#ኑ_ረሱላችንን_እንውደድ
ነብዩ (ሠለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሶሃቦቻቸው ጋር በጉዞ ላይ ሳሉ ፍየል እንዲታረድ አዘዙ:: ከእነሱም አንዱ ሱሃባ ማረዱ የኔ ፋንታ ነው አለ:: ሁለተኛው ደግሞ ቆዳውን መግፈፍ የኔ ፋንታ ነው አለ:: ሦስተኛው ደግሞ መቀቀሉ (ስጋ ማብሰሉ) የኔ ፋንታ ነው አለ:: ነብዩ (ሠለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በበኩላቸው "ለማገዶ የሚሆን እንጨት መልቀሙ የኔ ፋንታ ነው" ሲሉ ሶሃባዎቹ እኛ እንበቃለን ያ ረሱሉላህ ሲሏቸው "እንደምትበቁ አውቃለሁ ነገር ግን ከእናንተ የተለየ ክብር እንዲኖረኝ እጠላለሁ ብለው እንጨት መልቀም ጀመሩ::
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد
ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሠለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)
የአንድ ቀን አጭር ገጠመኛቸውን እንይ
የሀቢቢ(ሠለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአንድ ቀን አጭር ገጠመኝ።
አንድ ግዜ ነብዩ ወደ አንድ ቦታ እየሄዱ ነበር።በአካባቢያቸው የሚሆነውን ለመቃኘት ግን ብዙም አልከበዳቸውም ነበር። አይናቸው ከተማዋ ውስጥ ከሚተራመሰው ሰው መሃል አንድ አገልጋይ(ባሪያ) ላይ አረፈ። ይህ አገልጋይ የተከመረ እህል አስቀምጦ እየፈጨ ነው። ከአይኖቹ የሚንከባለለው የእንባው ፍሬ ፊቱን ማርጠቡ የነብዩን ልብ ስቧል።ያ ሩህሩህ ነብይ ይህን አይቶ ማለፍ እንዴት ይቻለዋ። ከወደ ሰውየው ዘንድ ተጠጉ።
በተረጋጋ ድምፅም ስራውን አየሰራ ስለሚያስለቅሰው ጉዳይ ጠየቁት።
አገልጋዪም: "ዛሬ በጣም ታምሜያለው። ስራ መስራት አልቻልኩም።ማረፍ እፈልጋለው። ነገር ግን አይደለም ካልሰራው ከዘገየው እንኳ የአለቃዬ ቅጣት ከባድ ነው። እየው እሱን ፈርቼ ከነህመሜ እየፈጨው ነው። የህመሜ ስሜት ነው የሚያስለቅሰኝ።"አላቸው።
ነብዩ የዚህን አግልጋይ ችግር ሲሰሙ በጣም አዘኑለት። ያግዙት ዘንድም መሳሪያውን እንዲሰጣቸው ጠየቁት። መፍጫውን ተቀብለው በራሳቸው ይፈጩለት ጀመሩ። አገልጋዩም ከስራው አረፍ አለ።
ነብዩ የነበረውን እህል በሙሉ ፈጭተው ጨረሱለት። ሊሄዱ ሲሉም እንዲህ አሉት "ከዚህ ቡሃላ ከአቅም በላይ የሆነ ስራ ካጋጠመህ፣ በህመም ምክንያት ስራ መስራት ቢያቅትህ የአለቃህን ቅጣት ከፈራህ እኔን ጥራኝና አግዝሃለው።" ብለው ቃል ገቡለት።
አገልጋዩም ዕረፍት ሰጥተው ስራውን የሰሩለትን ሰው ማመስገኛ ቃላት አጣ።(ደስ አለው)
የኛ አህመድለ ተቸገሩ እና ለተገፉ ደራሽ። እርዳታ ለሚሹ አጋዥ ነበሩ።
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد
ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም (ሠለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)