UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

🌹ረሱል ﷺ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በዱኒያ ላይ በጣም ስለሚዎዷቸው ነገሮች

አየተጨዋወቱ እያሉ ነብዩ ﷺ አቡበክርንረ.ዐ "ያ አባ በከር አንተ በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው

ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት።

አቡበክርም  ረ.ዐ "3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.ከአንቱን ጋር መቀመጥ፣

2.አንቱን ማየት፣

3.አንቱ ባዘዙዋቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ።

°

ዑመርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?"

"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ

1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣

2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣

3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ።

°

ዑስማንን ረ.ዐ ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን?

በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.ሰዎችን ማብላት፣

2.ሰላምታን ማብዛት፣

3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣

°

አልይን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?"

"በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.እንግዳን ማክበር፣

2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣

3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣

°

አባ ዘርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?"

"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :-

1.እርሃብን እወዳለሁ፣

2.በሽታን እወዳለሁ፣

3.ሞትን እወዳለሁ፣

ነብዩም ﷺ "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?"

አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣

በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣

ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ።

°

ነብዩ ﷺ " እኔም በዱኒያ ላይ

3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.ሽቶን እወዳለሁ፣

2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣

3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣

በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል አ.ሰ.ወ ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ

"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ

ነብዩም ﷺ "ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት።

1.መልዕክትን ማድረስ፣

2. አማናን አደራን መጠበቅ፣

3.ሚስኪኖችን መውደድ፣

ጅብሪል አ.ሰ.ወ ተመልሶ ወደ ከሄደ በኋላ ረሱልና ﷺ ሱሃቦቻቸው ረዲየሏሁ አጅመኢን ከመቀመጫቸው ሳይነሱ

ተመልሶ መጣና አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:-

"አላህም ሱ.ወ. ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም ሱ.ወ እንዲህ ብሏል:-

በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣

2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣

3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ።

አላህ ሱ.ወ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ﷺ ሱሃቦች ረ.ዐ.አ የወደዱትን ያስወድደን!

°

Follow & Share →Abubekr Ibn Fulan

↓↓↓↓

Abubekr Ibn Fulan

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ዘሬ ጁማህ በዉዱ ረሱለችን ሰለወት እነውርድ (ሰለአለህ አለይ ወሰለም)

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

በሚሰግድ ሰው ፊት አቋርጦ ማለፍ አደጋ አለው!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لَوْ يَعْلَمُ الْمَارُّ بَيْنَ يَدَيِ الْمُصَلِّي مَاذَا عَلَيْهِ لَكَانَ أَنْ يَقِفَ أَرْبَعِينَ خَيْرًا لَهُ مِنْ أَنْ يَمُرَّ بَيْنَ يَدَيْهِ﴾

📌 ﴿قَالَ أَبُو النَّضْرِ : لَا أَدْرِي أَقَالَ أَرْبَعِينَ يَوْمًا أَوْ شَهْرًا أَوْ سَنَةً﴾

“ከሰጋጅ ፊት የሚያልፍ ሰው ያለበትን ወንጀል ቢያውቅ ኖሮ፤ ከሚያቋርጥ አርባ መቆሙ በተሻለው ነበር።”

📌 አቡ ነድር እንዲህ ይላሉ፦ “አርባ ቀናት ወይም ወር ወይ አመት የትኛውን እንዳሉ እርግጠኛ አይደለሁም።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 510

ጆይን፦ https://t.me/BuhariMuslimAmharic

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ፍልስጤሞችን ለመርዳት ከዱዓ በተጨማሪ ከቀላሉ ነገር እንጀምር

👌የኮካና ፔፕሲ ምርቶችን መጠቀም እናቁም

ጤነችንን እየጠበቅን ወንድሞቻችንን እንደግፍ

image
image
image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group