UMMA TOKEN INVESTOR

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

ሰበር ድል !

እስራኤል ወደ ጋዛ ለመግባት ያደረገቺው ትግል በሀማስ አሸናፊነት ተጠናቆ ወደነበረችበች ተመልሳለች ።

ሀማስና የእስራኤል ጦር ከፍተኛ ትንቅንቅ ሲያደርጉ ከቆዩ በሗላ የዛሬውን የእስራኤል ወረራ ሀማስ መቀልበስ ችሏል ። የእስራኤል ጦርም ወደሗላ አፈግፍጓል ።

የሀማሱ ከፍተኛ ባለስልጣን ኦሳማ ሀምዳን አሁን እንደገለፀው እስራኤል እጅግ የበዛ የአየር ድብደባ እያደረገች ያለቺው ለራሷ ያሸናፊነት ስሜት ለመፍጠር ነው ብሏል ። በምድር የመጣውን የእስራኤል ጦርን አሳፍረው መመለሳቸውንም ገልጿል !

ቴሌግራም

👉 t.me/Seidsocial

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እኔ ፍልስጤማዊያን እጆግ የሚደንቀኝ ጀግንነታቸው አይደለም ! ማንም ጀግና ሊሆን ይችላልጰ!

እኔ ከነርሱ እጅግ ድንቅ የሚለኝ ሶብራቸው ነው ፅናታቸው ! የእነርሱን ፅናት ማንም ህዝብ ላይ አንብቤውም አይቼውም ሰምቼውም አላውቅም !

ቤተሰባቸው አልቀው ፅኑ ናቸው ሶብረኛ ! አካላቸው ጎድሎ እግራቸው እጃቸው ተቆርጦ አይናቸው ጠፍቶ ተስፋ ቆርጠው አይቀመጡም ! ይወጣሉ ይፋለማሉ ይታገላሉ ! ተስፋ አይቆርጡም አይደክሙም አይዝሉም ልባቸው ተሰብሮ አይልፈሰፈሱም ! መላው ምእራባዊ ሀገር ጠላታቸው ሆኖ አያለቃቅሱም ! ታግለው ቢችሉ ጥለው ይወድቃሉ እንጅ ተነፋርቀው ጠላቶቻቼውን አያስደስቱም !

ይሄ ጀግና የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ዋኢል አልደህዱህ የፍልስጤማውያን ፅናትና ሶብር አንዱ ማሳያ ነው ።

ትላንት መላ ቤተሰቡን አጣ ልጆቹን የልጅ ልጆቹን ባለቤቱን ተነጠቀ ። ቤተሰቦቹን ራሱ ሶላተል ጀናዛ አሰግዶ ኢማም ሆኖ ቀበረ ። ከዚያስ ከዚያማ ህዝቡ ትግል ላይ ነውና የቤተሰቦቹን ሀዘን ተቀምጦ ከማዘን ይልቅ ወደ ስራ ገበታው ተመለሰ ።

ታድያ ፍልስጤማዊያን የእርሱን ድምፅ በሚፈልጉበት ሰአት እንደት ለሀዘን ይቀመጥ !

ወላሂ ይሄንን ከፍልስጥኤማውያን ውጭ ማንም ያደርገው አይመስለኝም !

ምን አይነት ኢማን የው ? ምን አይነት ሶብር ነው ? ምን አይነት ኢስቲቃማ ነው ? ምን አይነት ጀሀድ ነው ? ምን አይነት ጀግንነት ነው ? ለነርሱ ብቻ ተነጥሎ የተሰጣቸው ?!!!

በመጨረሻም ተንታኞች ጋዜጠኛውን ካዩ በሗላ ያሉትን ልንገራችሁ " እነዚህን ህዝቦች ማሸነፍ አይቻልም !!!!"

#seid_mohammed_alhabeshiy

ቴሌግራም

👉 t.me/Seidsocial

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

" ምእራባውያንን የፍልስጤሞች መገደል የማያሳስባቸው የሚገደሉት ሙስሊሞች ስለሆኑ ነው "

ፕሬዝዳንት ረጄብ ጦይብ ኤርዶጋን

ኤርዶጋን ላለፉት 20 አመታት ከምእራባውያን ጋር ባደረጉት እልህ አስጨራሽ የፖለቲካ የድፕሎማሲና የኢኮኖሚ ትግል ቱርክን ከፍተኛ ዋጋ ስላስከፈላት የአረቦች ከምእራባውያን ጋር አብረው በቱርክ ላይ ማደምም ብዙ ተፅዕኖ ስለፈጠረባት ከዚያ ጫና እፎይታ ለመውሰድ ኤርዶጋን ባለፉት ወራት ለዘብ ማለትን መርጦ ነበረ ። ግና በፍልስጤም ጉዳይ ሁሌም ስሜታዊ የሆነው ኤርዶጋን የፍልስጤማውያን በወራሪዋ ሀገርና ግብረአበሮቿ መጨፍጨፍ ዳግም ከምእራባውያን ጋር ትግትግ እንዲገጥም አስገድዶታል ።

ኤርዶጋን አሁን ከምእራባውያንና ከእስራኤል ጋር የቃላት ጦርነት ላይ ነው ።

በኢኮኖሚና በማህበራዊ ድጋፍ የጋዛ የጀርባ አጥንት ከሆኑ ሀገሮች አንዷ የሆነቺው ቱርክ አሁን ዳግም ከምእራባውያን ጋር ያገረሸ ንትርክ ውስጥ ገብታለች ምክንያቱ ደግሞ የፍልስጤማውያን እልቂት ነው ።

ኤርዶጋን ዛሬ በሰጠው መግለጫ " ምእራባውያን ስለምን ለሚገደሉት ንፁሀን ያዝናሉ የሚሞቱትኮ ሙስሊሞች ናቸው የሙስሊሞች መሞት ደግሞ ለምእራባዊያን የሚያስደስት እንጅ የሚያሳዝን አይደለም " በማለት የምእራባውያን ይህ ሁሉ ፍርደገምድልነት ዋነኛው ምክንያት ኢስላም ጠልነት ሙስሊም ጠልነት ነው በማለት አውግዘዋቸዋል ።

ኤርዶጋን ለፍልስጥኤም ድጋፍ ሀገራትን ለማስተባበር እየሞከረ ቢሆንም ከሙስሊም ሀገራት የሚሰጠው ምላሽ ግን አሳዛኝ ነው ።

ቱርክና ኢራን ስለፍልስጤም በጋራ በሚቆሙበት ጉዳይ ላይ ከትላንት በስቲያ ሙምከራቸው የሚታወቅ ነው ።

ኤርዶጋን ሀማስን ሀገሩንና ህዝቡን ከወራሪዎች ነፃ ለማውጣት የሚታገል አርበኛ በማለት መግለፁ እስራኤልን ክፉኛ አስቆጥቷት የውግዘት መግለጫ እንድታወጣ መሆኑ ይታወሳል ። ኤርዶጋን አክሎም እስራኤልን " ህፃናትና ንፁሀንን ኢላማ አድርጎ የሚዋጋ ቤተእምነቶችን የሚያደወድም ብቸኛ ጦር ያላት ሀገር " በማለት ማውገዛቸው ይታወቃል።

ቱርክ እስራኤል ወደ አውሮፓ በቱርክ ግዛት ለማስተላለፍ ያሰበቺውን የጋዝ መስመርም እንድታቋርጥ አዛለች ።

#seid_mohammed_alhabeshiy

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

" በፍፁም ብቻችሁን አትጓዙም ! YOU WILL NEVER WALK ALONE !"

ይህ አሁን የሊቨርፑል ደጋፊዎች ለተጫዋቾቻቼው የሚዘምሩት መዝሙር አይደለም ። ይህ የታላቁ ክለብ የሴልቲክ ደጋፊዎች በስታዲዮማቸው ለፍልስጤማውያን የሚዘምሩት መዝሙር ነው ።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እዚያው እስራኤል ሂዶ እስራኤል ብቸኛ የሆነች ይመስል " እስራኤል ሆይ ብቻሽን አይደለሽም " አላት ። የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክም እስራኤል ተጉዞ እስራኤልን " ብቻሽን አይደለሽም " አላት ! የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማክሮንም እዚያው ሂዶ " እኔ እዚህ የመጣሁት እስራኤልን ብቻዋን እንዳልሆነች ለማሳየት ነው " አለ ። የጀርመኑ መርሀይተመንግስት ኦላፍ ስኩልዝም እስራኤልን " ጀርመን እያለች ብቻሽን አይደለሽም " አላት ። ብቸኛ ያልሆነቺዋንና መላ ምእራባዊ እንደ ልጁ የሚንከባከባትን እስራኤልን ብቻሽን አይደለሽም እያሉ ሲንቆለጳጵሷት የኔ ነሽ የኔ ነሽ ሲሏት በርግጥ ንፍቅናቸው ግብዝነታቸው ፍርደገምድልነታቸዝ አፍጦ ያገጠጠ መሆኑን ከማረጋገጥም በላይ ምን ያክል የሰብአዊነት ርዝራዥ እንኳ የሌለባቸው መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው ።

በሰብአዊነት የተሞሉት ሀቀኞቹ የሴልቲክ ደጋፊዎች ግን ብቸኛዎቹን ፍልስጤማዊያንን " ብቻችሁን አትጓዙም " እያሉ ሲዘምሩላቸው ምናልባት ሰብአዊነት ያለው ሰው እንባውን መገደብ ሀዘኔታውንም መቋቋም ሊያቅተው ይችል ይሆናል ። እነዚህ የሴልቲክ ሰው የሆኑ የሰውነት ውሀ ልኮች የአውሮፓ ኦግርኳስ ማህበር የጣለባቸውን ቅጣት ንቀው ስለሰብአዊነት የዘርና የሀይማኖት ድንበር ሳይገድባቸው ሜድትራኒያን ባህርን አቋርጠው ስለፍልስጤማዊያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አሰሙ ። " ከነፃዋ ፍልስጥኤም ጎን ነን ፍልስጤምም ነፃ ትወጣለች " አሉ ! ፍልስጤማዊያን ሆይ በዚህ የነፃነት ትግልም ውስጥ ብቻችሁን አትጓዙም ሁሌም ከጎናችሁ አለን YOU WILL NEVER WALK ALONE ሲሉ ከአንጀታቸው ከልባቸው አጋርነታቸውን አሳዩ ። በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተከታታይም የአትሌቲኮ ማድሪድንና የሴልታክን ጨዋታ ሊከታተል በቲቪ አፍጥጦ ሳለ የፍልስጤማውያንን የነፃየት የአልገዛም ባይነት ድምፅ በሴልቲክ ደጋፊዎች አማካኝነት ሰማ !!!

የአረብ ሀገራት መሪዎችና ተመሪዎች አፋቸው ተለጉሞ ጆሯቸው ተደፍኖ እጃቸው ተሳስሮ ሳለ እነዚያ የምእራብ አውሮፓ ሰብኦች ግን ሀሳብና ጭንቀታተው በስታዲየሙ የምትንከባለለው ፊኛ ሳትሆን እዚያ በጋዛ ፍርስራሽ ስር ስለነፃነት የሚከፈለው ዋጋ ነው !!!

የሴልቲክ ደጋፊዎችን የማመሰግንበት ቃል የለኝም !!

አንድ ቀን ፍልስጤማዊያን ነፃ ይወጣሉ ያኔ በፍልስጤማውያን ልብ ዘንድ የሴልቲክ ደጋፊዎች ታትሞ ሲወሳ ይኖራል !!!

#seid_mohammed_alhabeshiy

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሀማስ ጥቃቱን ከመፈፀሙ በፊት አይሁዶች መስጅድ አልአቅሷ ውስጥ ገብተው እየቀደሱ ነበር ። እነርሱ ሲገቡም ሙስሊም ሰጋጆችን የእስራኤል ጦር እየደበደበ ከመስጅዱ ሲያስወጣ ነበር ። ከዚያ የተረፉትን ደግሞ መስጅድ ውስጥ አስሮ በጀርባቸው አስቸኝቶ ይሳለቁበቸው ነበር ። ሙስሊም ሰጋጆች ታስረው አይሂዶች ደግሞ መስጅዱ ላይ እየጨፈሩበት ነበር ።

ይህ የአልአቅሷ መደፈር ያንገበገባቸው ሀማሶች ናቸው " የአልቅሷ ጎርፍ " የሚል ድንገተኛ ጦር በእስራኤል የከፈቱት ። ይህ የኢስላም ክብር መነካት ቆጭቶት ለመሰዋት መዝመት ሀማሶችን መሆን ይጠይቃል ።

እስራኤል አልአቅሷን ለመጠቅለልና ወደ አይሁድ ቤተመቅደስነት ለመቀየር ስራዋን እየጨረሰች ለዚያም እንዲረዳት ሳኡዲ አረቢያን ጨምሮ ከአረብ ሀገራት ጋር ወዳጅነቷን እያጠናቀቀች ባለችበት ወቅት ነው ሀማስ መብረቃዊ ጥቃት ሰንዝሮ ያቃዣት ።

ዛሬ በሀማስ የደረሰባትን ውርደትና ሽንፈት ለማካካስ ነው ንፁሀንና ህፃናት ላይ ሚሳኤል የምታዘንበው ። በእግር ለመግባትማ ሀማስ ያዘጋጀላቸውን የሞት ድግስ አያውቁትም !

#seid_mohammed_alhabeshiy

ቴሌግራም

               👉 t.me/Seidsocial

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group