አላህ ሆይ ረጅም እድሜን እንጠይቅሀለን። የዐፊያውን ሸማ ደርብልን። የኢማኑን ለዛ አጎናጽፈን። አንተን የምንፈራበት ጉልበት ስጠን። ዒልሙን እና ማዕሪፋውን አስታጥቀን። ከግራር ሥር የጠነከረ ትዕግስት አላብሰን። ሐላል በሆነ የኃብት ባህር እጠበን። አግኝቶ ከማጣት ደብቀን። ከድህነት እና ሥጋት ገላግለን። የመስጠትን ጣዕም ወፍቀን። ከጠላት ተንኮል አርቀን። በሰዎች ላይ እኩይ ከማሰብ እና መጥፎ ከመስራት አቅበን። ባንተም ሆነ በፍጡራኖችህ ዘንድ ተወዳጆች አድርገን። «ይኼ ቀረን» የምንለው ነገር ሁሉ ከእጃችን ገብቶ «የቀረን የለም» የምንልበትን አንደበት ስጠን።
ኢላሂ!
የትዳር ዓለም አቀበት የሆነበትን ሁሉ ለጥ ያለ ሜዳ አድርገህ አግራለት። ወልዶ ለመሳም ያልቻለውን ሁሉ በልጆች ጸጋ አንበሽብሸው። የአብራክ ክፋዮቻችንን ፍሬው የበዛ የበረካ ዛፍ አድርጋቸው።
አዛኙ ጌታችን ሆይ!
ትከሻችን ሊሸከመው ከማይችል የፈተና አይነት አርቀን። ነውሮቻችንን ሁሉ ሸፍነህ ኬላውን አሻግረን። ከወላጆች ሐቅ ጠብቀን። ከአደናቃፊ እና ከድንገተኛ ሞት ሰትረን። ዱንያን ስንሰናበት አንተ በምትወደው ሥራ ላይ ሆነን እንድንሰናበት መንገዱን ምቹ አድርግልን። በሞት የተለዩንን ሁሉ በምህረትህ አካበህ ዝንተአለም የሚኖሩባት የድሎት ከተማ የሆነችው ጀነትን ወፍቃቸው። እኛንም በመጪው ዓለም ያንተ ባለሟሎች ከሆኑት ደጋግ ባሮችህ መድበን።
💕🙏💕አሚን!
Via ኡስታዝ አቡበከር አህመድ