UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

اسلام عليكم ورحمة لله وبركاته

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የፍልስጤም ነፃነት ከሶርያ ጋር የተያያዘ ነው። ፍልስጤም ነፃ የምትወጣው ሶርያ ነፃ ስትወጣ ነው። ነቢዩ (ዐሰወ) በመጨረሻው ዘመን ሶርያ ዳቢቅ ላይ ከመስቀለኞች ጋር ጦርነት እንደሚደረግና ሙስሊሞችም አሸንፈው ሻምንና የተቀረውን ዓለም እንደሚከፍቱ እንዲህ ተናግረዋል፡-

«ሮማውያን አል-ዓማቅ ወይም ዳቢቅ ላይ ሳይዘምቱባችሁ በፊት ቂያማህ አትቆምም። በዚያን ጊዜ የዓለም ምርጥ የሚባሉት ህዝቦች ከመዲና ሊገጥሟቸው ይወጡና ከባድ ጦርነት ይጀመራል። በውጊያውም መሀል ከሙስሊሞች አንድ ሶስተኛው ይሸሻሉ። አንድ ሶስተኛው ሸሂድ ይሆናሉ። ቀሪዎቹ አንድ ሶስተኛው ደግሞ ያሸንፋሉ። ከዚያም ሸይጧን ይነሳና ደጃል አገራችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ይዞባችኋል! ይላቸዋል። በዚህ ጊዜ ወደ አገራቸው ይመለሳሉ። ነገርግን የተባለው ውሸት ሆኖ ያገኙታል። ከዚያም ለሁለተኛ ጦርነት ወደ ሻም ሲመጡ ደጃል ይወጣልና ይከባቸዋል። በዚህ ጊዜ ዒሳ ኢብኑ መርየም ይወርድና መሪያቸው ይሆናል። የአላህም ጠላቶች ፊትለፊት በተገናኙት ጊዜ እንደ ጨው ይቀልጣሉ። ዒሳም በጦሩ ጫፍ ላይ ደማቸውን ለምልክት ያሳያቸዋል።»

(ሙስሊም፥ 2897)

ይህ የመጨረሻው ጦርነት እስኪፈፀም ደግሞ በሻምና በፍልስጤም ዙርያ በእምነታቸው ፀንተው የሚታገሉ ይኖራሉ። ነቢዩ (ዐሰወ) ስለነዚህ ቡድኖች ሲናገሩ እንዲህ አሉ፡-

‹‹ከሕዝቦቼ የተወሰኑ ቡድኖች በኃይማኖታቸው ፀንተው ይቆያሉ። ጠላቶቻቸውንም ያሸንፋሉ። የተቃወማቸው አይጎዳቸውም። በርግጥ መከራና ችግር ያገኛቸዋል። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ የአላህ ውሳኔ (እርዳታ) ይፈፀማል።›› አሉ። ሰሃባዎችም ‹‹የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እነኝህ ኃይላት የት ይገኛሉ?›› በማለት ጠየቋቸው። ነቢዩም (ዐሰወ) ‹‹በበይተል መቅዲስ (ቁዱስ) እና በዙሪያዋ›› በማለት መለሱ።››

(አህመድ)

ኢብኑ ተይሚያህ ‹‹እነዚህ ቡድኖች እንደማንኛውም ‹ሙስሊም› ብቻ የሚባሉ ሳይሆኑ ትክክለኛውን መንገድ አጥብቀው የያዙና የአላህ ውሳኔ እስኪመጣ ድረስ ፀንተው የሚቆዩ ናቸው።›› ብለዋል።

አላህ የድል መክፈቻውን ቀን ቅርብ ያድርገው

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Muhammed Ahmed is feeling In love
7 month Translate
Translation is not possible.

اسلام عليكم ورحمة لله وبركاته

Send as a message
Share on my page
Share in the group