Rosa Ahmed Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Rosa Ahmed shared a
Translation is not possible.

ያረብ ፀጋ ስትውልላቸው ከሚያመሰግኑህ፣ ችግር ሲገጥማቸው በሶብር ከሚያልፉት፣ ኋጢዓት ሲሰሩ ኢስቲግፋር/ምሕረትን ከሚጠይቁህ ባሮችህ ውስጥ አድርገን!🤲

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Rosa Ahmed shared a
Translation is not possible.

#አላህን_ለማስታወስ_አዘውትሮ #መሰባሰብ_ተወዳጅ_ተግባር #ስለ_መሆኑና #ካለ_ምክንያት #አላህን_ከማስታወስ_ስብስቦች #መልለየት_ስለመከልከሉ

#ክፍል_3

#ሐዲሥ 247 / 1449

አቢ ዋቂድ ሐሪሥ ኢብኑ ዐውፍ እንዳስተላለፉት፥ የአላህ መልዕክተኛ መስጊድ ውስጥ ከሰዎች ጋር ተቀምጠው እያለ ሦስት ሰዎች መጡ። ሁለቱ ወደ አላህ መልዕክተኛ በመምጣት ከርሳቸው ዘንድ ቆሙ። አንደኛው ሔደ። አንደኛው ከስብስቡ መሐል ክፍት ቦታ አየና ተቀመጠ። ሌላኛው ደግሞ ከስብስቡ በኋላ ተቀመጠ። ሦስተኛው ግን ተመልሶ ሔደ። የአላህ መልዕክተኛ ጉዳያቸውን ሲያጠናቅቁ እንዲህ አሉ፦ "ስለነዚህ ሦስት ሰዎች ሁኔታ ልንገራችሁን? አንደኛው ወደ አላህ ተጠጋ፤ አላህም አስጠጋው፤ ሁለተኛው ትሁት ሆነ፤ አላህም ለርሱ ትሁት ሆነለት፤ ሦስተኛው ሸሸ፤ አላህም ከርሱ ሸሸ።" (ቡኻሪና ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ የዲን እውቀት ከሚሰጥባቸው ስብስቦች መቀመጥ ይወደዳል።

2/ ክፍት ቦታ ካገኙ እዚያ መቀመጥ፥ ካልሆነ ሰዎችን አለማጣበብና አለመጨናነቅ።

3/ የትሕትና (ሐያእ) ልቅናና ጠቀሜታ።

4/ ከእውቀት ቦታዎች መሸሽ የተወገዘ ተግባር ነው። ያለምክንያት የእውቀት ማዕዶችን የሸሸ ለአላህ ቁጣ ራሱን አጋልጧል።

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Rosa Ahmed shared a
Translation is not possible.

ብዙ ሰዎች ራሳቸውን ሲያታልሉ አያለሁ በእርግጥ እኔም በፊት እንደዛ ነበር ማስበው

#ትዳር ስኬት አይደለም  ስኬት ሰርቶ መለወጥ ነው ምናምን ብለው ይከራከራሉ ሰርቶ መለወጥ ትዳር ኖረህም አልኖረህም ሁሌም ምታስበው ነገር ነው።

ነገር ግን ለፍተህ የፈለከው ነገር ቢኖርህም ያለ ትዳር ትርጉም ያጣል። የምር ያኔ ገንዘብ ምንም ደስታ እንደማያመጣልህ ትረዳለህ። ስኬት ለገንዘብ መሮጥ ብቻ ሳይሆን አሪፍ ቤተሰብም መመስረት ለዛ ቤተሰብህ ደስታ መልፋትም ነው

https://t.me/SileTidarEnmekaker

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Rosa Ahmed shared a
Translation is not possible.

በጋዛ አልሺፋ ሆስፒታል ከጊዜ ገደብ ቀደም ብለው የተወለዱ 39 ህፃናት ይገኛሉ በእስራኤል እምቢተኝነት የነዳጅ አቅርቦት በመቋረጡ ጄኔሬተር የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት በማቆሙ ህፃናቶቹ ከኢንኩቤተር ለመውጣት ተገደዋል

እስካሁን ሁለት ህፃናት በኦክስጅን እጥረት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በቀጣይ ሰአታት የነዳጅ አቅርቦት ካልተገኘ ቀሪዎቹም ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ዶክተሮች አሳስበዋል

ስለ እንስሳት መብት የሚያስተምሩን ምዕራባውያን ግን የፍልስጤም ህፃናትን ህይወት ታደጉ ጥሪ እስካሁን ምላሽ አልሰጡም

ግፍ ሞልቶ ፈሰሰ

Bilal Zayed

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

♨️አንዳንድ ሚድያ ላይ ሴቶች ተጨንቀው አማረብኝ አላማረብኝም እያሉ ተጣበው ተኳኩለው ፎቶዋቸው ለሽያጭ ከሚፓስቱት ይልቅ ሚያናዱት  ማሻ አሏህ ዋው ዊው የሚሉት የኮሜንት ሱሰኞች ናቸው።

እስቲ አሁን አልሸጥ እንዳለ እቃና እንደ ቃረደ ልብስ እራሷን አሰማምራ ፎቶዋ አደባባይ የምትለጥፍ ሴት ማሻ አሏህ ማለቱ ምን አመጣው? እንደውም ማሻ አላህ እያሉ ለሌላ ጥፋት ከማበረታታት ይልቅ ሁለተኛ እንዳይለመዳት አጨፍርጎ መመለስ ነውጂ የምን በማሻ አላህ እያበረታቱ ወጀ ጀሀነም እሳት መግፋት ነው። እኔ ማውቀው የቃረደ ልብስ አልሸጥ ሲል ባሻንጉሊት አሰማምሮ አዲስ እንዲመስል ፊት ለፊት ገጭ ይደረጋል ግን አዲስ ነገር ከሆነ ውስጥ ቢቀመጥም ስለሚሸጥ አያስጨንቅም አዲስ እቃ ለሚፈልግ ከውስጥ ይወጣለታል ልክ እንደዚሁ አልሸጠ ያለ እቃና ተኳኩላ ሚድያ ላይ ፎቶ ምትለጥፍ ሴት እንደኔ አመለካከት ሁለቱ መሀከል ፈርቅ(ልዩነት) የላቸውም መብቴ ነው።!

እርግጠኛ ነኝ ፎቶ ከሚለጥፉ ሴቶች ስር እንደው በትንሹ ከመቶ በላይ የላይክና የኮሜት ጋጋታ ይደረደራል ግን በፎቶው ቦታ ስለተውሂድ ስለዲን ነክ ነገር ቢፖሰት አስርኳን የሚሞላ ላይክና ሼር ሚገኝ አይመስለኝም አቤት ሸይጣን ምንኛ ተሳካለት ጃል!

Send as a message
Share on my page
Share in the group