بسم الله الرحمن الرحيم
ሰው በተፈጥሮው መከበርን ይሻል። ይሄን ክብርን ለማግኘትና አግኝቶም ለማስጠበቅ ሕይወቱን እስከመሰዋት ይደርሳል።
አንዳንድ ሰው ክብሩን በገንዘብ ውስጥ ይፈልጋል። ገንዘቡን መከበሬያዬ ነው ብሎ ይጠብቀዋል። ነገ ብከስር ማን ያከብረኛል? ማን ቦታ ይሰጠኛል? ብሎ ቆጥቦና ቆንጥሮ ይጠቀመዋል። ሰው ይበልጥ እንዲያከብረኝ ይበልጥ ማካበት አለብኝ ይላል። ይለፋል ይለፋል ይለፋል። ጌታው እስኪወስደው ድርስ...
አንዳንድ ሰው ደግሞ ክብሩን በዘሩ ውስጥ ይፈልጋል። "የኔ ዘር እኮ" ብሎ ሰው ፊት ለመኮፈስ የአያቶቹን ታሪክ ያመጣል። አያቶቹ በሰሩት መልካምም ሆነ ክፉ ታሪክ ደረቱን ወጥሮ "የተከበርኩ ነኝ" ይላል። ይህን ክብሩ አንድ ሰው ከነካበት ቅድሚያ ተሰላፊ ነው። ምክንያቱም ክብሩ ነው። ለዘሩ መሄድ እስከሚችለው ጥግ ድረስ ይሄዳል። ቅርብ ጓደኞቹን ያስቀይማል፣ ያስከፋል፣ ይመታል እንዲሁም ይገድላል። ከርሱ ዘር ውጪ ያሉት ክብረ ቢስ እርሱ ግን ባለ ክብር። ለዚህ ክብሩ ይገድላል ይገደላል።
ስለዚህ ሰው ክብሬ ነው ብሎ ሊይዘው የሚገባውን ነገር ስለሚሻ አንድ ነገርን ይፈልጋል። እዚያህ ላይም ይንጠለጠላል።
የክብሮች ሁሉ ክብር፣ እርሱን ክብራችን ካደረግን የምድርም የሰማይም ፍጡራን የሚያከብሩን አንድ ክብር አለ። ከርሱ ውጭ እውነተኛ ክብር አይኖርም። ይሄን ክብር ታላቁ አምላካችን አላህ ሱወ እንዲህ ብሎ ይገልፀዋል፦
ክብራችሁ በውስጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደእናንተ በእርግጥ አወረድን፡፡ አታውቁምን? (ሱረቱል አንቢያእ 10)
በአጭር አገላለፅ አላህ መከበርያ ቁርአን ነው እያለ ነው። በደንብ ካወቅከው፣ ከሰራህበት፣ ለሌሎችም ካሳወቅከው ትከበራለህ...ከበላይህ አድርገው ከፍ ትላለህ...መመርያህ አድርገው ብርሃናማው ጎዳና ላይ ትዘዋወራለህ እያለህ ነው ታላቁ ጌታህ።
ቁርአን ይመራሃል። ቁርአንን ወዳጅህ ካደረከው ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃሃል። ወደ መልካም ነገሮች ሁሉ ያደርሳሃል። ክፉ ስራ ስታስብ ይሄ ምርጥ ጓደኛህ መጥቶ እጅህን ይዞ ይከለክልሃል። "ወዳጄ ተው ይሄ ላንተ አይሆንም...አምላክህ አላህ እኮ አይወደውም...ተወው ይቅርብህ...ነፍሲያህን ከምታስደስት ሰዎች እንዲወዱህ ብለህ ከምታደርግ ይቅርብህ...የአላህ ውዴታ ይሻልሃል እርሱ ከወደደህ ሌላው ትርፍ ነው... አትጨነቅ" ይልሃል። ምን ያምር ጓደኛ?!
ኸይር ስራ ላይም ስትሰንፍ ውዱ ጓደኛህ ቁርአን ዝም ብሎ አያይህም። የስራውን ጥቅም፣ ደረጃ ነገ አላህ ዘንድ የተዘጋጀልህን ምርጥ ስጦታ ያስታወሳሃል። ተሽቀዳደም ይልሃል። እንዳያልፍህ አደራህን...ቶሎ በል በርታ...አይዞህ...ጌታህ ዘንድ ትልቅ ስጦታ ተዘጋጅቶልሃል...የርሱ ስጦታ ይበልጣል...እያለ ከደከምክ ብርታትን፤ ከሰነፍክ ጉብዝናን ይችርሃል። ዱንያ ላይ አስከብሮህ በሰላም እንድተለቃት ያደርግሃል።
ዱንያን ስትለቅ ቁርአን ግን አይለቅህም። ቀብርህ ድረስ ይመጣል። አራቱም አቅጣጫዎች ድፍን ሆኖ ጭንቅ ጥብብ ባለህ ሰዓት ይህ ጓደኛህ ይመጣል። "አወከኝ?!" ይልሃል። "ትላንት ዱንያ ሳለህ ጓደኛህ ነበርኩኝ ታድያ ዛሬ ምትወህ ይመስልሃል? ዛሬ በቀብር ኑሮ ያንተ አጫዋች ነኝ።" ሲል ያበስርሃል። ቀብርህን ብርሃን በብርሃን ኑር በኑር ያደርገዋል። በጨዋታቹህ መሃል አንተም በምርጡ ወዳጅህ መኖር እጅግ ተደስተህ "አየህ ዛሬ እዚህ ማንም የለም ከአንተ ጋር። ትላንት በዱንያና በብልጭልጮቿ ተታልለህ ብትረሳኝና ብትዘነጋኝ ዛሬ ምን ትሆን ነበር? እኔን ጓደኛ ባታደርገኝና ያኔ ሌላውን ጓደኛ ብታደርግ ማን ብርሃን ይሆንልህ ነበር? አንተ ወዳጄ ነህ ጓደኛዬ ነህ በዱንያ አልተወከኝምና አልተውህም...ቀርተኸኝ ተረድተኸኛል... ተረድተኸኝ ሰርተህብኛል.....አብሽር!" ይልሃል።
ይህ ወዳጅህ በአኺራም አይተውህም። ጌታህ ዘንድ...ራቁትህን ሆነህ... ለሒሳብ ቆመህ ...መዝገብህ ተገልጦ...ክፉ ስራህ ተወስቶ ዋ እኔ ዋ እኔ እያልክ መላው ጠፍቶህ ጌታህ ዘንድ አንደበትህ ተሳስሮህ ምትይዘው ምትጨብጠው አጥተህ...ድንገት ከየት መጡ ሳትላቸው ሁለት ላንተ ሚማልዱ ሁለት ጠበቃዎች ይመጣሉ። ዱንያ ላይ ወዳጅህ ካደረከው ቁርአን ሱረቱል በቀራና አለ ዒምራን ይማልዱልሃል። "አብሽር ወዳጃችን...የረሳንህ መሰለህ አይደል? አብሽር አረሳንህም። ጌታህ ዘንድ እኛ እንማልድልሃለን አትጨነቅ" ይሉሃል።
ምን ያምር ወዳጅ? ግን ዱንያን አሳምሮ...ቀብርን አብርቶ...አኺሯን ማልዶ... የሚወዳጅህ ከቁርአን ውጪ የትኛው ጓደኛህ ይሆን? አደራህን ወዳጅህን ተወዳጀው። አትተወው። ያዘው። ጨብጠው። አንበበው። ተረዳው። ስራበት። በሶስቱም ዓለም አይተውህም።
ምን ያምር መከበርያ? ምን ያምር ክብር
#quran