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

📌 https://onelink.to/quvuv3

በሀገራችን ፋና ወጊ የሆነውንና የመስገጃ ቦታዎችን የሚያመላክት መተግበሪያ(Application) ይፋ ሆነ!

አፕሊኬሽኑ "Musalla" የሚሰኝ ሲሆን ለአንድሮይድና ለ IPhone (IOS) ተጠቃሚያዎች የተዘጋጀና መተግበሪያው በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በአረብኛና በእንግሊዘኛ ቋንቋ አማራጮች መስራት የሚችል ነው።

🚩 አፕሊኬሽኑ ዋና ዋና መስጂዶችን ፣ በንግድ ማዕከላት እና በሆቴሎች ውስጥ የሚገኙ መስገጃ ቦታዎችን የት እንደሚገኙ ይጠቁማል

🚩 በመስገጃ ቦታዎቹ ውዱእ ማድረጊያ ቦታ መኖሩን እና አለመኖሩን ይገልፃል

🚩መስጂዶቹ የሴቶች መስገጃ ቦታ እንዳላቸው እና እንደሌላቸው ይገልፃል

🚩 ከተማው ውስጥ የሚገኙ የቀብር ቦታዎችን፣ የመጅሊስ ፅህፈት ቤቶችንና ቂብላ ይጠቁማል። እንዲሁም የመስጂዶችን አድራሻ በቪዲዮና በምስል ጭምር ማሳየት የሚችል አፕሊኬሽን ነው ይፋ የሆነው።

የፈጠራው ባለቤቶች በነሱ አቅም ማካተት የቻሏቸውን መስጂዶች ያሰገቡ ቢሆንም እርሰዎ ክፍለ አገርም ሆኑ አዲስ አበባ በየጉራንጉሩ ያሉ የሚያውቋቸውን መስጂዶች እና ተያያዥ መረጃዎች በአፕሊኬሽኑ ውስጥ ማስገባት እንዲችሉ ክፍት ተደርጓል። በጣም ደስ የሚለው ነገር ያልተካተቱ መስጂዶችን እርሰዎ ካስገቡ በኋላ አፕሊኬሽኑ ላይ ባስገቡት መስጂዶች ላይ ሰዎች ሲገለገሉ ለእርሰዎ ይኼን ያህል ሰው በመስጂዱ ሰግዷል የሚል ብዙ ምንዳ የሚያዝቅ መረጃ በየጊዜው ይልክልዎታል።

አፕሊኬሽኑን ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ አውርዳችሁ መጠቀም የምትችሉ ሲሆን ሌሎች እንዲጠቀሙበትም ሼር በማድረግ እንድታጋሩ እንጠይቃለን።

የአፕሊኬሽን መገኛ ሊንክ:- https://onelink.to/quvuv3

የቲክቶክ አድራሻቸው 👉 https://t.ly/i8Tkc

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

መምከሩን ምከር ነፍስህን ግን አትርሳ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَثلُ الَّذي يُعلِّمُ النّاسَ الخيرَ وينسى نفسَه، كمثَلِ السِّراجِ؛ يُضِيءُ للنّاسِ ويحرِقُ نفسَه﴾

“ያ! ሰዎችን በመልካም እያሳወቀ (እየመከረ) ነፍሱን የሚረሳ ምሳሌው ልክ እንደ ፋኖስ (ሻማ) ነው። ለሰዎች እያበራ እራሱ እንደሚቀልጠው።”

📚 ሶሂህ አተርጊብ: 131

#islam

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

240 ነፍስ Vs 2.4 ሚሊዮን ነፍስ‼

========================

✍ የምዕራቡ ዓለምና ከፊል የአውሮፓው ዓለም ወራሪዋን ከጀርባ በሎጂስቲክስ እየደገፈ፤ በሐማስ ታስረውብኛል ያለቻቸውን 240 ሰዎች ለማስለቀቅ 2.4 ሚሊዮን ህዝብ በከበባ እስር ቤት ውስጥ አድርጋ እስካሁን ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ገድላለች። ከነዚህ መካከል ከ4,100 በላይ የሚሆኑት ጨቅላ ህፃናት ናቸው። ከ2, 600 በላይ ሴቶች ተገድለዋል፣ 26,000 ገደማ ቁስለኞች ሆነዋል። በተለይ ከትናንት ጀምሮ ሆስፒታሎች የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል።

56 መስጂዶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፣ 136 የሚሆኑት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ተጨማሪ 3 ቤተ ክርስቲያናት ወድመዋል።

40 ሺህ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ ከ222 ሺህ በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ ውድመት ደርሶባቸዋል።

47 ጋዜጠኞች፣ 53 የመስጂድ ኢማሞችና ዳዒዎች ተገድለዋል።

ይህ ሁሉ የሆነው የታገቱ 240 ሰዎችን ለማስለቀቅ ነው ተብሎ ጀስቲፋይ እየተደረገ ነው።

የታገቱትን ያለ ውጊያ በድርድር እንሰጣለን እየተባለ ባልሰማ ጭፍጨፋውን መቀጠሏ፤ ጋዛ ወደተለመደው በወረራ ወደያዘቻቸው ግዛቶቿ አጠቃላ ከቻለች ነዋሪዎቿን ወደ ግብፅ የሲናይ በረሃ ማሰደድ፣ በመቀጠልም ዛሬውኑ የጀመረቻቸውን የዌስት ባንክ፣ ረምላህ፣ እየሩሳሌምና ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ ፈለስጢናዊያንን ሙሉ በሙሉ አስወጥታ ከወንዙ እስከ ባህሩ የነበረውን የቀድሞ የፈለስጢን ግዛት ማጠቃለል ነው ህልሟ። ይህን ካሳካች በኋላ ደግሞ ሌሎች የዓረብ ሃገራት ተረኞቹ ፈለስጢን መሆናቸው ላይቀር ይችላል።

ገና ከወዲሁ ተረባርበው ይህቺን ነቀርሳ ከመሃላቸው መንቀል ሲገባቸው፤ እነርሱ ግን የነቁና የገባቸው አይመስልም። አላህ ያንቃቸውና!

ጋዛዊያንን ማፈናቀል ካልቻለች ግን ቢያንስ እንደ ሌሎቹ ክፍሎች ጨቁናና ረግጣ ለማስተዳደር ትፈልጋለች።

እየሆነ ያለው ነገር ያሳዝናል። ደም ጠጪዎቹ እነ አሜሪካ የሟቾች ቁጥር ስንት ሲደርስ እንደሚረኩ እስካሁን አልታወቀም።

አላህ ሆይ! ካንተ ውጭ መጠጊያ የለንምና ደካማ ባሮችህን በጥበብህ እርዳቸው፤ በጠላቶቻቸው ላይ ድልን አቀዳጃቸው፤ የመከራና የጨለማ ሌሊቶቻቸውን ከዚህ በላይ አታርዝምባቸው፤ ለሞቱት ሸሂድነትን፣ ላሉት ድልንና ሰላምን ከሶብርና ጽናት ጋር ወፍቃቸው።🤲

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group